“ተስፋ ማድርግ”
“Keeping Hope Alive”
ተስፋ የሚያስፈልገው ተስፋ ለማድረግ ነባራዊ ሁኔታው ባስቸገረ ዘመንና ስፍራ ነው፡፡
ተስፋ በድቅድቅ ጨለማ የንጋት ብርሃንን ማለም ነው፤
ተስፋ በጨፍጋጋ ደመና የፀሐይ ብልጭታን መጠበቅ ነው፤
ተስፋ በተዘጋ ዋሻ ውስጥ ሆኖ የመውጫ ጭላንጭል አለው ብሎ መትጋት ነው፤
ተስፋ ብዙዎች ከዳገቱ ሲቀሩ እችላለሁ ብሎ ጉዞን መቀጠል ነው፡፡
ተስፋ የትጋትና የእምነት ውጤት ነው!
በመጨረሻም ሁሉም መልካም ይሆናል ብሎ ማመን ነው፡፡ መልካም ካልሆነ ህንዶች እንደሚሉት መጨረሻው ገና ነው ማለት ነው ብሎ መበርታት ነው!
አለማየው ዋሴ
51 ·