ChatCrawlersearch across public Telegram Open the app
ግ

ግዜ እና ትንፋሹ💡🖌

сообщение · 2026-09-20 15:04 UTC
I
የምድር ጌጥ ኢትዮጵያ፡  የትውልድ ቅብብል እና የታሪክ ውበት በሐመረ ብርሃን የቤተክርስቲያን ተስፋዎችና የእግዚአብሔር ድንቅ ስጦታዎች የሆኑት ህፃናት የአባቶቻቸውን አሰረ ፍኖት፣ የሀገራቸውን ገናና ታሪክ እና የማንነታቸውን መሰረት የሚጨብጡበት ልዩ አገራዊና መንፈሳዊ ኩነት።  ሐመረ ብርሃን ያዘጋጀው "የምድር ጌጥ ኢትዮጵያ" የተሰኘው ታላቅ ዓውደ ርዕይ ታሪክን ከነባህሉ፣ እምነትን ከነቅርሱ ለወጣቱ ትውልድ በግልፅ የሚያስተላልፍ ድልድይ ሆኖ ቀርቦ ነበር። በሆላንድ ፓርክ የተካሄደዉ  ዓውደ ርዕይ ልጆች ብቻ ሳይሆን ለሌሎችም የዕድሜ ክልሎች የኢትዮጵያን ድንቅ ማንነትና የታሪክ ሰበዝ በአካል ተገኝተው ያዩበት፣ የተማሩበትና የአባቶቻቸውን አደራ የተረከቡበት ልዩ አጋጣሚ እንደነበር የብዙዎች ምስክርነት ነው። በዕለቱ በሌላ መድረክ የሥራ ባልደረባችን እንዲሁም የዓውደ ርዕዩ አስጎብኚ ከነበሩት የህዝብ ግኑኝነት ክፍል ሙያዊ ማብራሪያ ከመግቢያው ጀምሮ እስከ ማጠቃለያው ድረስ የተመለከትናቸው ሁነቶች ልብን የሚመስጡና ከህሊና የማይጠፉ ነበሩ። በዓውደ ርዕዩ መግቢያ ላይ የሚገኘው ረጅም ቢልቦርድ ታሪክን ከቅርብ ጊዜ ሁነቶች ጀምሮ ወደ ኋላ ወደ ጥንቱ በመቁጠር ህፃናትና ወጣቶች ከሚያውቁትና ከቅርቡ ዘመን ተነስተው ደረጃ በደረጃ ወደ ጥንታዊውና ገናናው የአባቶቻቸው ታሪክ በጥበብ እንዲጓዙና የታሪኩን ሰበዝ በቀላሉ እንዲረዱ ለማስቻል የታለመ ይመስላል። ከመግቢያው በመቀጠል ንግሥተ ሳባ ታቦተ ጽዮንን በጥበብ ይዛ ስታመጣ ቀይ ባህር እንደተከፈለላቸው የሚዘክረው ማለፊያ ግሩም እና አዲስ መረጃ ሰጪ ሁኖ ያገኘውበት፣ የባኮስ ሰረገላ፣ አክሱም ሀውልት፣ቅዱሳት መጻሕፍት የተሳቱ ቅዱሳን አምሳለ ዋሻዎችና ታሪክ ፣ አባቶቻችን በሰም ቅርፅ በማውጣት ልዩ ልዩ የብረት ቅርፆችን ይሰሩ እንደነበርና ከበሬና ፍየል ቆዳ ብራና ፍቀው መጻሕፍትን በማዘጋጀት ያሳዩት የዕደ-ጥበብና የቴክኖሎጂ እውቀት እና የአምሳለ ላሊበላ ሕንፃ ጥበብ ፣የቅዱስ ያሬድ የዜማ ሀብት በተጨማሪም የነገረ-መለኮትና የድርሰት አባታችን አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ አሰር ልብን የሚመስጡ ነበሩ። ታድያ ይህ ሁሉ የታሪክ ነገራ ብቻ ሳይሆን ምን እንደሚመስሉም በንድፍ ደረጃ መቀመጣቸው ለጎብኚው በአካል ቦታው ላይ የተከሰተ ያህል ድባብን ያላብሳል። በጉብኝቱ ማጠቃለያና መውጫ አካባቢ ደግሞ ቤተ ክርስቲያኗ በየዘመናቱ ያለፈችበትንና ይደርስባት የነበረውን መከራና ፈተና እንዲሁም የጽናቷን ታሪክ የሚያሳይ ቦታ መኖሩ የጉብኝቱን መንፈሳዊና ታሪካዊ ሚዛን ሙሉ አድርጎታል። እንዲህ ያሉ ጉዳዮች ይበል የሚያስብሉ እና በተለይ አሁን እንዳለንበት ዘመን ከቦታ ቦታ ተዘዋዎሮ ጥንታዊ ቦታዎችን ለመሳለም አስቸጋሪ በሆነበት ሰዓት አንድ ቦታ ላይ ሰዉን ስለቤተክርስቲያኗ ከፍተኛ እውቀት እሚያስጨብጡ ስለሆኑ በርቱልን እንላለን! https://t.me/beensurvival/400
13 ·

Вся лента · оригинал в Telegram

Open in Telegram Каталог площадок Искать в ChatCrawler

A snapshot of an open public feed from the search index ChatCrawler — “Google for public Telegram”; refreshed as the venue is crawled. Times are UTC.

Public content only, official Telegram API. About · FAQ · What we do not do · Remove a page · Catalog