ChatCrawlersearch across public Telegram Open the app
A

Amhara University Students

3 567 members
D
Фотография
click to show
BREAKING NEWS #WOLDIA UNIVERSITY Congratulations to Dr. Tizazu Asefa from Veterinary Medicine for an outstanding achievement! With an exceptional 3.97 GPA and an impressive 46 A+ grades, he has earned the prestigious University Gold Medal. A testament to his dedication, brilliance and hard work.  Well done, Dr. Tizazu! Your success inspires us all. 🎓 AMHARA UNIVERSITY STUDENTS https://t.me/amharaus
Admin
በዛሬው ዕለት የምትመረቁ ተማሪዎች እንኳን ደስ አላችሁ
A
Фотография
click to show
Ĵ
Фотография
click to show
Фотография
click to show
Фотография
click to show
Фотография
click to show
Wollo University 2013 Batch Law Graduates!👨‍⚖️👩‍⚖️
Фотография
click to show
Фотография
click to show
D
ታላቁ የጨረቃ ግርዶሽ በኢትዮጵያ ሰማይ ! ዛሬ ጳጉሜን 2 ምሽት ላይ ኢትዮጵያን ጨምሮ በመላው ምስራቅ አፍሪቃ፣ ምስራቅ አውሮጳ ፣ ማዕከላዊ እስያ ፣ ምዕራባዊ ኦሽኒያ እና በከፊል ሩቅ ምስራቅ እስያ አስደናቂ የሆነ ሙሉ የጨረቃ ግርዶሽ ይታያል። ይህ ክስተት ጨረቃ በመሬት ሙሉ ጥላ ውስጥ ስታልፍ ደማቅ ቀይ ቀለም ስለምትይዝ " ቀይ ጨረቃ " (Blood Moon) በመባል ይታወቃል። በኢትዮጵያ ውስጥ እንደምንገኝበት አካባቢ የግርዶሹ አተያይ ላይ መጠነኛ ልዩነት ይኖራል። እስቲ ይህ ግርዶሽ እንዴት እንደሚከሰት እና በሀገራችን ክፍሎች ያለው ልዩነት ምን እንደሆነ በትክክለኛው መረጃ ላይ ተመስርተን እንመልከት። የጨረቃ ግርዶሽ እንዴት ይከሰታል ? የጨረቃ ግርዶሽ የሚከሰተው ፀሀይ፣ መሬት እና ጨረቃ በአንድ መስመር ላይ ሲሰለፉና መሬት በፀሀይ እና በጨረቃ መካከል ገብታ ጥላዋን ጨረቃ ላይ ስታሳርፍ ነው። የመሬት ጥላ ሁለት አይነት ነው ፦ ° የመሬት ድብዝዝ ጥላ (Penumbra) የውጪውና ደብዛዛው ሲሆን፣ ° የመሬት ጽልም ጥላ (Umbra) ደግሞ ዋናውና ጥቁሩ ጥላ ነው። ሙሉ ግርዶሽ የሚባለው ጨረቃ ሙሉ በሙሉ በጽልም ጥላ ውስጥ ስትገባ ነው። በኢትዮጵያ የግርዶሹ አተያይ ልዩነት ፦ 1. ምስራቃዊ እና መካከለኛው የኢትዮጵያ ክፍል (ግርዶሹን ሙሉ በሙሉ የሚያዩ) እነዚህ አካባቢዎች (#አዲስ_አበባን ጨምሮ) ግርዶሹ ከመጀመሪያው እስከ መጨረሻው ድረስ ያሉትን ሁሉንም ሂደቶች ያያሉ። ግርዶሹ ሲጀምር ጨረቃ ቀድማ ሰማይ ላይ ወጥታ ስለምትገኝ፣ የመጀመሪያው የብርሃን መደብዘዝ (በድብዝዝ ጥላ)፣ ወደ ጽልም ጥላ መግባቷ፣ ሙሉ በሙሉ ቀይ መሆኗ እና ከጥላ መውጣቷን በሙሉ መመልከት ይችላሉ። በዚህ ምድብ ስር የሚገኙ ከተሞች ፦ - አዲስ አበባ፣ - ደብረ ብርሃን፣ - ደሴ፣ መቐለ፣ - አዲግራት፣ - አክሱም፣ - ሰመራ፣ - ድሬዳዋ፣ - ሐረር፣ - ጅግጅጋ፣ - አዳማ፣ - አሰላ፣ - ሻሸመኔ፣ - ሀዋሳ፣ - አርባ ምንጭ፣ - ወልቂጤ፣ - ሮቤ፣ - ጎዴ፣ ሞያሌ እና ሌሎችም። 2. ምዕራባዊ የኢትዮጵያ ክፍል (የግርዶሹ የመጀመሪያ ክፍል የማይታይባቸው ቦታዎች) እንደ ጋምቤላ፣ ባህር ዳር ፣ ሚዛን ተፈሪ እና አሶሳ ያሉ የምዕራብ ኢትዮጵያ ከተሞች የግርዶሹ ዋና ዋና ክፍሎች የሆኑትን ከፊል ግርዶሹን እና ሙሉ ግርዶሹን በሙሉ ያያሉ። ልዩነቱ የሚመጣው በመጀመሪያው የድብዝዝ ግርዶሽ (Penumbral Eclipse) ወቅት ነው፦ የድብዝዝ ግርዶሹ የሚጀምረው ምሽት 12:28 ሰዓት (6:28 PM) ላይ ነው። በዚህ ሰዓት እንደ ጋምቤላ ባሉ ምዕራባዊ ከተሞች ጨረቃ ከአድማስ በታች ስለምትሆን አትታይም። በጋምቤላ ጨረቃ ከአድማስ በላይ ወጥታ መታየት የምትጀምረው ምሽት 12:39 (6:39 PM) ላይ ነው። ይህ ማለት የጋምቤላ እና ሌሎች የምዕራብ ኢትዮጵያ ተመልካቾች ጨረቃን ማየት ሲጀምሩ፣ እሷ ለ11 ደቂቃ ያህል በድብዝዝ ጥላ ውስጥ ተጉዛለች ማለት ነው። ስለዚህ፣ የሚያመልጣቸው የግርዶሹ የመጀመሪያ 11 ደቂቃ ብቻ ሲሆን፣ ይህ ክፍል ደግሞ በዓይን በቀላሉ የማይለይ የብርሃን መቀነስ ብቻ ነው። ዋናው ነጥብ በጣም አስደናቂዎቹ የግርዶሹ ክፍሎች (ከፊል እና ሙሉ ግርዶሽ) ከመጀመራቸው በፊት ጨረቃ በሰማይ ላይ በደንብ ከፍ ስለምትል፣ ከነዚህ አስደናቂ ሂደቶች አንድም አያመልጣቸውም። በዚህ ምድብ ስር የሚገኙ ከተሞች፦ - ጋምቤላ፣ - ጎንደር፣ - ባህር ዳር፣ - አሶሳ፣ - መተማ፣ - ደምቢ ዶሎ፣ - ነቀምት፣ - ጅማ፣ - ሚዛን ተፈሪ፣ - ቦንጋ፣ - ጂንካ እና ሌሎችም። የግርዶሹ የጊዜ ሰሌዳ (በአዲስ አበባ ሰዓት
D
Фотография
click to show
Фотография
click to show
Фотография
click to show
Фотография
click to show
Фотография
click to show
Фотография
click to show
አስገራሚው በጉባ ተራራ ላይ የታየው እና #የአሶሳዩኒቨርሲቲ ቴክኖሎጂ መምህራን የተሳተፉበት ድንቅ የድሮን ትርኢት ይሄንን ይመስላል https://t.me/amharaus https://t.me/amharaus https://t.me/amharaus
D
Фотография
click to show
ታሪክን የኋሊት ከዛሬ ሶስት እና አራት አመታት በፊት በአማራ ክልል በተፈጠረው የሰሜኑ ጦርነት እና የእርስ በእርስ ግጭት በክልሉ የምንማር የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ላይ  ከፍተኛ የሆነ ተስፋ መቁረጥ፣ ጭንቀት፣ ድብርት ውስጥ ያስገባው። በዚህም ምርር ያለው ተማሪ ከአስሩም ዩኒቨርሲቲ ተወካይ በማወጣጣት እና የቴሌግራም ግሩፕ በመክፈት ተማሪው ሀሳቡን ወደ አንድ አምጥቶ ለመብቱ እንዲታገል በማሰብ "አስተምሩን አስመርቁን" በሚል መፈክር ከ ebs እስከ Asham tv ብሎም Abay tv ቀጥሎም  በተለያዩ ማህበራዊ ድረገፆች እንዲሁም ጉዳዩ የሚመለከተው የትምህርት ሚኒስቴር ድረስ በመሄድ መብታችን ይከበር እድሜያችንን አትጨርሱ በሚል ከፍተኛ ንቅናቄ ሲያረግ የነበረው በመጨረሻም ትግሉ ፍሬ አፍርቶ አስተምሮ ለማስመረቅ የደረሰው። የዛን እልህ ሳይሆን አይቀርም Exit Exam ያመጣው😂 አንድነትን በተግባር አሳይቶ ታግሎ ለውጥ ያመጣው የዛ ዘመን ተማሪ መሆን መታደል ነው። የትላንት ተማሪዎች የዛሬ ሰራተኞች እንኳን ለ2018 አዲስ አመት በሰላም እና በጤና አሸጋገራችሁ መልካም በአል ይሁንላችሁ። እንዲሁም በትምህርት ላይ ላላችሁ እና ከመሰከረም ጀምሮ ወደ ጊቢ ለምትመለሱ ነባር ተማሪዎች እና አዲስ ገቢ ተማሪዎች መልካም የትምህረት ጊዜ መልካም በአል እንመኝላችኋለን!!!!
D
Фотография
click to show
Фотография
click to show
አርቲስት ነጻነት ወርቅነህ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ አዲስ አበባ፣ ጥር 8፣ 2018  አርቲስት ነጻነት ወርቅነህ ባደረበት ህመም በድንገት ከዚህ ዓለም በሞት መለየቱን ኢቢኤስ ቴሌቪዥን ገለጸ። አርቲስት ነጻነት ወርቅነህ በቴሌቪዥን ፕሮግራም አቅራቢነት፣ በተዋናይነትና በሌሎች የጥበብ ስራዎቹ በኪነ ጥበቡ ቤተሰብ ዘንድ ይታወቃል። ሁለገቡ አርቲስት ነጻነት ወርቅነህ ለበርካታ ዓመታት በኢቢኤስ ቴሌቪዥን የሚተላለፈውን የቤተሰብ ጨዋታ ፕሮግራም አዘጋጅና አቅራቢ በመሆን እያገለገለ ነበር። አርቲስት ነጻነት ወርቅነህ በፊልም እና በቴአትር ስራዎቹ እጅግ ተወዳጅ የነበረ ሲሆን፤ ሲቲ ቦይስ፣ ሳልነግራት፣ ያንቺው ሌባ 2፣ ኤፍቢአይ፣ ሚስተር ኤክስ፣ ቾምቤ እና ሌሎችም ድንቅ ብቃቱን ያሳየባቸው ፊልሞች ናቸው። ፍሬሽ ማን ከህዝብ ጋር ያስተዋወቀው የቴአትር ስራው ነው።   አርቲስት ነጻነት ወርቅነህ ባለትዳርና የ3 ልጆች አባት ነበር።
Archive by month
Open in Telegram Каталог площадок Искать в ChatCrawler

A snapshot of an open public feed from the search index ChatCrawler — “Google for public Telegram”; refreshed as the venue is crawled. Times are UTC.

Public content only, official Telegram API. About · FAQ · What we do not do · Remove a page · Catalog