ChatCrawlersearch across public Telegram Open the app
🌺

🌺የውኃውና የመንፈሱ ወንጌል 🇪🇹

1 473 members
25 July 2026
27 July 2026
28 July 2026
29 July 2026
I
የኢየሱስ ምሳሌዎች ጥልቅ እውነቶች--የመንግስተ ሰማያት ደቀ መዝሙር የሆነ ጻፊ አዲሱንና አሮጌውን ከመዝገቡ የሚያወጣ ባለቤት (ክፍል 2) ፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨ ‹‹የመንግስተ ሰማያት ደቀ መዝሙር የሆነ ጻፊ›› ‹‹ከመዝገቡ›› (የእግዚአብሄር ቃል) ‹‹አዲሱንና አሮጌውን›› ያወጣል፡፡ በዚህ የኢየሱስ ምሳሌ ውስጥ ‹‹አሮጌ›› የተባለው ብሉይ ኪዳን ወይም ኢየሱስና ሐዋርያት ‹‹መጻህፍት›› ብለው የጠሩት ነው፡፡ ኢየሱስ ‹‹መጻህፍት›› ብሎ በጠራው ውስጥ 1.ሙሴ 2.መዝሙራትና 3. ነቢያት ተካተዋል፡፡ እነዚህ ሁሉ ስለ ኢየሱስ የሚያወሩ ናቸው፡፡   "ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፡- ግንበኞች የናቁት ድንጋይ እርሱ የማዕዘን ራስ ሆነ ይህም ከጌታ ዘንድ ሆነ ለዓይኖቻችንም ድንቅ ነው የሚለውን ከቶ ከመጻህፍት አላነበባችሁምን?›› (ማቴዎስ 22፡42)  አሁን ‹‹ከመዝገቡ›› የወጣውን ‹‹#አዲሱን›› እንመልከት፡፡ ሙሴ በጻፋቸው በአምስቱ መልዕክቶቹ ውስጥ ሰፊውን የመጽሐፎቹን ክፍል የያዙት እግዚአብሄር ለሕዝበ እስራኤል የሰጣቸው የመስዋዕት ሕጎች ነው፡፡ እነዚያ የመስዋዕት ሕጎች የኢየሱስን ማንነት፥ የሚሸከማቸውን ሐጢያቶችና ለእነዚያ ሐጢያቶች የሚከፍለውን ዋጋ ጉልህ አድርገው የሚገልጡ ናቸው፡፡ የእሰራኤል ሕዝብ፥ ካህናቶቹና ሊቀ ካህኑ የሚያቀርቡዋቸው ‹‹ነውር የሌለባቸው›› የበግ፥ የወይፈንና የፍየል መስዋዕቶች (ዘሌዋውያን ምዕራፍ 1,4,17) ናቸው። ኢየሱስ ‹‹የአለምን ሐጢያት የሚያስወግድ የእግዚአብሄር በግ›› (ዮሐንስ 1፡29) ተብሎዋል፡፡ ይህም እግዚአብሄር በሙሴ ‹‹መጻህፍት›› ውስጥ ለመስዋዕት ይቀርብ የነበረውን ‹‹ነውር የሌለበት የአንድ አመት ተባት ጠቦት›› የሚያመለክት ነበር፡፡ (ዘሁልቁ 28፡9) ‹‹ከአባቶቻችሁ እንደወረሳችሁት ከከንቱ ኑሮአችሁ በሚያልፍ ነገር በብር ወይም በወርቅ ሳይሆን ነውርና እድፍ እንደሌለው እንደ በግ ደም በክቡር የክርስቶስ ደም እንደተዋጃችሁ ታውቃላችሁ፡፡›› (1ኛ ጴጥሮስ 1፡19) ሐዋርያው ጴጥሮስ ‹‹የክርስቶስን ደም›› ‹‹ነውርና እድፍ›› ከሌለው ‹‹በግ ደም›› ጋር አነጻጽሮታል፡፡  ይህ እውነት በዕብራውያን መጽሐፍ ውስጥ በግልጽ ተጽፎዋል፡፡ ‹‹መሥዋዕትንና መባን አልወደድህም ሥጋን ግን አዘጋጀህልኝ፡፡... በዚህ ላይ መሥዋዕትንና መባን በሙሉ የሚቃጠል መሥዋዕትንም ስለ ሐጢአትም የሚሰዋ መሥዋዕትን አልወደድህም፤ በእርሱም ደስ አላለህም ብሎ እነዚህ እንደ ሕግ የሚቀርቡት ናቸው፡፡›› (ዕብራውያን 10፡5-8) እግዚአብሄር ያልወደዳቸው ‹‹በሙሉ የሚቃጠል መስዋዕትና ስለ ሐጢአት የሚሰዋ መሥዋዕት›› ኢየሱስ ወደዚህ ምድር በመጣ ጊዜ የተካቸው ናቸው፡፡ እግዚአብሄር በእነዚህ ‹‹መስዋዕቶች›› ደስ አልተሰኘም፡፡ ነገር ግን እነዚህን መስዋዕቶች በተካው በኢየሱስ ደስ ተሰኘ፡፡ (ማቴዎስ 3:16)  ‹‹ሊቀ ካህናትም ሁሉ ዕለት ዕለት እያገለገለ ሐጢአትን ሊያስወግዱ ከቶ የማይችሉትን እነዚያን መሥዋዕቶች ብዙ ጊዜ እያቀረበ ቆሞአል፡፡ እርሱ ግን ስለ ሐጢአት አንድን መሥዋዕት ለዘላለም አቅርቦ በእግዚአብሄር ቀኝ ተቀመጠ፡፡›› (ዕብራውያን 10፡11-12)  ምንም እንኳን የእነዚህ መስዋዕቶች አላማ ‹‹ሐጢአትን ማስወገድ›› ቢሆንም ያንን የማድረግ አቅም አልነበራቸውም፡፡ ኢየሱስ ግን በተደጋጋሚ ይቀርቡ የነበሩትን እነዚያን ‹‹ሐጢአትን ማስወገድ›› የማይችሉ ‹‹መስዋዕቶች›› በመተካት ‹‹አንድን መስዋዕት ለዘላለም አቅርቦ በእግዚአብሄር ቀኝ ተቀመጠ፡፡›› ይቀጥላል…
500 ·
31 July 2026
I
የኢየሱስ ምሳሌዎች ጥልቅ እውነቶች--የመንግስተ ሰማያት ደቀ መዝሙር የሆነ ጻፊ አዲሱንና አሮጌውን ከመዝገቡ የሚያወጣ ባለቤት (ክፍል 3) ፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨ ‹‹በሙሴ›› መጻህፍት ከዘጸአት 25፡8 ጀምሮ በመገናኛው ድንኳን ዙሪያ የሚከናወኑት ተግባራቶች በሙሉ የሚሽከረከሩት እስራኤሎች ሐጢያቶችን በሚሰሩበት ጊዜ በሚያቀርቡዋቸው መስዋዕቶች ዙሪያ ነበር፡፡ አንድ እስራኤላዊ ሐጢያት በሚሰራበት ጊዜ ከሐጢያቱ መላቀቅ የሚችለው እያነባ ወደ እግዚአብሄር በመጸለይና ሐጢያቱን በዝርዝር ለእግዚአብሄር በማቅረብ ሳይሆን ነውር የሌለበትን መስዋዕት ለእግዚአብሄር በማቅረብ ነው፡፡ የሐጢያት ስርየትን ለማግኘት እግዚአብሄር ያስቀመጠውን ሕግ ብቻ መከተል ይኖርበታል፡፡ በእግዚአብሄር የሐጢያት ስርየት ሕግ መሰረት የሐጢያት ስርየት ሊገኝ የሚችለው ‹‹መስዋዕትን›› በማቅረብ፤ እጆችን በመስዋዕቱ ራስ ላይ ጭኖ ሐጢያትን በመናዘዝና በመጨረሻም መስዋዕቱን በማረድ ብቻ ነው፡፡ (ዘሌዋውያን 1፡1-13፤ዘሌዋውያን 4፡1-35፤ዘሌዋውያን 16፡6-22) አንድ እስራኤላዊ ተራም ሰው ይሁን መኮንን ሐጢያት በሚሰራበት ጊዜ የሐጢያት ስርየትን ለማግኘት በእግዚአብሄር ፊት የመስዋዕት እንስሳን የማቅረብ ግዴታ አለበት፡፡ ለመስዋዕት የሚሆነው እንስሳ ወይፈን አውራ በግ አውራ ፍየል ጠቦትና የመሳሰሉት ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ለሐጢያቱ የሚሆን መስዋዕት ይዞ በመገናኛው ድንኳን አደባባይ ላይ ካልመጣ በሐጢያቱ ምክንያት ይሞታል፡፡ አንድ ሐጢያት የሰራ እስራኤላዊ በእርሱ ፋንታ የሚሞትለትን መስዋዕት ይዞ በሚቀርብበት ጊዜ ሁለት ወሳኝና አስፈላጊ ነገሮችን ማድረግ አለበት፡፡ 1.እጆቹን በመስዋዕቱ እንስሳ ራስ ላይ ጭኖ ሐጢያቶቹን ወደ መስዋዕቱ ማስተላለፍ 2. መስዋዕቱን በማረድ ደሙን ማፍሰስ፡፡ የሐጢያት ስርየትን ለማግኘት እነዚህ ሕጎች ተግባራዊ መሆን አለባቸው፡፡  አሁን ‹ከመዝገቡ›› የወጣውን ‹‹አዲሱን›› እንመልከት--ወንጌላትና የሐዋርያቶች መልዕክቶች ኢየሱስ የሰውን ዘር ሐጢያት በሙሉ በራሱ ላይ መሸከሙን ለማረጋገጥ ከአጥማቂው ዮሐንስ ጋር ‹‹ጽድቅን ሁሉ ለመፈጸም›› ተጠመቀ፡፡ (ማቴዎስ 3፡15) ‹‹ጽድቅ›› የሚያስፈልጋቸው ‹‹ሐጢያተኞች›› በመሆናቸው ኢየሱስ ‹‹ጽድቅን ሁሉ ለመፈጸም›› የተጠመቀው ያንን ‹‹ጽድቅ ለሐጢያተኞች›› ለመስጠት ነው፡፡ ኢየሱስ ሲጠመቅ እግዚአብሄር በጉልህ የሰዎችን ሐጢያቶች በጽድቁ ለወጠ፡፡ ኢየሱስ እኛ ‹‹የእግዚአብሄር ጽድቅ›› እንድንሆን ስለ እኛ ‹‹ሐጢአት›› ሆነ፡፡ (2ኛ ቆሮንቶስ 5፡21) ኢየሱስ ይህንን ካደረገና ለእኛ ‹‹ጽድቅን›› ፈጽሞ የእኛን ሐጢያት በምትኩ በራሱ ላይ በመውሰድ በመስቀል ላይ ስለ ‹‹ሐጢያታችን›› ደሙን አፈሰሰ፡፡ ኢየሱስ በመስቀል ላይ ደሙን ያፈሰሰው አስቀድሞ የሰውን ዘር ሐጢያት በሙሉ በጥምቀቱ በራሱ ላይ በመሸከሙ ነው፡፡ ኢየሱስ የሞተው ‹‹ስለ ሐጢያታችን›› ነው፡፡ (1ኛ ቆሮንቶስ 15፡3) ኢየሱስ ሐጢያታችንን በራሱ ላይ ባይወስድ ኖሮ አይሞትም ነበር፡፡ የሞቱ ምክንያት የእኛ ሐጢያት ነው፡፡   ይቀጥላል…
603 ·
2 August 2026
3 August 2026
4 August 2026
6 August 2026
9 August 2026
10 August 2026
24 August 2026
I
የኢየሱስ ጥምቀት ለደህንነቴ ምን ጥቅም አለው? መጥመቁ ዮሐንስ ኢየሱስን ባያጠምቀው ምን ችግር ይኖረዋል? ሰው መጽሐፍ እንደሚል በኢየሱስ ካለመነ መዳን ይችላል? መልሳቹን @dehninetbot ወይም @Jonahnlm ላይ አድርሱን። ከላይ ያለውን መጽሐፍ በነጻ አንብቡ በነጻ የእግዚአብሔር ጽድቅ ተቀበሉ።
376 ·
9 September 2026
10 September 2026
(የዮሐንስ ወንጌል ምዕ. 3) ---------- 13፤ ከሰማይም ከወረደ በቀር ወደ ሰማይ የወጣ ማንም የለም፥ እርሱም በሰማይ የሚኖረው የሰው ልጅ ነው። 14-15፤ ሙሴም በምድረ በዳ እባብን እንደ ሰቀለ እንዲሁ በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ የሰው ልጅ ይሰቀል ይገባዋል። 16፤ በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና።
14 September 2026
የጽድቅ አብሳሪ
Аудио
ከውሃና ከመንፈስ.m4a · 4.3 MB · click to show
Аудио
የእግዚአብሰብ ጽድቅ.m4a · 4.0 MB · click to show
Аудио
የኢየሱስ ጽድቅ ነው.m4a · 4.3 MB · click to show
[Verse 1] ከሰው ውጭ የሚገኝ አይደለም ሰውን የሚያረክሰው ከልብ የሚወጣው ነው ክፉው ሁሉ የሚመጣው ዝሙትና ስርቆት ትዕቢትና ተንኮል የልቤን ሁኔታ ቃልህ ገለጠው [Pre-Chorus] ራሴን ማጽዳት አልችልም በሥራዬ ንጹሕ አልሆንም አንተ ግን መጣህ ጌታ በውሃና በመንፈስ ልታድነኝ [Chorus] ከውሃና ከመንፈስ እንደገና እወለዳለሁ የኃጢአቴን ሁሉ በአንተ ላይ አየዋለሁ በዮርዳኖስ ውሃ ኃጢአቴን ተሸክመሃል በመስቀል ላይ ሞተሃል ሙሉ ማዳን ሰጥተኸኛል [Verse 2] የልቤ ክፋት ሲገለጥ እኔ እንዳልድን አየሁ የራሴን ጽድቅ ትቼ ወደ ኢየሱስ መጣሁ ውሃው ይናገራል “ኃጢአትህን ተሸክሜያለሁ” መስቀሉ ይናገራል “ፍርድህን ከፍያለሁ” [Chorus] ከውሃና ከመንፈስ እንደገና እወለዳለሁ የኃጢአቴን ሁሉ በአንተ ላይ አየዋለሁ በዮርዳኖስ ውሃ ኃጢአቴን ተሸክመሃል በመስቀል ላይ ሞተሃል ሙሉ ማዳን ሰጥተኸኛል [Bridge] “ከውሃና ከመንፈስ ካልተወለደ ሰው ወደ መንግሥቱ መግባት አይችልም” ይህ ነው ወንጌል ይህ ነው ተስፋዬ ኢየሱስ ሆይ አንተ ጽድቄ ነህ! [Final Chorus] ከውሃና ከመንፈስ እንደገና ተወለድኩ በኢየሱስ ሥራ ኃጢአቴ ተወገደ ከልቤ የሚወጣው ክፉውን አውቄአለሁ ነገር ግን የኢየሱስን ጽድቅ ተቀብያለሁ [Outro] ከውሃና ከመንፈስ… እንደገና ተወለድኩ… የኢየሱስ ጽድቅ የዘላለም ሕይወቴ ነው…
165 ·
17 September 2026
Архив по месяцам
Open in Telegram Каталог площадок Искать в ChatCrawler

A snapshot of an open public feed from the search index ChatCrawler — “Google for public Telegram”; refreshed as the venue is crawled. Times are UTC.

Public content only, official Telegram API. About · FAQ · What we do not do · Remove a page · Catalog