Фотография
click to show
click to show
ያማኛል አሉ ያዝናብ፣
ካገር ከቀየው በሃሳብ።
አሁን ከሰሰኝ ከንጉሡ በር
የወረደብኝ እራሱ ነበር፣
ዘሬን ስዘራ አበላሽቶብኝ ጎርፍ ሆኖ መጥቶ፣
ሲደብቅብኝ ሰብሌን ሁሉ እንደጉልቶ።
ስንቱን ልናገር ስንቱን ስንቱን፣
ያደረገብኝን የግፍ ግፉን።
እንዳልጠየቅሁት ተው ዝናቡን፣
ይኸው አከለኝ እጥፍጥፉን።
ምን ይደረጋል ንጉሥ ካለማ፣
መቀበል አይደል ምንም ቢመጣ።
አንዳችም ነገር ሳይሰማ ከቶ፣
ንጉሡም አለ እሱኑ ሰምቶ።
ተንግዲህ ወዲያ ላትገናኙ
አንተም በረሀ እሱም ለምለሙ
እንዲህ ባለበት በዚያው ቅፅበቱ
በሀገሬው ላይ ዝናቡን አጡ
አሁን ንጉሱ ግብር ፈልጎ ካገር ከምሱ
አስገቡ ይላል ያገሬውን ህዝብ ከነፈረሱ
ያገሬውም ህዝብ ስለበዛበት ድርቅ እና ክሱ
ንጉስ ማን ነበር ወደሚለው ሀቅ ተመላለሱ
ንጉስ ህዝብ ነው
ህዝብም ንጉስ ነው
ወደሚለው ሀቅ ተደራረሱ
ልክ ሲደርሱ ያንኑ ዝናብ ካለበት ስበው ልክ እንዳመሉ
አነጋገሩት ሁኖ እዲዘንብ ባገሬው ልማድ ላገሬው ሲሉ።
ግዜን ለማስታወስ የተሞነጨረ'
ተፃፈ ሐምሌ-2-2018
49 ·