🕊
† እንኳን ለካህኑ ሰማዕት አባ ኦሪ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፤ አደረሰን። †
† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ! †
† 🕊 ቅዱስ አባ ኦሪ ቀሲስ 🕊 †
† ይህ ቅዱስ አባት የዘመነ ሰማዕታት ፍሬ ነው:: በዘመኑ [በ፫ [3]ኛው መቶ ክ/ዘመን] ክርስቲያን መሆን ብቻውን ለሞት እንደሚያበቃ ወንጀል ይቆጠር ነበር:: በጊዜው ክርስቲያን ከመሆን በባሰ መንገድ እረኛ ካህን ሆኖ መገኘት በጣም ከባድ ነበር::
ከመነሻውም ያን ጊዜ ክህነት የሚሰጠው በሕዝቡና በሊቀ ጳጳሱ ምርጫ ነበር እንጂ እንደ ዘንድሮ "እኔን ሹሙኝ" ማለት ልማድ አልነበረም:: ምዕመናንም እረኛቸውን ሲመርጡ በጉቦ: በዝምድና አይደለም:: በርትቶ የሚያበረታቸውን: ለመንጋው ራሱን አሳልፎ የሚሰጠውን ይመርጣሉ እንጂ::
ያልሆነ ሰው ለክህነት ቢመረጥ አንድም ክዶ ያስክዳል: ሲቀጥልም ለሕዝቡ መሰናክል መሆኑ አይቀርም:: በጊዜው [በዘመነ ሰማዕታት] የነበሩ ካህናት የቤት ሥራቸውም ማስተማር ብቻ አልነበረም:: በድፍረት በምዕመናን ፊት አንገታቸውን ለሰይፍ መስጠት ይጠበቅባቸው ነበር እንጂ::
ይህንን በገሃድ መፈጸም ከቻሉ አበው አንዱ ደግሞ አባ ኦሪ ቀሲስ ናቸው:: ቅዱሱ ተወልደው ባደጉባት ሃገረ ስጥኑፍ [የግብፅ አውራጃ ናት] መጻሕፍትን የተማሩ: ተወዳጅ እና ደግ ሰው ነበሩ::
አባ ኦሪ ገና ከወጣትነት ቀዳሚ ግብራቸው መንኖ ጥሪት [ምናኔ] ነበር:: በንጽሕናቸው ደስ የተሰኙ ምዕመናንም "ቅስና ተሹመህ ምራን: አስተምረን::" ቢሏቸው አበው ውዳሴ ከንቱን አይፈልጉምና "አይሆንም" አሉ::
ነገሩ ፈቃደ እግዚአብሔር ነበረና አባ ኦሪ ቅስናን ተሹመው ያገለግሉ ገቡ:: ሕዝቡን በማስተማር: በመምከር: ደካማውን በማጽናት ብዙ ደክመዋል::
ከቅድስናቸው የተነሳ ቅዳሴ ሊቀድሱ ሲገቡ ጌታችን በገሃድ ይገለጥላቸው ነበር:: ሠራዊተ መላእክትም ከበው ይነጋገሯቸው ነበር::
ሥጋውን ደሙን በማቀበልም ተግተው ዘመናት አለፉ:: ቆይቶ ግን ያ በዜና ይሰሙት የነበረ መከራ [ሰማዕትነት] በደጃቸው ደረሰ:: በጊዜው ብዙ ሰው በሰማዕትነት አለፈ:: አባ ኦሪም ወደ ቤተ እግዚአብሔር ገብተው ስለ ራሳቸውና ሕዝቡ ጽናትን: ደኅንነትን ለመኑና ከቤተ ክርስቲያን ወጡ::
በቀጥታ የሔዱትም ወደ ዐውደ ስምዕ [የምሥክርነት አደባባይ] ነበር:: በመኮንኑ ፊት ቀርበው "ክርስቶስ አምላክ: ፈጣሪ: የሁሉ ጌታ ነው:: የእናንተ ጣዖት ግን ጠፊ: ረጋፊ: ወርቅ: ብር: እንጨትና ድንጋይ ነው::" ሲሉ በድፍረት ተናገሩ::
መኮንኑም ከአነጋገራቸው የተነሳ ተቆጥቶ ሥቃይን አዘዘባቸው:: ወታደሮቹ ይሆናል ያሉትን ማሰቃያ ሁሉ አባ ኦሪ ላይ ሞከሩ:: በኋላም ወደ ጨለማ እሥር ቤት ወስደው ጣሏቸው:: በእሥር ቤት ውስጥም ድውያንን ፈወሱ: ተአምራትን ሠሩ::
ይሕንን ዜና የሰሙ አሕዛብ ብዙ ድውያንን ሰብስበው መጡ:: ቅዱሱም ሁሉን በጸሎታቸው ፈወሱ:: በዚህ ምክንያትም ብዙ አሕዛብ ወደ ክርስትና መጥተዋል:: በክርስቶስ አምነውም ለክብር በቅተዋል::
ቅዱሱንም ከእሥር ቤት አውጥተው ብዙ ካሰቃዩዋቸው በኋላ በዚህች ቀን ገድለዋቸው ሰማዕትነትን አግኝተዋል:: በአክሊለ ጽድቅ ላይ አክሊለ ካህናትን: በአክሊለ ካህናትም ላይ አክሊለ ሰማዕታትን ደርበዋል::
† አምላከ ቅዱሳን በአባቶቻችን ጽናት ያጽናን:: ጸጋ በረከታቸውንም ይክፈለን::
🕊
[ † ነሐሴ ፱ [ 9 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]
፩. ቅዱስ አባ ኦሪ ቀሲስ [ሰማዕት]
፪. አባ ጲላጦስ ሊቀ ጳጳሳት
[ † ወርኀዊ በዓላት ]
፩. አባ በርሱማ ሶርያዊ [ለሶርያ መነኮሳት ሁሉ አባት]
፪. አ
††† እንኳን ለካህኑ ሰማዕት አባ ኦሪ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። †††
††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††
††† ቅዱስ አባ ኦሪ ቀሲስ †††
††† ይህ ቅዱስ አባት የዘመነ ሰማዕታት ፍሬ ነው:: በዘመኑ (በ3ኛው መቶ ክ/ዘመን) ክርስቲያን መሆን ብቻውን ለሞት እንደሚያበቃ ወንጀል ይቆጠር ነበር:: በጊዜው ክርስቲያን ከመሆን በባሰ መንገድ እረኛ ካህን ሆኖ መገኘት በጣም ከባድ ነበር::
ከመነሻውም ያን ጊዜ ክህነት የሚሰጠው በሕዝቡና በሊቀ ጳጳሱ ምርጫ ነበር እንጂ እንደ ዘንድሮ "እኔን ሹሙኝ" ማለት ልማድ አልነበረም:: ምዕመናንም እረኛቸውን ሲመርጡ በጉቦ: በዝምድና አይደለም:: በርትቶ የሚያበረታቸውን: ለመንጋው ራሱን አሳልፎ የሚሰጠውን ይመርጣሉ እንጂ::
ያልሆነ ሰው ለክህነት ቢመረጥ አንድም ክዶ ያስክዳል: ሲቀጥልም ለሕዝቡ መሰናክል መሆኑ አይቀርም:: በጊዜው (በዘመነ ሰማዕታት) የነበሩ ካህናት የቤት ሥራቸውም ማስተማር ብቻ አልነበረም:: በድፍረት በምዕመናን ፊት አንገታቸውን ለሰይፍ መስጠት ይጠበቅባቸው ነበር እንጂ::
ይህንን በገሃድ መፈጸም ከቻሉ አበው አንዱ ደግሞ አባ ኦሪ ቀሲስ ናቸው:: ቅዱሱ ተወልደው ባደጉባት ሃገረ ስጥኑፍ (የግብፅ አውራጃ ናት) መጻሕፍትን የተማሩ: ተወዳጅ እና ደግ ሰው ነበሩ::
አባ ኦሪ ገና ከወጣትነት ቀዳሚ ግብራቸው መንኖ ጥሪት (ምናኔ) ነበር:: በንጽሕናቸው ደስ የተሰኙ ምዕመናንም "ቅስና ተሹመህ ምራን: አስተምረን::" ቢሏቸው አበው ውዳሴ ከንቱን አይፈልጉምና "አይሆንም" አሉ::
ነገሩ ፈቃደ እግዚአብሔር ነበረና አባ ኦሪ ቅስናን ተሹመው ያገለግሉ ገቡ:: ሕዝቡን በማስተማር: በመምከር: ደካማውን በማጽናት ብዙ ደክመዋል::
ከቅድስናቸው የተነሳ ቅዳሴ ሊቀድሱ ሲገቡ ጌታችን በገሃድ ይገለጥላቸው ነበር:: ሠራዊተ መላእክትም ከበው ይነጋገሯቸው ነበር::
ሥጋውን ደሙን በማቀበልም ተግተው ዘመናት አለፉ:: ቆይቶ ግን ያ በዜና ይሰሙት የነበረ መከራ (ሰማዕትነት) በደጃቸው ደረሰ:: በጊዜው ብዙ ሰው በሰማዕትነት አለፈ:: አባ ኦሪም ወደ ቤተ እግዚአብሔር ገብተው ስለ ራሳቸውና ሕዝቡ ጽናትን: ደኅንነትን ለመኑና ከቤተ ክርስቲያን ወጡ::
በቀጥታ የሔዱትም ወደ ዐውደ ስምዕ (የምሥክርነት አደባባይ) ነበር:: በመኮንኑ ፊት ቀርበው "ክርስቶስ አምላክ: ፈጣሪ: የሁሉ ጌታ ነው:: የእናንተ ጣዖት ግን ጠፊ: ረጋፊ: ወርቅ: ብር: እንጨትና ድንጋይ ነው::" ሲሉ በድፍረት ተናገሩ::
መኮንኑም ከአነጋገራቸው የተነሳ ተቆጥቶ ሥቃይን አዘዘባቸው:: ወታደሮቹ ይሆናል ያሉትን ማሰቃያ ሁሉ አባ ኦሪ ላይ ሞከሩ:: በኋላም ወደ ጨለማ እሥር ቤት ወስደው ጣሏቸው:: በእሥር ቤት ውስጥም ድውያንን ፈወሱ: ተአምራትን ሠሩ::
ይሕንን ዜና የሰሙ አሕዛብ ብዙ ድውያንን ሰብስበው መጡ:: ቅዱሱም ሁሉን በጸሎታቸው ፈወሱ:: በዚህ ምክንያትም ብዙ አሕዛብ ወደ ክርስትና መጥተዋል:: በክርስቶስ አምነውም ለክብር በቅተዋል::
ቅዱሱንም ከእሥር ቤት አውጥተው ብዙ ካሰቃዩዋቸው በኋላ በዚህች ቀን ገድለዋቸው ሰማዕትነትን አግኝተዋል:: በአክሊለ ጽድቅ ላይ አክሊለ ካህናትን: በአክሊለ ካህናትም ላይ አክሊለ ሰማዕታትን ደርበዋል::
††† አምላከ ቅዱሳን በአባቶቻችን ጽናት ያጽናን:: ጸጋ በረከታቸውንም ይክፈለን::
††† ነሐሴ 9 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ አባ ኦሪ ቀሲስ (ሰማዕት)
2.አባ ጲላጦስ ሊቀ ጳጳሳት
††† ወርኀዊ በዓላት
1.አባ በርሱማ ሶርያዊ (ለሶርያ መነኮሳት ሁሉ አባት)
2.አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ (ኢትዮጵያዊ)
3
197 · ፍሬ የጠፋብኝ ብላቴና††† እንኳን ለካህኑ ሰማዕት አባ ኦሪ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። †††
††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††
††† ቅዱስ አባ ኦሪ ቀሲስ †††
††† ይህ ቅዱስ አባት የዘመነ ሰማዕታት ፍሬ ነው:: በዘመኑ (በ3ኛው መቶ ክ/ዘመን) ክርስቲያን መሆን ብቻውን ለሞት እንደሚያበቃ ወንጀል ይቆጠር ነበር:: በጊዜው ክርስቲያን ከመሆን በባሰ መንገድ እረኛ ካህን ሆኖ መገኘት በጣም ከባድ ነበር::
ከመነሻውም ያን ጊ 203 ·
Фотография
click to show
click to show
Фотография
click to show
click to show
Фотография
click to show
click to show
Фотография
click to show
click to show
የፍልሰታ ጾም እኩሌታ አልፈናል 🙏💙
እስከዚህ ያደረሰንን እግዚአብሔርን የተመሰገነ ይሁን 🙏
ጾም ማለት ምግብን ብቻ መተው አይደለም፤
ልባችንን ከኃጢአት ማራቅ፣
ይቅር ማለት፣ መጸለይ፣ ለችግረኛ መርዳት
እና ወደ እግዚአብሔር መቅረብ ንስሐ መግባት ነው...
እስከ ፍጻሜውም በጽናት እንቀጥል...
እመቤታችን በቃልኪዳኗ ትጠብቅን
መልካም ጾም! 🙏
@Zemari_Biniyam
Join and share ➵ @elul_zema
145 · Фотография
click to show
click to show
የፍልሰታ ጾም እኩሌታ አልፈናል 🙏💙
እስከዚህ ያደረሰንን እግዚአብሔርን የተመሰገነ ይሁን 🙏
ጾም ማለት ምግብን ብቻ መተው አይደለም፤
ልባችንን ከኃጢአት ማራቅ፣
ይቅር ማለት፣ መጸለይ፣ ለችግረኛ መርዳት
እና ወደ እግዚአብሔር መቅረብ ንስሐ መግባት ነው...
እስከ ፍጻሜውም በጽናት እንቀጥል...
እመቤታችን በቃልኪዳኗ ትጠብቅን
መልካም ጾም! 🙏
@Zemari_Biniyam
Join and share ➵ @elul_zema
145 · 🕊
† እንኳን ለታላቁ ጻድቅና ገዳማዊ አባ ዓቢየ እግዚእ ዓመታዊ የተአምር በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፤ አደረሰን። †
† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ! †
† 🕊 ጻድቅና ገዳማዊ አባ ዓቢየ እግዚእ 🕊 †
† አባ ዓቢየ እግዚእ የተወለዱት በ፲፬ [14]ኛው መቶ ክ/ዘመን ትግራይ ተንቤን [መረታ] ውስጥ ነው:: የተባረኩ ወላጆቻቸው ያፍቅረነ እግዚእ እና ጽርሐ ቅድሳት ይባላሉ:: አጥምቀው "ዓቢየ እግዚእ" ሲሉ ስም ያወጡላቸው የወቅቱ ጳጳስ ሰላማ መተርጉመ መጻሕፍት ናቸው:: ትርጉሙም 'በጌታ ዘንድ ታላቅ ሰው' ማለት ነው::
ዓቢየ እግዚእ በሕፃንነታቸው ሌሊት ሌሊት ባሕር ውስጥ ሰጥመው ሲጸልዩ አድረው ቀን ቀን እየተማሩ ብሉይ ከሐዲስ ጠነቀቁ:: ገና በወጣትነታቸው ወደ ታላቁ መነኮስ አቡነ መድኃኒነ እግዚእ [ደብረ በንኮል] ሔደው መንኩሰዋል::
በገዳሙ በጾም: በጸሎትና በስግደት ተወስነው ከኖሩ በኋላ ወደ ዋልድባ ሔደው የተሰወረች ቤተ ክርስቲያን አግኝተዋል:: በጊዜው በአርባ ቀን አንዲት ቅጠል ብቻ ለቁመተ ሥጋ ይበሉ ነበር::
ከዚያም ወደ ሃገራቸው ተንቤን ተመልሰው ዛሬም ድረስ ድንቅ ሆኖ የሚታየውን ገዳም መሥርተው ብዙ መናንያንን አፍርተዋል:: ዓቢየ እግዚእ ገዳማዊና ጻድቅ ብቻ ሳይሆን ሐዋርያዊ አባትም ነበሩ:: ከትግራይ እስከ ደንቢያ ደግሞ ሃገረ ስብከታቸው ነው::
አንድ ጊዜ ደቀ መዛሙርትን አስከትለው ለስብከት ሲንቀሳቀሱ ተከዜ ወንዝ አካባቢ ደረሱ:: ቀኑ ነሐሴ ፲ [10] ነውና ተከዜ እስከ ገደፉ ሞልቶ ለሦስት ቀናት ባለመጉደሉ ከአንድ ሺ በላይ ሰዎች ሲያለቅሱ ደረሱ:: ጻድቁ በአካባቢው የነበሩት ኢ-አማንያን [አሕዛብ] ቢሆኑም ራርተዋልና "አምላከ ሙሴ" ብለው ጸልየው ወደ ጥልቁ ውስጥ ገቡ::
ቅዱስ ሚካኤል አብሯቸው ነበርና ተከዜ ግራና ቀኝ ተከፍሎ መሃሉ የብስ ሆነ:: ይሕን ድንቅ ያዩ ከዘጠኝ መቶ አርባ በላይ አሕዛብም አምነው በጻድቁ እጅ ተጠምቀዋል:: ይሕም ዘወትር ነሐሴ ፲ [10] ቀን በቤተ ክርስቲያናቸው [ጐንደር] ይከበራል::
ከዚያም እያስተማሩ ጐንደር ደረሱ:: ያኔ ጐንደር በቀሃና አንገረብ ወንዞች የታጠረች አንዲት መንደር ነበረች:: ጻድቁ ቀን ቀን እየሰበኩ ማታ ዛሬ ቤተ ክርስቲያናቸው የታነጸበት ሥፍራ ላይ ሲጸልዩ ያድሩ ነበር::
በዚያ ዘመን ጐንደር ውስጥ ጅብ: እባብና መሠል አራዊት ገብተው ሕዝቡን ጨረሱት:: ይሕንን የተመለከቱት አባ ዓቢየ እግዚእ ወደ እግዚአብሔር አለቀሱ:: በፍጹም ልባቸውም ስለ ሕዝቡ ለመኑ::
የለመኑትን የማይነሳ ጌታ ወደ ጻድቁ ቀርቦ "በስምሕ የተማጸኑ: በቃል ኪዳንህ ያመኑ: በምድር አራዊት አይሠለጥኑባቸውም:: በሰማይም እሳትን አያዩም:: ጐንደርንም አራዊት ገብተው ሰውን አይጐዱም::" ብሏቸው አርጓል::
ጻድቁም የወንጌል አገልግሎታቸውን ፈጽመው ወደ ገዳማቸው ተንቤን ተመልሰዋል:: ይሔው እኛ ምን ብንከፋ: ጻድቁንም ብንረሳቸው እግዚአብሔር ግን ዛሬም በጻድቁ ምልጃ ከተማዋን ጠብቆ ይኖራል:: ነገን ደግሞ እርሱ ያውቃል:: ዛሬ ቤተ ክርስቲያኑ የታነጸበት ቦታ [ጎንደር ቀበሌ ፱ [09] ኪዳነ ምሕረት] ጻድቁ የጸለዩበት ቦታ ነው:: እንኳን በወርኀዊ በዓላቸው [በ፲፱ [19] ይቅርና በዓመታዊ በዓላቸው [ግንቦት ፲፱ [19], ነሐሴ ፲ [10] እንኳ ለንግስ የሚመጣው ሰው ቁጥር ያስተዛዝባል::
አባ ዓቢየ እግዚእ በገዳማቸው ተንቤን ለብዙ ዘመናት በቅድስና ኑረው: ሦስት ሙታንን አስነስተው: ብዙ ድውያንን ፈውሰው: ብሔረ ብጹዓንን ጎብኝተው: የድኅነት ቃል ኪዳንም ተቀብለው: በመቶ አርባ ዓመታቸው ግንቦት ፲፱ [19] ቀን አርፈዋል:: የጻድቁ ክብር ለ
✨ድንግል ማርያም ወላዲተ አምላክ [Theotokos ፧ Θεοτόκος]
ዛሬ ቅዳሴ ላይ የተነበበው የወንጌል ክፍል “ ኤልሳቤጥም የማርያምን ሰላምታ በሰማች ጊዜ ፅንሱ በማኅፀንዋ ውስጥ ዘለለ፤ በኤልሳቤጥም መንፈስ ቅዱስ ሞላባት ፥
በታላቅ ድምፅም ጮኻ እንዲህ አለች፦ አንቺ ከሴቶች መካከል የተባረክሽ ነሽ፥ የማኅፀንሽም ፍሬ የተባረከ ነው።🥺” - ሉቃስ1:39-46
አንድ ሰው ድንግል ማርያምን የጌታ እናት [የአምላክ እናት] ለማለት በ መንፈስቅዱስ መሞላት አለበት። ኢየሱስን ጌታ ለማለት ግዴታ አምላክ በስጋ ከቅድስት ድንግል ማርያም ተወልዷል ብሎ ማመን አለበትና።
ቅድስት ኤልሳቤጥ ምንም እንኳ “በእግዚአብሔር ፊት ጻድቅ” እንደነበረች ይኸው ወንጌል ቢናገርም.. እግዚአብሔርም ታላቅ ተአምርን ቢያደርግላትም.. እመቤታችን ወደሷ ስትመጣ ግን “የጌታዬ እናት ወደ እኔ ትመጣ ዘንድ እንዴት ይሆንልኛል?” አለች.. የእመቤታችን ክብር ከእርሷ በጣም በእጅጉ ይበልጣልና።
እመቤታችን ከኤልሳቤጥ ብቻ ሳይሆን ከፍጥረት ሁሉ ትበልጣለች..
ጽንዕት በድንግልና ሥርጉት በቅድስና እመቤታችን ሆይ ልጅሽ ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሳን ለምኚልን፡፡ አእምሮውን ጥበቡን በልቡናችን ሳይብን አሳድሪብን፡፡ አሜን!
መልካም የጌታ ቀን (ሰንበት! )
@YilikalOrthodox
326 · Ссылка
click to show
click to show
በዚህ በሱባኤ ወቅት ሊደመጥ የሚጠባው ትምርት እግዚአብሔር መልስ የሚመልስባቸው መይገዶቸ
https://youtu.be/JdUOKEKZgZM?si=sHG-FnZtznkxNuDL
ዛሬ ጠዋት ቅዳሴ ላይ የተነበበው ወንጌል :
ሉቃስ 1፥39–47
39 ማርያምም በዚያ ወራት ተነሥታ ወደ ተራራማው አገር ወደ ይሁዳ ከተማ ፈጥና ወጣች፥
40 ወደ ዘካርያስም ቤት ገብታ ኤልሳቤጥን ተሳለመቻት።
.
.
.
.
39 ማርያምም በዚያ ወራት ተነሥታ ወደ ተራራማው አገር ወደ ይሁዳ ከተማ ፈጥና ወጣች፥
40 ወደ ዘካርያስም ቤት ገብታ ኤልሳቤጥን ተሳለመቻት።
47 ነፍሴ ጌታን ታከብረዋለች፥ መንፈሴም በአምላኬ በመድኃኒቴ ሐሴት ታደርጋለች፤
48 የባሪያይቱን ውርደት ተመልክቶአልና፡— እነሆም፥ ከዛሬ ጀምሮ ትውልድ ሁሉ ብፅዕት ይሉኛል፤
ማርያም ከመልአኩ የተቀበለችውን ታላቅ የምስራች ከሰማች በኋላ ወደ ኤልሳቤጥ በፍጥነት ሄደች....አናታችን ማርያም የራሷን ክብር ሳትፈልግ ወደ እግዚአብሔር ክብር አመለከተች ትህትናን አስተማረች
❤️ “ነፍሴ ጌታን ታከብራለች፤ መንፈሴም በመድኃኒቴ በእግዚአብሔር ደስ ይለዋል።”
ይህ ለእኛም ታላቅ ትምህርት ነው። እግዚአብሔር ሲባርከን፣ “እኔ አደረግሁት” ከማለት ይልቅ “እግዚአብሔር አደረገልኝ” ማለትን እንማር።
መልካም ሰንበት ❤️
@Zemari_Biniyam
Join and share ➵ @elul_zema
59 ·