Ссылка
click to show
click to show
https://t.me/litjournalism/129379
ሐምሌን በማለዳ
የሩሲያው ታላቅ ፈላስፋ ፊዮዶር ዶስቶየቭስኪ “ከሁሉ የከፋው የባርነት አይነት በሌሎች የመረዳት ጉጉት ነው” ሲል ብዙዎቻችን እንደ በጎ ምግባር የምናየውን “ተረዱኝ” ባይነትን ወደ ረቂቅ የስነ-ልቦና ወጥመድነት ይቀይረዋል። በአሁኑ ዘመን በተለይም ማህበራዊ ሚዲያ እና የሰዎች ይሁንታ (validation) ህይወታችንን በገዙበት አለም ይህ አባባል ከመቼውም ጊዜ በላይ ትልቅ ትርጉም አለው።
አንድ ሰው “እባካችሁ እኔንና ሃሳቤን ተረዱልኝ” ብሎ ሲማጸን በተዘዋዋሪ ለሰዎቹ የሚሰጣቸው መልዕክት፡ “የእኔ የመረጋጋት የመደሰትና የራሴን ዋጋ የመወሰን ስልጣን በእናንተ እጅ ነው” የሚል ነው። ይህ ደግሞ በራስህ ላይ የምታውጀው ትልቁ የውስጥ መፈንቅለ-መንግስት ነው። ሰዎች ካልተረዱህ ትበሳጫለህ፣ ካጣጣሉህ ትከፋለህ፣ ካደነቁህ ትቦርቃለህ። በዚህ ጊዜ አንተ የራስህ ህይወት መሪ ሳትሆን የሰዎች ስሜትና አስተያየት እንደፈለገ የሚነዳህ “የስሜት ተላላኪ” (emotional puppet) ትሆናለህ።
በታሪክ ውስጥ ትልልቅ ለውጥ ያመጡ ሳይንቲስቶች፣ ጸሐፊዎች፣ መሪዎችና የጥበብ ሰዎች በዘመናቸው በነበሩ ሰዎች አልተረዱም። እንዲያውም በአብዛኛው እንደ እብድ ነበር የሚታዩት።
ልዩነቱ እዚህ ላይ ነው ያልበሰለው ሰው ሳይረዱት ሲቀሩ “እባካችሁ ተረዱኝ” እያለ ይማጸናል፤ እውነተኛው ጀግና ግን አለመረዳቱን እንደ ልዩነቱ መገለጫ (uniqueness) ይቀበለዋል።
አለም የአንተን ጥልቀት ማየት ስላልቻለች ብቻ የአንተን ወርቅነት ወደ ናስ ልትቀይረው አትችልም። ስለዚህ አለመረዳትን እንደ ውድቀት ሳይሆን ከሰፊው ህዝብ የተለየ መንገድ እየተጓዝክ መሆንህን ማረጋገጫ አድርጎ መውሰድ የነጻነት መጀመሪያ ነው።
በሰዎች መካከል በምትኖርበት ማህበራዊም ሆነ ሙያዊ ህይወት ውስጥ እያንዳንዱን እርምጃህንና ውስጣዊ አላማህን ለሰዎች ለማስረዳት መሞከር ጉልበትን በከንቱ ማባከን ነው።
ቁም ነገሩ አለም ሁሉ አጨበጨበልህ ወይም ተረዳህ ላይ አይደለም። እውነተኛው ነጻነት የሚጀምረው ፈጣሪህ ያወቀህን ያህል ብቻ በቂ እንደሆነ ተረድተህ የሰዎችን የይሁንታ ሰንሰለት በጥሰህ በራስህ እውነት ላይ ስትቆም ነው። አለም ባይረዳህ እንኳ አንተ ራስህን እና የቆምክበትን አላማ በሚገባ ካወቅኸው አንተ ቀድሞውኑ ነጻ ወጥተሃል።
እውነተኛ ነጻነት የሚጀምረው ሰው በራሱ ማንነትና በፈጣሪው ፊት ሙሉ በሙሉ ሲረካና ሲረጋጋ ነው።
ሐምሌያችን እንኳን ደህና መጣሽ!
መልካም ግዜ!
55 ·