English
Open in Telegram
EEthiopian Islamic Affairs Supreme Council

Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council

✅ High trust
@eiasc1 · channel · Education · indexed since 2026-08-26
11 158subscribers−8 in a week
1 336average post reach
12%ER — reach to subscribers
178posts in 30 days
Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
Photo
Photo
Photo
Photo
Photo
Photo
Photo
Photo
Photo
Photo
2 · 1.3K ·
E
Link
click to show
ጠቅላይ ምክር ቤቱ ለ1448ቱ የአረህማን እንግዶች የጤና ምርመራ አገልግሎት ከሚሰጡ የጤና ተቋማት ጋር ውል ተፈራረመ። •••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••• ጥቅምት 9 /2019 ዓ.ል| ጁማደል አወል 8/1448 ዓ.ሒ بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ ••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••• አዲስ አበባ | የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ለ2019 ዓ.ል (1448 ዓ.ሂ) የሐጅ ተጓዦች የጤና ምርመራ አገልግሎት ከሚሰጡ 29 የህክምና ተቋማት ጋር ውል ተፈራረመ። የውል ስምምነቱ የአረህማን እንግዶች ወደ ሳውዲ አረቢያ ከማቅናታቸው በፊት አስፈላጊውን የጤና ምርመራ በተቀናጀ መልኩ በጥራት ለማግኘት እንደሚያስችላቸው የጠቅላይ ምክር ቤቱ በምክትል ፕሬዝዳንት ማዕረግ የሐጅና ዑምራ ዘርፍ ኅላፊ ዶክተር ሙሀመድ ሷሊህ በፊርማ ስነ ስርዓቱ ወቅት ተናግረዋል። ዘርፉ በዚህ ዓመት የሚያቀርበው የሀጅ አገልግሎትና መስተንግዶ "የላቀ አገልግሎት ለሑጃጆች እርካታ!" በሚል መሪ ሀሳብ ተግባራዊ እንደሚደረግ የገለጹት ኅላፊው የጨረታ መስፈርቱን አሟልተው የተመረጡት 29 የህክምና ተቋማት ደረጃውን የጠበቀ የህክምና አገልግሎት ለሁጃጆች እንደሚሰጡም አክለዋል። ውል የፈረሙ የጤና ተቋማት አስፈላጊ የህክምና ቁሳቁስና ባለሙያ ያላቸው በመሆኑ የአረህማን እንግዶች ፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎት አግኝተው የጉዞ ብቃት ማረጋገጫ የህክምና የምስክር ወረቀት እንደሚቀበሉም ዶክተር ሙሀመድ ሷሊህ ጨምረው አብራርተዋል። የሀጅና ዑምራ ዘርፉ የሳዑዲ ዓረቢያ ሐጅ ሚኒስቴር የሚያወጣቸውን መመሪያዎች መሠረት በማድረግ ተገቢ አገልግሎት ለመስጠት እየሰራ እንደሚገኝ ያመላከቱት ኃላፊው በዛሬው ዕለት ውል የተፈራረሙ የጤና ተቋማት በፈረሙት ውል መሰረት ኃላፊነታቸውን በብቃት እንዲውጡም አደራ ብለዋል። የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ዋና ስራ አስኪያጅ ሀጅ ከማል ሀሩን በበኩላቸው ለሑጃጆች የሚሰጠው የጤና ብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ዲጅታል በመሆኑ አገልግሎቱን የበለጠ ውጤታማ ያደርገዋል ብለዋል። ​የዘንድሮውን የሐጅ ጉዞ ዝግጅት ቀደም ብሎ የጀመረው ሀጅና ዑምራ ዘርፉ ከምግብ፣ ከትራንስፖርት እና ከሆቴል አገልግሎት አቅራቢ ተቋማት ጋር የስራ ውል በመፈራረም አገልግሎቱን ስኬታማ ለማድረግ እየሰራ ይገኛል። ••••••••••••••••••••••••••••••••••••• የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት ይከታተሉን | Follow us፡ ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council ቴሌግራም | t.me/eiasc1 ትዊተር | https://x.com/eiasc1
2 · 1.4K ·
Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
Photo
Photo
Photo
Photo
Photo
Photo
Photo
Photo
Photo
Photo
913 ·
E
Link
click to show
የ2019 (1448ዓ.ሒ) የሀጅ ምዝገባ ጥቅምት 12/2019 በመላው ሀገሪቱ በቴክኖሎጂ በተደራጁ 33 የሀጅ ምዝገባ ማዕከላት እንደሚጀምር ተገለጸ። ••••••••••••••••••••••••••••••••• ጥቅምት 12፣ 2019 ዓ.ል| ጁማዱ አል ኡላ 09 1448 ዓ.ሒ بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ ••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••• አዲስ አበባ ​የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የሐጅና ዑምራ ዘርፍ "የላቀ አገልግሎት ለሐጃጅ እርካታ" በሚል መሪ ሃሳብ የሚያቀርበውን የ2019 (1448 ዓ.ል) የሐጅ ጉዞ የሀጅ አገልግሎት ምዝገባ አስመልክቶ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል። ​የዘንድሮው የሀጅ ምዝገባ ሐሙስ ጥቅምት 12/ 2019 ዓ.ል በዘመናዊ ቴክኖሎጂ በተደራጁ 33 የማስተባበሪያ ጣቢያዎች መካሄድ እንደሚጀምር በመግለጫው ተመላክቷል። የሀጅ ምዝገባው ጥር 10/2019 ዓ.ል እንደሚጠናቀቅ እና አጠቃላይ ክፍያውም 827,000 (ስምት መቶ ሃያ ሰባት ሺህ) ብር እንደሆነ ተገልጿል። የሐጅ አገልግሎት ዋጋ ተመን የወጪ መጠንን ለመቆጣጠርና ጥራቱን ለማሻሻል የሳዑዲ ዓረቢያ አገልግሎት አቅራቢ ድርጅቶችን በግልጽ ጨረታ በማወዳደር የተሻለ ስራ ስለመሰራቱም በመግለጫው ተመላክቷል። በመግለጫው መክፈቻ ላይ ንግገር ያደረጉት የጠቅላይ ምክር ቤቱ ​የልማትና ማህበራዊ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝዳንት ሸይኽ ሃሚድ ሙሣ የሐጅ አገልግሎቱ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻለ መምጣቱን ገልጸው ባለፈው ዓመት የተገኘውን የላቀ ውጤት በዚህ ዓመትም አሻሽሎ ለማስቀጠል የዝግጅት ስራዎች ተጠናቀው ምዝገባ መጀመሩን አብስረዋል። የጠቅላይ ምክር ቤቱ በምክትል ፕሬዝደንት ማዕረግ የሀጅና ዑምራ ዘርፍ ኃላፊ ዶክተር ሙሀመድ ሷሊህ በጋዜጣዊ መግለጫው ዕለት እንዳስረዱት ሀጅና ዑምራ ዘርፉ ባለፈው ዓመት ባስመዘገበው የላቀ አፈጻጸም ከሳዑዲ ዓረቢያ ሐጅ ሚኒስቴር ከፍተኛው የክብር ማዕረግ የሆነውን የለበይቱም የአልማዝ ደረጃ ሽልማት አግኝቷል። ዶክተር ሙሀመድ ሷሊህ አክለውም በዚህ ዓመትም አገልግሎትና መስተንግዶውን የሳዑዲ ሀጅ ሚኒስቴር በሚያወጣው መመሪያ መሰረት ደረጃውን ጠብቆ እንዲፈጸም ለማድረግ በቂ የዝግጅት ስራ መሰራቱን ጠቅሰው ንያ ያላቸው ሁሉ ከወዲሁ በአቅራቢያቸው ወደሚገኝ የሀጅ ምዝገባ ማዕከል እንዲመዘገቡ ጥሪ አቅርበዋል። የጠቅላይ ምክር ቤቱ ​የፕሬዝዳንት ዋና ጽህፈት ቤት ዋና ኃላፊ ዑስታዝ አቡበከር አህመድ በበኩላቸው ሐጅ በእስልምና ትልቅ ቦታ የሚሰጠው የአምልኮ ስርዓት በመሆኑ ሀጅ የማድረግ አቅሙ ያላቸው ምእመናን በመዘግየታቸው ምክንያት እድሉን እንዳያጡና በአገልግሎት አሰጣጡ ላይ ጫና እንዳይፈጥሩ በጊዜ እንዲመዘገቡ ጥሪ አድርገዋል። ጋዜጣዊ መግለጫውን በንባብ ያቀረቡት የጠቅላይ ምክር ቤቱ የአስተዳደር ጉዳዮችና የተቋማዊ ልህቀት ምክትል ፕሬዝዳንት ዑስታዝ ተምኪን አብዱላሂ የሐጅ ምዝገባ የልዩ መስተንግዶ (VIP) እና የትውልደ ኢትዮጵያ (ዲያስፖራ) የሐጅ አገልግሎትን በተመለከተ በቀጣይ ማብራሪያ እንደሚሰጥ ጠቅሰዋል። በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ የጠቅላይ ምክር ቤቱ ስራ አስፈጻሚ አባላት፣ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎችና በርካታ የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች የተገኙ ሲሆን መግለጫው በተለያዩ ቋንቋዎች ይፋ ሆኗል። ••••••••••••••••••••••••••••••••••• የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነትና ሚዲያን ይከታተሉ | Follow us፡ ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council ቴሌግራም | t.me/eiasc1 ትዊተር | https://… Read in full →
22 · 1.1K ·
E
Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
Link
click to show
በክቡር ዶክተር ሸይኽ ሀጅ ኢብራሂም ቱፋ የተመራ የጠቅላይ ምክር ቤቱ ይፋዊ የስራ ልዑክ የአዲስ አበባ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤትን ጎበኘ። ••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••• ጥቅምት 21/2019 ዓ.ል| ጁማደል አወል 20/1448 ዓ.ሒ بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ •••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••• ​አዲስ አበባ | በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት የክቡር ዶክተር ሸይኽ ሀጂ ኢብራሂም ቱፋ የተመራው የጠቅላይ ምክር ቤቱ ከፍተኛ የስራ አመራሮች ልዑክ በአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት በተከናወኑ የለውጥ፣ የአገልግሎት ማሻሻያ እና የልማት ስራዎችን ጎበኘ። የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት የክቡር ዶክተር ሸይኽ ሱልጧን አማን ኤባ እና የስራ ኅላፊዎች ከፍተኛ ምክር ቤቱ የተከናወናቸውን የአደረጃጀት፣ የአገልግሎት አሰጣጥ ማሻሻያ እና ጅምር የልማት ስራዎችን አስመልከተው ለልዑኩ ገለጻ አድርገዋል። የክቡር ዶክተር ሸይኽ ሀጂ ኢብራሂም ቱፋ በጉብኝቱ ማጠናቀቂያ ላይ ባደረጉት ንግግር የአዲስ አበባ መጅሊስ ተቋማዊ አሰራርን በማዘመን ማህበረሰቡን ለማገልገል እያደረገ ያለው ጥረት የሚደነቅ ነው ብለዋል። በአዲስ አበባ መጅሊስ ተግባራዊ እየተደረጉ ያሉት የለውጥ እና የልማት ስራዎች ለሌሎች የክልል እና የከተማ አስተዳደር መጅሊሶች አርአያ ሊሆን የሚችል እንደሆነ የገለጹት ፕሬዝደንቱ ጠቅላይ ምክር ቤቱ ለአዲስ አበባ መጅሊስ የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥልም አረጋግጠዋል። የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት የክቡር ዶክተር ሸይኽ ሱልጧን አማን ኤባ በበኩላቸው ልዑኩ ላደረገው ጉብኝትና ወንድማዊ ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበው ከፍተኛ መወክር ቤቱ የጀመራቸውን የለውጥና የልማት ስራዎች በቀጣይም አጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል። የአዲስ አበባ መጅሊስ አሰራሩን በማዘመን ለሕዝበ ሙስሊሙ የሚሰጠውን አገልግሎት ለማቀላጠፍ የዘረጋቸው አሰራሮች በልዑኩ የተጎበኙ ሲሆን መጅሊሱ ሁለንታዊ አቅሙን ለማጠናከር የያዛቸውን ዕቅዶች በተመለከተ ለልዑኩ ገለፃ ተደርጓል። በይፋዊ የስራ ጉብኝቱ ላይ የኡለማ ጉባዔ ዘርፍ ምክትል ፕሬዝዳንት ሸይኽ ጁነይድ ሐምዛ፣ የልማትና ማሕበራዊ ጉዳይ ዘርፍ ምክትል ፕሬዝዳንት ሸይኽ ሐሚድ ሙሳ እና ሌሎች የጠቅላይ ምክር ቤቱ የስራ አስፈጻሚ አባላት፣ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎችና ዑለማዎች ተገኝተዋል። ••••••••••••••••••••••••••••••••••• የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት ይከታተሉን | Follow us፡ ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council ቴሌግራም | t.me/eiasc1 ትዊተር | https://x.com/eiasc1
808 ·

An open public feed from the search index ChatCrawler — “Google for public Telegram”; refreshed as the venue is crawled. Times are UTC.

Public content only, official Telegram API. About · FAQ · Index limits · Remove a page · Catalog · Search · How we count