የዩኒቨርሲቲ ምደባ
የትምህርት ሚኒስቴር በ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች የመንግሥት ዩኒቨርሲቲ ምደባ ውጤትን ይፋ አድርጓል።
📌 የምደባው ዋና መስፈርቶች
• የተማሪው አጠቃላይ ውጤትና የዩኒቨርሲቲ ምርጫ
• የዩኒቨርሲቲዎች የቅበላ አቅም
• የክልል፣ ዞን፣ ወረዳና ትምህርት ቤት ስርጭት
• የፆታ ሚዛን
🌍 የክልል ስርጭት
➡️ 70% ተማሪዎች ከተወለዱበት/ከተማሩበት ክልል ወይም ዞን ውጭ ባሉ ዩኒቨርሲቲዎች
➡️ 30% ተማሪዎች በራሳቸው ክልል ወይም ዞን ውስጥ ባሉ ዩኒቨርሲቲዎች እንዲመደቡ ታሳቢ ተደርጓል።
⭐️ 500 እና ከዚያ በላይ ያስመዘገቡ ተማሪዎች
ከ600 ውስጥ 500 እና ከዚያ በላይ ያስመዘገቡ ተማሪዎች ለውጤታቸው ልዩ ታሳቢነት ተደርጎላቸው፣ በመጀመሪያ ምርጫቸው ባስቀመጡት ዩኒቨርሲቲ እንዲመደቡ ተደርጓል።
♿️ ልዩ ታሳቢነት
የዓይነ ስውራን እና የመስማት ችግር ያለባቸው ተማሪዎች ተገቢውን የትምህርትና የድጋፍ አገልግሎት በሚያገኙባቸው ዩኒቨርሲቲዎች እንዲመደቡ ልዩ ታሳቢ ተደርጓል።
🔎 የምደባ ውጤት ለማየት
👉 የምደባ ውጤት:
https://student.ethernet.edu.et/view-placement
📝 ቅሬታ ለማቅረብ
የምደባ ውጤት ላይ ቅሬታ ያላችሁ ተማሪዎች ቅሬታችሁን በኦንላይን ሥርዓቱ ብቻ ማቅረብ ትችላላችሁ።
⏰ የቅሬታ ጊዜ፦ 5 ተከታታይ ቀናት ብቻ
👉 ቅሬታ ማቅረቢያ:
https://student.ethernet.edu.et/complaints
⚠️ ማሳሰቢያ
በቅሬታ ሂደት ሐሰተኛ መረጃ፣ የተሳሳተ ማስረጃ ወይም የተጭበረበረ ሰነድ ማቅረብ የተከለከለ ነው። የቀረበው መረጃ ይረጋገጣል፤ ሐሰተኛ መረጃ ያቀረበ ተማሪ ምደባው ሊሰረዝ ይችላል።
🎉 ለተመደባችሁ ተማሪዎች በሙሉ እንኳን ደስ አላችሁ!
በቀጣዩ የከፍተኛ ትምህርት ጉዟችሁ ስኬታማ እንድትሆኑ መልካም ምኞታችንን እንገልጻለን።
የትምህርት ሚኒስቴር
https://t.me/dbuhub