ChatCrawlersearch across public Telegram Open the app
ግ

ግዜ እና ትንፋሹ💡🖌

сообщение · 2026-07-07 04:35 UTC
I
ሀብትና ስልጣን በሰው ልጅ ህሊና ላይ የሚያሳድሩት ተፅዕኖ በታሪክም ሆነ በስነ-ልቦና እጅግ አነጋጋሪ ከሆኑ ጉዳዮች መካከል አንዱ ነው። ሰው በሌለውና አቅም ባጣበት ወቅት ለፈጣሪው ቅርብ፣ ለሰው ልጅም አዛኝና ሩሩህ ሆኖ መኖር የተለመደ ነው። ሆኖም ግን የቆመበት ምድር ተቀይሮ የቁሳቁስና የገንዘብ አቅም ሲያገኝ፣ ፈጣሪውን የመርሳትና ምስኪኑን የማንኳሰስ አዝማሚያ በስፋት ይስተዋላል። ይህ ለውጥ የሚመነጨው በሀብት ምክንያት ከሚፈጠር የ"እኔነት" እና የ"ሉዓላዊነት" የሃሰት ስሜት (Illusion of Self Sufficiency) ነው። ገንዘብ ጊዜያዊ የደህንነት ጋሻ ስለሚሆንለት፣ ሰውየው ሁሉንም ነገር ያሳካው በገዛ ጥበቡና ጉልበቱ እንደሆነ ማመን ይጀምራል። በዚህም ምክንያት በችግር ጊዜ ይማጸነው የነበረውን ፈጣሪ ከመዘንጋት አልፎ፣ እጣ ፈንታ ያልቀናቸውን ምስኪኖችን እንደ ሰነፍና አቅመ-ቢስ አድርጎ በመመልከት ይጨቁናቸዋል። ይህ የሰው ልጅ የተዛባ ስነ-ልቦና እና የባለጉልቤነት ትዕቢት በኪነ-ጥበብ ውስጥም ትልቅ ትኩረት ተሰጥቶት እናገኘዋለን ድምጻዊ ቴዲ አፍሮ በሙዚቃው "ማርኮ መማር ነበር የጀግና ሞገሱ" በማለት ያስቀመጠው ስንኝ የዚህን የባለጉልቤነት ልክና የእውነተኛ ጀግንነትን ምንነት ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ማሳያ ነው። እውነተኛ ጥንካሬና ጀግንነት የሚለካው ደካማን በማንበርከክ ወይም ምስኪኑ ላይ አቅምን በማሳየት ሳይሆን፣ የመጨቆንና የማጥፋት ሙሉ ጉልበት እያለህ "የምህረትና የማስተማር" ምርጫን ስትከተል ነው። አቅምን ተገን አድርጎ ምስኪኑን መርገጥና መብቱን መንጠቅ የውስጥ ስብራትንና የሞራል ዝቅጠትን የሚያመለክት የፈሪነት ተግባር እንጂ የጀግንነት መገለጫ ሊሆን አይችልም። የቁሳቁስ መበልጸግ የውስጥ ማንነትንና ህሊናን እንዲበክል መፍቀድ ታላቅ ውድቀትን ይወልዳል። ታሪክ ደጋግሞ እንዳረጋገጠው፣ አቅም በሌለው ምስኪን ላይ የሚገተር ባለጉልቤ የቆመበት መሰረት አሸዋ በመሆኑ ውድቀቱ የከፋ ይሆናል። የሰው ልጅ እውነተኛ ሞገስና ልዕልና የሚለካው ባገኘው ሀብትና ስልጣን ልክ ለፈጣሪው የሚያሳየው ትህትና እና ለደካሞች የሚዘረጋው የርህራሄ እጅ ሲኖር ብቻ ነው። "ቻው ሰኔ " ፍትህ ከጥግ እስከ ጥግ ይጣራል! መልካም ግዜ
45 ·

Вся лента · оригинал в Telegram

Open in Telegram Каталог площадок Искать в ChatCrawler

A snapshot of an open public feed from the search index ChatCrawler — “Google for public Telegram”; refreshed as the venue is crawled. Times are UTC.

Public content only, official Telegram API. About · FAQ · What we do not do · Remove a page · Catalog