ERA ኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር
Link
click to show
click to show
የለሚ ሲሚንቶ ፋብሪካ - ጀማ ወንዝ የሲሚንቶ ኮንክሪት መንገድ ግንባታ ሥራ በይፋ ተጀመረ።
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 06 ቀን 2019 ዓ.ም. (ኢመአ)፦ በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ሰሜን ሸዋ ዞን እንሳሮ ወረዳ የሚገኘው የለሚ ሲሚንቶ ፋብሪካ - ጀማ ወንዝ የሲሚንቶ ኮንክሪት መንገድ የግንባታ ፕሮጀክት ሥራ በይፋ ተጀመረ።
የሰሜን ሸዋ ዞን እና የእንሳሮ ወረዳ ከፍተኛ አመራሮች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የደብረ ብርሃን አካባቢ ፕሮጀክቶች ማኔጅመንት ጽሕፈት ቤት የሥራ ኃላፊዎች እንዲሁም የለሚ ሲሚንቶ ፋብሪካ ተወካዮች በተገኙበት የግንባታ ሥራው በይፋ ተጀምሯል።
ይህ 20 ኪሎ ሜትር ርዝማኔ የሚሸፍነው የመንገድ ፕሮጀክት ሥራ የመንግሥት የልማት ድርጅት የሆነው ሕብር ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን የሥራ ተቋራጭ የሚያከናውነው ሲሆን፤ የጥራት ቁጥጥርና የማማከር ሥራውን ደግሞ የኢትዮጵያ ኢንጅነሪንግ ኮርፖሬሽን በአማካሪ መሐንዲስነት በኃላፊነት ይከታተለዋል። ፕሮጀክቱ በኮንትራት ውሉ መሰረት በ14 ወራት እንደሚጠናቀቅ ይጠበቃል።
ይህ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት ሲጠናቀቅ የለሚ-አለምከተማ -ደጎሎ የመንገድ ፕሮጀክት አካል እንደመሆኑ የአካባቢውን ማኅበረሰብ በማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ትስስር ይበልጥ ለማጠናከር አይነተኛ ጠቀሜታ አለው።
ከዚህም ባለፈ ለለሚ ሲሚንቶ ፋብሪካ ዋነኛ ጥሬ ዕቃ የሆኑትን የኖራ ድንጋይ እና ጂፕሰም በከፍተኛ ፍጥነትና ቅልጥፍና ለማጓጓዝ ያስችላል።
በተጨማሪም በለሚ ከተማ ዙሪያና በደብረ ብርሃን ከተማ ለተገነቡ ፋብሪካዎች የኢንዱስትሪ ግብዓቶችን ለማቅረብ ከፍተኛ ፋይዳ ይኖረዋል።
የመንገዱ የጎን ስፋት በቀበሌ መቀመጫዎች 12 ሜትር እንዲሆን የተደረገ ሲሆን፣ በገጠር አካባቢዎች ደግሞ ከ8 እስከ 10 ሜትር ስፋት እንዲኖረው ተደርጎ ይገነባል።
የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክቱ በተያዘለት የጊዜ ሰሌዳና የበጀት ገደብ ውስጥ በጥራት ለማጠናቀቅ ይቻል ዘንድ፣ የሚመለከታቸው የፌደራል፣ የክልል፣ የዞን እና የወረዳ የመንግሥት መዋቅሮች እንዲሁም የአካባቢው ማኅበረሰብ ለግንባታ ሥራው አስፈላጊውን ድጋፍና ትብብር እንዲያደርጉ የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ያሳስባል።
በተጨማሪ
› አጭር መልዕክት 8561
› ፖስታ ሳጥን ቁጥር 1770
› ድህረገጽ www.era.gov.et
› ፊስቡክ https://www.facebook.com/www.era.gov.et
› ቴሌግራም https://t.me/ethioroads
› ትዊተር https://twitter.com/EthiopiaRoadsAd
› ኢንስታግራም https://www.instagram.com/ethioroads
› ኢሜል [email protected]
› ዩቲዮብ www.youtube.com/@ethioroads
❤4
9 · 2.8K · ERA ኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር
Link
click to show
click to show
የቢሾፍቱ - ጨፌ ዶንሳ - ሰንዳፋ መንገድ ግንባታ ሥራ በተያዘው ዓመት ለማጠናቀቅ እየተሠራ ነው
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 10/2019 (ኢ መ አ):- የኦሮሚያ እና የአማራ ክልሎችን ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ትስስር የሚያጠናክረው የቢሾፍቱ - ጨፌ ዶንሳ - ሰንዳፋ መንገድ ግንባታ ዋና ዋና ሥራዎች በተያዘው ዓመት ለማጠናቀቅ እየተሠራ ነው።
በአጠቃላይ 53 ኪሎ ሜትር የሚሸፍነው ይህ የመንገድ ፕሮጀክት፥ ከቢሾፍቱ ወደ ሰንዳፋ ለመጓዝ በአዲስ አበባ በኩል ይደረግ የነበረውን የ83 ኪሎ ሜትር ርቀት በ30 ኪሎ ሜትር የሚያሳጥር ነው። ይህም የአካባቢውን ማኅበረሰብ የጉዞ እንግልትና ወጪ በከፍተኛ ደረጃ ይቀንሳል።
ከዚህም ባለፈ አካባቢው ከፍተኛ የጤፍ፣ ስንዴ እና ሽንብራ ምርት የሚመረትበት በመኾኑ፥ የግብርና ምርቶችን በፍጥነት ወደ ቢሾፍቱና አዲስ አበባ ገበያዎች ለማውጣት ብሎም የኢንቨስትመንት ፍሰትን ለመሳብ ትልቅ ፋይዳ አለው።
የመንገድ ፕሮጀክቱ ከዚህ ቀደም ከሥራ ተቋራጩ የአቅም ውስንነት እና ከወሰን ማስከበር መዘግየት ጋር ተያይዞ በተያዘለት ጊዜ እንዳይጠናቀቅ እንቅፋት ገጥሞት የነበረ ቢኾንም፥ አሁን ላይ ችግሩን ለመፍታት ሥራው በሁለት ሎት ተከፍሎ በሁለት ተቋራጮች በመከናወን ላይ ይገኛል። ይህም በአፈጻጸሙ ላይ ከፍተኛ መሻሻል እንዲታይ አድርጓል።
በዚህም መሠረት የመጀመሪያው ሎት ከቢሾፍቱ ከተማ መነሻውን አድርጎ እስከ ጨፌ ዶንሳ መግቢያ ድረስ ያለው 24 ነጥብ 3 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን ሲኾን፥ በሀገር-በቀሉ ራማ ኮንስትራክሽን በመከናወን ላይ ይገኛል። ሁለተኛው ሎት ደግሞ ቀሪውን የዋና መንገድ ክፍል እና በጨፌ ዶንሳ ከተማ ውስጥ የሚሠራውን 1 ነጥብ 8 ኪሎ ሜትር የውስጥ አገናኝ መንገድ ጨምሮ በአጠቃላይ 28 ነጥብ 9 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን ነው። ግንባታውን የኢትዮጵያ ኢንጅነሪንግ ኮርፖሬሽን በማከናወን ላይ ይገኛል።
አሁን ላይ ከአጠቃላይ የመንገዱ ክፍል ውስጥ 30 ኪሎ ሜትር ያህሉን አስፋልት የማንጠፍ ሥራ ተጠናቅቋል። በቀሪው የመንገድ ክፍል የአፈር ቁፋሮ እና ሙሌት እንዲሁም የሰብቤዝ እና ቤዝኮርስ ግብዓት የማምረት ሥራዎች በመሠራት ላይ ናቸው።
የመንገድ ግንባታው ከፌደራል መንግሥት በተመደበ አጠቃላይ 3 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር ወጪ ነው በመከናወን ላይ የሚገኘው።
በተጨማሪ
› አጭር መልዕክት 8561
› ፖስታ ሳጥን ቁጥር 1770
› ድህረገጽ www.era.gov.et
› ፊስቡክ https://www.facebook.com/www.era.gov.et
› ቴሌግራም https://t.me/ethioroads
› ትዊተር https://twitter.com/EthiopiaRoadsAd
› ኢንስታግራም https://www.instagram.com/ethioroads
› ኢሜል [email protected]
› ዩቲዮብ www.youtube.com/@ethioroads
❤8👍1
7 · 2.1K ·