13 August 2026
27 August 2026
የግብርና ቤተሠብ እንደምን አላችሁ፣የዘንድሮ የቡና ምርታማነት የተሻለ መሆኑን የመሥክ ምልከታም ሆነ የቡና ትመና ውጤት ያሳያል።የቡና ምርቱም የዘንድሮ የአየር ንብረት የተሻለና የተስማማ በመሆኑ በጊዜ ምርቱ ወደገበያ እየገባ ይገኛል፣በተለይ ቆላማ አከባቢወች አዲሎ ዙዙሪያና ሀደሮጡንጦ ዙሪያ በብዛት እየገባ ይገኛል።የወረዳውን የቡና ግብረ ኃይል በማንቀሳቀስ ወደገበያወች በመጎብኙትና ባለሙያ በማሰማራት አገራዊ የቡና ዋጋ በተጠቆመው መሠረት ከብክነት በመከላከል የእሸት ቡና ግዢ መረጃ እየተያዘ አንዲፈጸምና ለተዘጋጁ ለማጠቢያ ኢንዱስትሪወች ቅዲሚያ እንዲሰጥ ና ጥብቅ ክትትል እንዲደረግ አጥብቀን እናሳውቃለን።
31 August 2026
3 September 2026
4 September 2026
5 September 2026
7 September 2026
12 September 2026
ቤተሰብ እንኳን ለ2019 በሰላም፣በጤና አሸጋገረን፣ዓመቱ የሰላም፣የጤና‹የብልጽግናና የስኬት ዓመት ይሁንልን፤
የመዋቅራችን አመራርና ባለሙያወች በለፈዉ ዓመት ጳጉሜ 2/2018 የቡና ግብረ ኃይል መድረክ የዞኑን አድረገን ስናበቃ የየመዋቅረችሁን የቡና ግብረኃይል መድረክ ዓመቱ ሳይጠናቀቅ እንዲንጨርስ መግባባታችን ይታወቃል፡፡በመረሃ ግብሩ መሰረት ባለሀብቶችንና የሚመለከተዉን አካል በመጋበዝ ተገቢ ትኩረት በመስጣት አድረጎ ያጠናቀቀዉ ቀዲዳ ጋሜላ ወረዳ ብቻ ነዉ፡፡ መድረኩን ተከትሎ የግብረኃይል አባላትንና ባለሙያወችን በመመደብ የገበያ ህገወጥነትን፣የአርንጓዴ ቡና ግብይትንና ያልተገበ የዋጋ ሺሚያን የመቆጣጠር ስራ በመስራቱ ህጋዊነት ሰፍኗል፡፡ሌሎችም ቡና ፖቴንሻል የሆናችሁ አከባቢወች የእሸት ቡና ግብይትና የአርጓዴ ቡና ግብይት ከስርዓት ዉጪ ሳይሆን የግብረ ኃይል መድረክ እንዲታደርጉና የግብይት ማዕከላትን ከከተማ መዋቅር ጋር በመናበብ አስጠግናችሁ አገልግሎቱን የተሳለጠ እንዲታደርጉ አበክረን እንጠይቀለን፡፡ መልካም አዲስ ዓመት