ChatCrawlersearch across public Telegram Open the app
E

Eva show በኮንስትራክሽን ዙሪያ መወያያ ገጽ

1 925 members
30 August 2026
31 August 2026
የዛሬው የነሀሴ 25 ቀን 2018 ዓ.ም የኢትዮ ኮን የሬድዮ ፕሮግራም ዝግጅት እና የውይይት መነሻ 🏗 ሰላም ውድ የኢትዮ ኮን የቴሌግራም ቻናል ቤተሰቦች እና የሬድዮ አድማጮቻችን! ዛሬ ማምሻውን ከ2:00-3:30 በአሀዱ ራዲዮ 94.3 አበይት የፕሮግራም ይዘቶች ጋር በጉጉት እንጠብቃችኋለን። የዛሬው ዝግጅታችን ዋና ዋና ክፍሎች የሚከተሉት ናቸው 🎙 1. የእንግዳ ሰዓት (ክፍል ሁለት) በሀገራችን የኮንስትራክሽን ዘርፍ ውስጥ ታይቶ የማይታወቅ ትልቅ ለውጥ ያመጣል ተብሎ የሚጠበቀውን አዲስ ዲጂታል ፕላትፎርም ሊያወቁ ዝግጁ ኖት? በዓመት እስከ 300 ቢሊዮን ብር ማዳን የሚያስችለውን እና በአፍሪካ ደረጃ የመጀመሪያ የሆነውን የተቀናጀ ሥነ-ምህዳር (Ecosystem) ፈጥሮ ወደ ሥራ የገባውን 'ኤቫኮኔት' (Evaconect) ፕላትፎርም ባለቤትና የሲቪል መሐንዲስ የሆነውን እንግዳችንን አቤሴሎምን መለሰ ዛሬ ምሽት በቀጥታ ስርጭት ጋብዘን ሰፋ ያለ ቆይታ እናደርጋለን። 💬 2. ወቅታዊ ፕሮግራም አዲስ አበባ ዓለም አቀፍ ድምቀት ለሚሰጥበት ታላቁ የኮፕ 32 (COP-32) ጉባኤ ከወዲሁ ሰፊ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎችን ማከናወን ጀመረ! ከተማችን አዲስ አበባ ከዓለም ዙሪያ የሚመጡ እጅግ በርካታ እንግዶችን ለመቀበል ስትዘጋጅ፣ የኮንስትራክሽን፣ የሪል ስቴት እና የሆቴል ዘርፍ ባለሙያዎች በሰፊው የተሳተፉበትን መድረክ በወቅታዊ ፕሮግራማችን በጥልቀት እንመለከተዋለን። 📢 የአድማጮች ተሳትፎ የእርስዎን ጥያቄ፣ ሃሳብና አስተያየት በፕሮግራማችን በቀጥታ እንቀበላለን። ሃሳብዎን ለመጋራት እና ከእንግዳችን ጋር ለመወያየት ዝግጁ ይሁኑ! 📩✉️ 0974466655 ለአጭር የጽሁፍ መልዕክት መስመሮቻችን ክፍት ናቸው። “የነገውን ግንባታ በጋራ እንገንባ!” 🏗 🇪🇹🏗
3.7K ·
በአሀዱ ሬዲዮ ምሽት ከሁለት ስአት ጀምሮ ይጠብቁን
A
Фотография
click to show
1 September 2026
T
💫 ኢትዮ ኮን መረጃ 🔲 የግንባታ ፕሮጀክት ፊዚካል አፈጻጸም መለኪያ ስታንዳርድ ይፋ ተደረገ። ​ለሀገራችን የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ዘርፍ እድገት ከፍተኛ ሚና የሚጫወት አዲስ የፕሮጀክት ፊዚካል አፈጻጸም መለኪያ ስታንዳርድ ዛሬ ነሐሴ 26 ቀን 2018 ዓ.ም. ይፋ ተደረገ። ​በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የከተማና መሠረተ-ልማት እና ትራንስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ እንዲሁም የዘርፉ ተዋናዮችና ባለድርሻ አካላት በተገኙበት አዲስ የተዘጋጀው የስታንዳርድ ማዕቀፍ አዲስ አበባ በሚገኘው ሀርመኒ ሆቴል ላይ በተዘጋጀ መድረክ ይፋ ተደርጓል። ​በመድረኩ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር መስፍን ነገዎ (ዶ/ር)፤ ስታንዳርዱ የአንድ ፕሮጀክት አፈጻጸምን ብቻ ለመለካት ሳይሆን፣ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪውን ብቃት፣ ምርታማነት፣ ጥራትና ተወዳዳሪነት ለማሳደግ ወሳኝ ሚና እንዳለው ገልጸዋል። ​ለኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪው የሚኖረው ቁልፍ ጠቀሜታዎች፦ ​የፕሮጀክት መዘግየትን መቀነስ፦ የግንባታ ስራዎች በታቀደላቸው ጊዜና የጥራት ደረጃ እንዲጠናቀቁ በማድረግ ረገድ የላቀ ሚና ይጫወታል። ​ምርታማነትንና ጥራትን ማሳደግ፦ ሀገራዊ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪውን አጠቃላይ ብቃት በማሳደግ የሥራ ጥራት ደረጃዎች እንዲከበሩ ያደርጋል። ​ተጠያቂነትን ማስፈን፦ በግንባታ ሂደቶች ላይ ግልጽነትን በመፍጠርና የክትትል ስርዓትን በማጠናከር ተጠያቂነትን ያሰፍናል። ​የኢንቨስትመንት እምነትን ማሳደግ፦ የኢንዱስትሪውን መረጃ አስተማማኝ በማድረግ ባለሀብቶችና አጋር አካላት በዘርፉ ላይ ያላቸውን እምነት ከፍ ያደርጋል። ​ተወዳዳሪነትን ማሳደግ፦ የኮንትራክተሮችን አቅም በማሻሻል አህጉራዊና ዓለምአቀፋዊ ተወዳዳሪነታቸውን ያጠናክራል። ​የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለስልጣን የተሰጠውን ተልዕኮና ኃላፊነት በብቃት ለመፈጸም ከባለድርሻ አካላት ጋር በመደመር መርህ በጋራ እየተንቀሳቀሰ መሆኑን የገለጹት ዶ/ር መስፍን፤ በአገር አቀፍ የዘርፉ ደረጃ አዲስ የሆነው የግንባታ ፕሮጀክቶች ፊዚካል አፈጻጸም መለኪያ ስታንዳርድ ማዕቀፍ እውን እንዲሆን ተቋሙ የአጋርነት ሚና መጫወቱን አንስተዋል። ​በቀጣይም የስታንዳርድ ማዕቀፉ ወደ መሬት ወርዶ ውጤታማ እንዲሆን ባለስልጣን ተቋሙ አጋርነቱን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸው፤ የዘርፉ ተዋናዮችና ባለድርሻ አካላትም ትብብራቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪ አስተላልፈዋል። ​ይህ መረጃ የተዘጋጀው በ"ኢትዮ ኮን" መረጃ ሰንሰለት ነው።
3K ·
2 September 2026
T
​ሰላም የኢትዮ ኮን ቤተሰቦች! 🏗️ 👉​ በቅርብ ዓመታት በኢትዮጵያ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ውስጥ የሚስተዋሉ የውል አፈጻጸም መዘግየቶች እና የፕሮጀክት ማጠናቀቂያ ዋጋ ንረቶች ዋና ዋና ምክንያቶች ምን ምን ይመስሉዎታል? ​ሀሳብዎን 0974466655 አካፍሉን! 💬
3K ·
Видео
107.8 MB · click to show
"ግብጽ ለኢትዮጲያ ትሪሊዮን ብር ካሳ ልትከፍል ይገባል።" እንዴት ለምን...? ከወንድም አለም ኡስታዝ ጀማል ጋር በአባይ ጉዳይና በውሀ አጠቃቀም ዙሪያ የተደረገ ሙያዊ ውይይት ነው። አድምጣችሁ አስተያየታችሁን ስጡን
A
የግብጽ ምሁራን የውሸት ትርክት ያመከንበትን ወይይት ዘና ብላችሁ በመረጃ የተደገፈ ውይይት እስከመጨረሻው ያድምጡ
I
በጣም አሪፍ ውይይት ነው። ግብፅ ለዘመናት ያለ ከልካይ የኢትዮጵያን ውሃ ፣ ለም መሬት ፣ወርቅ ለተጠቀመችበት ተገቢውን የካሳ ክፊያ መክፈል ግዴታዋ ነው።
3 September 2026
A
የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራች በርካታ ኢትዮጵያውያን በተለይም የከተሞች ነዋሪዎች የቤት ጉዳይን በችግርነት ያነሳሉ። ይህ ችግር የቤት አቅርቦት እጥረት እንዲኖር ከማድረግ እስከ ዜጎች የተጋነኑ የቤት ኪራይ ክፍያ መጠየቅ ይደርሳል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሰኔ 30 ፣ 2018 ዓ.ም በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በነበራቸው ቆይታ አንድ ብስራት ለዚህ አንገብጋቢ የቤት ጥያቄ አብስረው ነበር። “በቀጣይ አመታት 1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ቤቶች ይገነባሉ። ለዚህም የሚያስፈልገው የሞርጌጅ ስርአት ይገነባል።” ነበር ያሉት። የቤት አቅርቦት እጥረቱን ከፈጠሩ ችግሮች መካከል የፋይናንስ አቅርቦት አለመኖር ነው። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዛሬ ለዚህ ችግር እልባት የሚሰጥ ጅማሬ ወደ ተግባር መቀየሩን አብስረዋል። ዛሬ ይፋ የተደረገው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክና የዓለም አቀፍ የፋይናንስ ኮርፖሬሽን (IFC) የደረሱበት ስምምነት፣ በሀገራችን የፋይናንስ ታሪክ ውስጥ ትልቅ ምዕራፍ የከፈተ ክስተት ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)እንዳስታወቁት፣ ይህ ስምምነት ሀገራችን የመጀመሪያውን የተለየ የቤት መግዣ ብድር መልሶ ማጠናከሪያ ተቋም እንድትመሠርት የሚያስችል ታሪካዊ የትብብር ማዕቀፍ ነው። ጉዳዩ ከቁጥሮች ባለፈ፣ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን የቤት ባለቤት የመሆን ህልማቸውን እውን ለማድረግ የተጣለ የፖሊሲ መሠረት ነው። አዲሱ ተቋም በ100 ቢሊዮን ብር ካፒታል የሚቋቋም ሲሆን፣ ዓለም አቀፉ የፋይናንስ ኮርፖሬሽን ደግሞ እስከ 200 ሚሊዮን ዶላር የሚደርስ አስተዋፅኦ ያደርግበታል። ይህ ተቋም መልሶ ማጠናከሪያ በሚል ስልት የሚሠራ በመሆኑ፣ ባንኮች ለቤት ገዢዎች የሚሰጡትን የረዥም ጊዜ ብድር ሙሉ ለሙሉ ከራሳቸው ተቀማጭ ገንዘብ ከመሸፈን ይልቅ፣ ከዚህ ተቋም ተጨማሪ የገንዘብ ፍሰት እንዲያገኙ ያስችላቸዋል። ይህ መንገድ በዓለም ላይ በበርካታ ሀገራት የተሳካ ሞዴል ሲሆን፣ የቤት ብድር ገበያን ከባንኮች የአጭር ጊዜ ተቀማጭ ጫና ነፃ በማድረግ ዘላቂነት ያለው የቤት ፋይናንስ ሥርዓት ይፈጥራል። እርምጃው ምን ችግር ይፈታል? የሚለውን እንጠይቅ... እስካሁን በኢትዮጵያ የቤት ባለቤት መሆን ለብዙ ዜጎች የራቀ ህልም ሲሆን ኖሯል። ዋነኛው ምክንያትም ረዥም ጊዜ የቤት ብድር አቅርቦት ውስንነትና ከፍተኛ ወለድ ነው። ይህ አዲስ ተቋም በመላው ኢትዮጵያ ተደራሽ የሚሆን የቤት ብድር ፋይናንስ በማቅረብ፣ በተለይ በመካከለኛ ገቢ ላይ ለሚገኙ ዜጎች፣ ወጣቶች እና ለቤተሰብ መስራች ትውልድ ትልቅ ዕድል ይፈጥራል። በተጨማሪም፣ 1.5 ሚሊዮን በተመጣጣኝ ዋጋ የሚገነቡ ቤቶች ግብ መያዙ፣ ከከተማ እስከ ገጠር ላለው የቤት እጥረት ችግር ተጨባጭ ምላሽ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል። ይህም ማለት ዜጎች ከኪራይ ውጣ ውረድ ተላቀው፣ የራሳቸውን ቤት ባለቤት በመሆን የኑሮ መረጋጋትና ማህበራዊ ክብር የማግኘት ዕድላቸው ይሰፋል ማለት ነው።
2.1K ·
የ
Within Section 4 (Cost Control), you need to look specifically at the Variations clauses (typically numbered between Clauses 37 to 41 depending on the specific standard bidding document layout for national/international competitive bidding): PPA GCC Variation Clause: It states that the Engineer has the authority to issue instructions for variations (changes to the Bill of Quantities). [1] The 25% Threshold Directive Integration: Under Ethiopia's Federal Public Procurement Directive, which governs how these Cost Control clauses are executed, once the cumulative variation orders cross 25% of the original contract price, the standard Section 4 Variation clauses stop applying. [1] According to the PPA 2011 Directive evaluation, "Variation is allowed up to 25% of the original contract price... If the total variation exceeds 25%, it is NO LONGER a simple variation. It REQUIRES a Supplementary Agreement." Are you currently analyzing Section 4 (Cost Control) to find out:If a specific change order exceeds the 25% threshold?How a new item rate should be evaluated if it was not included in the original Bill of Quantities (BOQ)?
4 September 2026
T
​🏙️ የኢትዮ ኮን የሳምንቱ የሪል ስቴት ዜና እና ትንተና ​በአሁኑ ወቅት የአዲስ አበባ የሪል ስቴት ገበያ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተቀየረ መጥቷል። የኮንስትራክሽን ግብዓቶች ዋጋ መዋዠቅ እና የከተማዋ መስፋፋት በገበያው ላይ የራሳቸው ተጽዕኖ እያሳደሩ ይገኛሉ። ​🔍 አሁን ላይ በገበያው የሚታዩ ዋና ዋና ሁኔታዎች፡ ​የቦታ ምርጫ: ከከተማ ማዕከል ውጪ በሚገኙ እንደ ለገጣፎ፣ ሰበታ፣ አያት እና ኑጂ አካባቢዎች የሚደረጉ አዳዲስ የጋራ እና የግል መኖሪያ ፕሮጀክቶች ፍላጎት እየጨመረ ነው። ​የግንባታ እቃዎች ተጽዕኖ: በሲሚንቶ እና ብረት ዋጋ ላይ የሚታዩ ለውጦች ፕሮጀክቶች በሚጠናቀቁበት ጊዜ ላይ ጫና እያደረጉ ይገኛሉ። ​የግልጽነት ፍላጎት: ገዢዎች የኩባንያዎችን ህጋዊነት እና የግንባታ ሂደት በባለቤትነት ማረጋገጥ ላይ ከፍተኛ ትኩረት እየሰጡ ነው። ​🏠 ቤት ከመግዛትዎ በፊት ማወቅ ያለብዎት 3 ቁም ነገሮች፦ ​ህጋዊነት: የድርጅቱን የሊዝ ማረጋገጫ (ካርታ) እና ከሚመለከተው አካል የተሰጠ ፈቃድ ማጣራት። ​የጊዜ ሰሌዳ: ኩባንያው ከዚህ ቀደም የሰራቸውን ፕሮጀክቶች በሰዓቱ የማስረከብ ታሪክ መገምገም። ​መሰረተ ልማት: የመንገድ፣ የውሃ እና የኤሌክትሪክ አቅርቦቶች መሟላታቸውን ማረጋገጥ። ​📌 ተጨማሪ ዝርዝር መረጃዎችን እና የሳምንቱን የኮንስትራክሽን ዙር ዜናዎች ለማግኘት ከኛ ጋር ይቆዩ! ​#EthioCon #RealEstate #Construction #AddisAbaba #Ethiopia
3.3K ·
5 September 2026
Файл
Directive_No_1073_2025_Federal_Government_Public_Procurement · 3.4 MB · click to show
A
Файл
Procurement and Property Proclamation-2024-.pdf · 1.9 MB · click to show
7 September 2026
T
🏗 አዲስ የስታንዳርድ ማዕቀፍ እና የድሬዳዋ የልማት ጉዞ ዛሬ በኢትዮ ኮን! ​በሀገራችን የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ዕድገት ታሪክ ውስጥ ትልቅ ትርጉም ያለው አዲስ ክንውን ተከናውኗል። ለዘርፉ ውጤታማነት የጀርባ አጥንት የሚሆን አዲስ የፕሮጀክት ፊዚካል አፈጻጸም መለኪያ ስታንዳርድ ማዕቀፍ ይፋ ሆኗል። ​በዛሬው ጳጉሜ 3 ቀን 2018 ዓ.ም መርሃ ግብራችን፡- ​🎙 ወቅታዊ ፕሮግራም ​አዲስ ይፋ ስለሆነው የፕሮጀክት ፊዚካል አፈጻጸም መለኪያ ስታንዳርድ ማዕቀፍ እና ለዘርፉ ከሚያበረክተው ከፍተኛ አስተዋጽኦ ጋር ዝርዝር ዳሰሳ እናቀርባለን። ​💬 የዕለቱ የከተማ ጉዞ ​በሰሜናዊው የሀገራችን ክፍል የምትገኘውን፣ በንግድና በስትራቴጂካዊ አቀማመጧ ታዋቂ የሆነችውን የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር የኮንስትራክሽንና የከተማ ልማት ጉዞ በቅርበት እንቃኛለን። ​📢 የአድማጮች ተሳትፎ የእርስዎን ጥያቄ፣ ሃሳብና አስተያየት በቀጥታ እንቀበላለን። ሃሳብዎን ለመጋራት ዝግጁ ይሁኑ! ​📩✉️ ለአጭር የጽሁፍ መልዕክት፦ [0974466655 ] ​“የነገውን ግንባታ በጋራ እንገንባ!” 🏗 🇪🇹🏗
3.3K ·
8 September 2026
T
📓ኢትዮ ኮን – የኮንስትራክሽንና የሪል ስቴት መረጃዎች ​በመርካቶ የሚገነባው የ2,500 ዘመናዊ ሱቆች ሜጋ ፕሮጀክት ይፋ ሆነ ​የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን በመርካቶ ጣና ገበያ አካባቢ ከ10,000 በላይ ዜጎች የሥራ ዕድል የሚያገኙበት እና 2,500 ዘመናዊ የንግድ ሱቆችን የሚያጠቃልል አዲስ የግንባታ ፕሮጀክት አስጀመረ። ​ 1 ነጥብ 8 ሄክታር ስፋት ባለው መሬት ላይ በ10 ሳይቶች የሚከናወነው ይህ ፕሮጀክት ባለ 5 ወለል ሕንጻዎችን፣ በቂ የፓርኪንግ ቦታዎችን እና የከተማዋን ስታንዳርድ የጠበቁ ዘመናዊ መዋቅሮችን ያካተተ ነው። ​የተቋሙ ገቢ ማሻሻያ፡ የኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዶ/ር ረሻድ ከማል በግንባታ ማስጀመሪያው ላይ እንደገለጹት፤ ኮርፖሬሽኑ ባደረገው ጠንካራ ሪፎርም ዓመታዊ ገቢውን ከነበረበት 300 ሚሊዮን ብር ወደ 12.5 ቢሊዮን ብር ማሳደግ ችሏል። ​ለግንባታ ሲባል የፈረሱ የቀድሞዎቹን 230 ሱቆች ተክቶ የኮርፖሬሽኑን ገቢ ለማስቀጠል፣ ተጨማሪ 399 አዳዲስ ሱቆች በመርካቶ አዳራሽ ገበያ አካባቢ በአጭር ጊዜ ተገንብተው በዛሬው ዕለት አገልግሎት መስጠት ጀምረዋል። ​ፕሮጀክቱ በዜሮ ኢንቨስትመንትና የግል ባለሀብቶችን አሳታፊ በማድረግ ከአንድ ዓመት ባነሰ ጊዜ ውስጥ ሙሉ በሙሉ ተጠናቀው ለአገልግሎት እንደሚበቁ ታውቋል። ​ግንባታው ለአዲስ አበባ ከተማ ኮሪደር ልማትና ዘመናዊ ገጽታ ግንባታ ትልቅ አስተዋጽኦ የሚያበረክት ሲሆን፤ ኮርፖሬሽኑ ብቁ ለሆኑ የግል አልሚዎች በጋራ ለመሥራት ጥሪ አቅርቧል።
2.7K ·
I
Please remove unnecessary posts of the spam like *xwloo3 thanks the admin of this group
10 September 2026
A
Фотография
click to show
ወንድሞቼ እህቶቼ እንኳን ለአዲሱ አመት በሰላም አደረሳችሁ። 2019 የሰላም የፍቅር የደስታ የብልጽግና ዘመን ይሁንላችሁ። እንዲህ እንደተሰባሰብን መድሃኒያለም ኢየሱስ ክርስቶስ አይለያየን🙏 አክባሪያችሁ አቤሴሎም ነኝ
T
Фотография
click to show
🌼🌼​በዕንቁጣጣሽ🌼🌼 አዲስ ዓመት 🌼🌼የኢትዮጵያ 🌼🌼የኮንስትራክሽን እና የኢንፍራስትራክሽን ዘርፍ በሰመረ የዕድገት እና የልማት ምዕራፍ እንዲሸጋገር እንመኛለን! ​"ኢትዮ ኮን" የሬዲዮ ፕሮግራም  በዘርፉ የሚከናወኑ ትልልቅ የኮንስትራክሽን፣ የሪል ስቴት፣ የመንገድ መሰረተ ልማት እና የቴክኖሎጂ ስራዎችን ባለፉት አመታት እንዳስጎበኘው ሁሉ በአዲሱ ዓመትም አዳዲስ እና ጥራት ያላቸው መረጃዎችን ይዞ ይመጣል። 🌼🌼🌼🌼🌼🌼 ​ለመላው የኮንስትራክሽን ባለሙያዎች፣ ተቋራጮች፣ መሐንዲሶች እና የኢትዮጵያ ህዝብ እንኳን ለ2019 ዓ.ም አዲስ ዓመት በሰላም አደረሳችሁ! 🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼 ​መልካም አዲስ ዓመት!🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
3.5K ·
14 September 2026
የሳምንቱ ዓለም አቀፍ የኮንስትራክሽን ዜናዎችና ቴክኖሎጂዎች 🏗️🌍 ​ለዚህ ሳምንት ዓለም አቀፍ የኮንስትራክሽን እና የሪል ስቴት ዘርፍ ትኩረትን የሳቡ ዋና ዋና ክስተቶች፣ የዘመናዊ ቴክኖሎጂ ፈጠራዎች እና የግንባታ ማሻሻያዎች ከዚህ በታች ተዘርዝረዋል፦ ​አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) በግንባታ ደህንነት ቁጥጥር ላይ በአውሮፓ እና በሰሜን አሜሪካ የሚገኙ ግንባር ቀደም የኮንስትራክሽን ኩባንያዎች የደህንነት ካሜራዎችን ከ AI ቴክኖሎጂ ጋር በማቀናጀት በግንባታ ቦታዎች ላይ ሊከሰቱ የሚችሉ አደጋዎችን አስቀድሞ የሚጠቁም ሥርዓት በስፋት እየተጠቀሙበት ይገኛሉ። ቴክኖሎጂው ሠራተኞች የግንባታ እቃዎችን (ለምሳሌ ሄልሜት እና የደህንነት ማሰሪያዎችን) በትክክል ማጥለቃቸውን በራስ-ሰር በመከታተል የሥራ ላይ አደጋዎችን በከፍተኛ ሁኔታ መቀነስ ችሏል። ​የካርቦን ልቀት ቅነሳ በሲሚንቶ ማምረቻዎች ዓለም አቀፍ የሲሚንቶ አምራቾች ማህበር ባወጣው አዲስ ሪፖርት መሰረት፣ በግንባታ ግብአቶች ዘርፍ የሚወጣውን የካርቦን ዳይኦክሳይድ ልቀት በግማሽ ለመቀነስ የሚያስችሉ አዳዲስ 'ግሪን ሲሚንቶ' (Green Cement) አማራጮች ተጠናክረው ቀጥለዋል። በተለይ እንደ ቮልካን አሽ እና በኢንዱስትሪ ቆሻሻዎች ላይ የተመሰረቱ የሲሚንቶ ማምረቻ ቴክኖሎጂዎች በፈረንሳይ እና ጀርመን በስፋት ወደ ሥራ እየገቡ ናቸው። ​የትላልቅ ከተሞች የከርሰ ምድር መሠረተ ልማት እና አውቶሜትድ ቦይ ማዕቀፎች በእስያ እያደጉ ባሉ መካከለኛ እና ታላላቅ ከተሞች፣ የትራፊክ መጨናነቅን እና የቧንቧ መስመር ጥገና ፈተናዎችን ለመቅረፍ ባለ ብዙ ደረጃ የከርሰ ምድር መሠረተ ልማት ኔትወርኮች እየተገነቡ ይገኛሉ። እነዚህ ፕሮጀክቶች ሙሉ በሙሉ በሮቦቲክስ እና በዲጂታል መንታ (Digital Twin) ቴክኖሎጂዎች የሚታገዙ ሲሆን፣ የከተሞችን የረጅም ጊዜ ዘላቂነት እያረጋገጡ ይገኛሉ። ​በቅድመ-ግንባታ (Prefabrication) እና ሞጁላር ህንፃዎች ላይ የሚታየው ዕድገት በአሜሪካ እና በMiddle East (መካከለኛው ምስራቅ) የሪል ስቴት ገበያ የጊዜ እና የወጪ ቆጣቢነቱን ከፍ ለማድረግ በፋብሪካ ተጠናቀው የሚገጠሙ የሞጁላር ህንፃዎች ፍላጎት ከዕለት ወደ ዕለት እየጨመረ ነው። ይህ አሰራር የግንባታ ጊዜን እስከ 40 በመቶ መቀነስ እንደቻለ የዘርፉ ጥናቶች ያመለክታሉ። ​ይህንን መረጃ ለተከታዮቻችን አሰናዳን! ለተጨማሪ ዓለም አቀፍ እና የሀገር ውስጥ የኮንስትራክሽን መረጃዎች የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። በኢትዮ ኮን የተዘጋጀ ​ኢትዮ ኮን - የኮንስትራክሽን መረጃዎ ማዕከል! 📡🏗️
2.5K ·
18 September 2026
I
ሠላም! ለረጅም ጊዜ በ97.1 FM ፕሮግራማችሁ በፅሞና ስከታተል ነበር። እውነት ለመናገር የመውረድ አዝማሚያ ስላየሁበት ትኩረት አጥቼበት ነበር። ከዛ ተነስታችሁ እዚህ ከፍታ ላይ በመድረሳችሁ መገረሜን እና ማድነቄን ያለስስት ልግለጽ፤ ከዚህም የተሻለ ትደርሳለህ ብዬም አምናለሁ። " መልካም አዲስ ዓመት! "
19 September 2026
A
#በመሬት_መንቀጥቀጥ_ጉዳይ_አትጨናነቁ_የት_አከባቢ_እንደሚከሰት_ጹሁፉን_ያንብብቡ_ሊንኩን_በመጫን_ፕሮግራሙን_ያድምጡ ከአንድ ቴሌግራም ገጽ ያነበብኩትን ላካፍላችሁ 👉የመሬት መንቀጥቀጥ (Seismic load) 🏷የመሬት መንቀጥቀጥ በአንድ የግንባታ ንድፍ (በተለይ በስትራክቸራል ዲዛይን ሥራ) ሂደት ከግምት ውስጥ የሚገባ ከዋናዎቹ ጫናዎች (loads) መካከል ነው። ይህ የመሬት መንቀጥቀጥ ማባዣ (seismic factor) ለተለየያዩ አካባቢዎች የተቀመጠ ሲሆን ማብዣ ቁጥሩ የሚወሰነው ቀድሞ በነበረው የመሬት መንቀጥቀጥ ታሪክ (Historical records) መሰረት ነው። በዚህ አግባብ በቀድሞው EBCS ምትክ የተቋቋመው በኢትዮጵያ የልኬት ኤጀንሲ (Ethiopian Standard Agency) በ2015 (እ.ኤ.አ) ለስትራክቸራል ዲዛይን ሥራ ከግምት ውስጥ እንዲገባ ባዘጋጀው የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረትን በወሰነበት CES 160 ልኬት መሰረት ከፍተኛው የመሬት መንቀጥቀጥ ማባዣ አምስት (5) እንዲሆን ያረቀቀ ሲሆን ይህ ልኬት የተሰጣቸው አካባቢዎች፦ 🏷1ኛ)፦ በአፋር ክልል፦ አፍዴራ፣ አርጎባ ልዪ፣ አሳይታ፣ አዋሽ ሸለቆ፣ ዳልፋጊ፣ ዱብቲ፣ ዱሌቻ፣ ኤሊዳር፣ ገዋኔ፣ ሀደሌላ፣ ሰመራ፣ ሰሙሮቢና ገላሎ 🏷2ኛ)፦ በአማራ ክልል፦ አንኮበር፣ አንጾኪያ ገምዛ፣ አርቱማ ፉርሲ፣ ባሶና ወራና፣ መንዝ ግሼ፣ ጅሌ ጥሙጋ፣ ቀወት፣ መንዝ ጌራ፣ መንዝ ማማ፣ ሞጃና ወደራ፣ ወይን አምባ፣ ጣርማ በር ናቸው። ⭐️በእነዚህ አካባቢዎች ዙሪያ ያሉ አካባቢዎች የሀገሪቱ ስምጥ ሸለቆ ዞኖች ስለሆኑ ከፍተኛ የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረት የሚስተዋልባቸው ናቸው። ❇️ነገር ግን በዚህ ሰሞን የሚስተዋለው የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረት በሬክታል ስኬል እስከ 5.2 የደረሰ መሆኑ ተዘግቧል። ⏺ይህ ማለት የሀገሪቱ የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረት ልኬት ከተቀመጠው ስታንዳርድ  ያለፈ ሆኖ የተመዘገበ ታሪክ ስለሆነ የስታንዳርድ (standard) ማስተካከያ ሊያስፈልገን ነው ማለት ነው። ለበለጠ እውቀት ሊንኩን በመጫን ሙሉ ፕሮግራሙን ያድምጡ። @highlight https://youtu.be/w-64RmgP-cM?si=eLMx2L_OqbzER24r
Архив по месяцам
Open in Telegram Каталог площадок Искать в ChatCrawler

A snapshot of an open public feed from the search index ChatCrawler — “Google for public Telegram”; refreshed as the venue is crawled. Times are UTC.

Public content only, official Telegram API. About · FAQ · What we do not do · Remove a page · Catalog