ChatCrawlersearch across public Telegram Open the app
የ

የአባቶች ምክር comment

1 536 members
27 August 2026
ለነገ አትበሉ! ''ዲያብሎስ 'ነገ' በሚል የተስፋ ቃል ዛሬን ይነጥቀናል : ዛሬን ካልተጠቀምንባት ነገም እንደዚሁ በከንቱ ታልፋለች። የሰይጣን ስልቱ በአሁኑ ሰዓት ልናደርገው የሚገባንን በጎ ነገር እንድናዘገይ ማድረግ ነው ፤ ምክንያቱም አንድን መልካም ሥራ ስ ለነገ ካስተላለፍነው ፣ ያቺ ነገ ስትመጣም ለሌላ ነገ እንድናስተላልፋትና ዕድሜአችንን በሙሉ በከንቱ ቀጠሮ እንድንጨርስ ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ እውነተኛው ጥበብ ዛሬ በእጃችን ያለቸውን ሰዓት ለበጎ ሥራና ለንስሐ መጠቀም ነው።" ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ የቅዱሳን አምላክ ዛሬችንን እንድንጠቀምበት አስተዋይ ልቦናን ለሁላችንም ያድለን!🥺🙏
2.7K ·
I
Фотография
click to show
That’s exactly how I feel right now, 'አለማመኔን እርዳው ጌታየ!'😭😭
3K ·
28 August 2026
Y
እምነቴ ደካማ ነው ምን ላድርግ ? እምነት እያደር የሚያድግ ነው። በመጽሐፍ ቅዱስ ሐዋርያት እራሱ ጌታ ሆይ እምነትን ጨምርልን እያሉ ሲለምኑት ተመልክተናል። ስለዚህ አንተም ጌታ እግዚአብሔርን በጸሎት ለምነው። በየዕለቱ ከመጽሐፍ ቅዱስ ጥቂት ጥቂት አንብብ [ በተለይ ታሪኮችን ] ፤ ቅዳሴ አስቀድስ [ ቅዳሴው ውስጥ በዜማ የምንለውን ለመረዳት ሞክር ] .... ከሁሉም በላይ ግን በእግዚአብሔር መመካት ያስፈልጋል። አስቀድሞም ካለመኖር ወደ መኖር አምጥቶ የፈጠረን እሱ እንደሆነ ፣ ኋላም በዘመኑ ፍጻሜ ከድንግልም ማርያም ተወልዶ ተሰቅሎ ሞቶ ያዳነን( በውድ ደሙ የገዛን ) እሱ መሆኑን ፤ ነገም በዓለም ፍጻሜ ለፍርድ እንደሚመጣና አለምን አሳልፎ እንደሚኖር ሁሌም ማስታወስ ያስፈልጋል። ይሄን ግዜ ከጌታችን በቀር ሌላ ተስፋ እንደሌለን እየተገነዘብን እንመጣለን በርሱ ላይ ያለን እምነትም እየጨመረ ይመጣል። ✍ ሀብተ ኢየሱስ @YilikalOrthodox
797 ·
I
"ዕለትን የሠጠህ እርሱ ለዕለት የሚበቃህንም ይሠጥሃል!" ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ
2.4K ·
29 August 2026
ራሳችሁን ስሩ! “ለእናንተ የምትኖሩት መቼ ነው? ስለኳስ የምትኖሩት? ለሰው መኖር የምናቆመው መቼ ነው? ታውቃላችሁ ዲያያቢሎስ እንዴት እንደተጫወተብን 'እኔ በማንነቴ እኮራለሁ' ስንል አናፍርም በትክክል በደምብ ተደርጎ ጎግል (Google) ስምን እንደተሰራ ታውቃላችሁ? ሳይኮሎጂያችንን ለማጥናት በደምብ የተሰራ ነው ይሄንን ትተን ራሳችንን እንስራ! ቤት የምሰራ ስለቤተክርስቲያኔ የምኖር መቼ ነው ለመንግስተ ሰማያት የምኖረው መቼ ነው ለሰውነቴ የምኖረው መቼ ነው? ለህሊናዬ የምኖረው መቼ ነው? እንድትሉ ነው? ሃይማኖት መሰረት ፍቅር ግድግዳ ተስፋን ጉልላት አድርጋችሁ ራሳችሁን ስሩ?" አባ ገብረኪዳን ግርማ
2.5K ·
30 August 2026
I
እንኳን ለአባታችን ለፃድቁ አቡነ ተክለሃይማኖት እና ለእናታችን ለቅድስት ክርስቶስ ሠምራ ዓመታዊ መታሰቢያ በዓል አደረሳችሁ! የፃድቅ ሰው ፀሎት ኃይልን ያደርጋልና እኛን መማር የማይሰለቸው ቅዱስ እግዚአብሔር በቃልኪዳናቸው ይማረን ከበረከታቸውም ያሳትፈን!
1.4K ·
M
A
D
እንኳን አብሮ አደረሰን ! አሜን 🙏🙏🙏
I
ለካ የከለከለኝ ለዚህ ነበር...! እስክትሉ ድረስ እግዚአብሔር አብዝቶ ይባርካችሁ
1.1K ·
Архив по месяцам
Open in Telegram Каталог площадок Искать в ChatCrawler

A snapshot of an open public feed from the search index ChatCrawler — “Google for public Telegram”; refreshed as the venue is crawled. Times are UTC.

Public content only, official Telegram API. About · FAQ · What we do not do · Remove a page · Catalog