Photo
click to show
click to show
Photo
click to show
click to show
Link
click to show
click to show
ሙስና የመልካም አስተዳደር ጠንቅ በመሆኑ ለመፍታት በቁርጠኝነት መሥራት ወቅቱ የሚጠይቀው ኃላፊነት ነው - አቶ አረጋ ከበደ
****
(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ መስከረም 21/2019 ዓ.ም አዲስ አበባ) የአማራ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ አረጋ ከበደ በድጋሚ የክልሉ ፕሬዝዳንት ሆነው ከተሾሙ በኋላ ለክልሉ ምክር ቤት ባደረጉት ንግግር፣ መንግሥት ትኩረት ሰጥቶ ሊሠራባቸው ከሚገባቸው ዋና ጉዳዮች መካከል ሙስና አንዱ መሆኑን ገለጹ።
የመንግሥት አገልግሎት አሰጣጥ የክልሉን ሕዝብ ዕለታዊ ኑሮ በቀጥታ የሚነካ በመሆኑ፣ ልማትንና መልካም አስተዳደርን ለማረጋገጥ ያለው ሚና ከፍተኛ መሆኑንም አመልክተዋል።
ነገር ግን በአሁኑ ወቅት በአገልግሎት አሰጣጡ ኢ-ፍትሐዊነት፣ አድልዎ፣ እንግልት እንዲሁም የዜጎች ጊዜና ጉልበት መባከን የሚታይበት ሁኔታ መኖሩን ጠቁመዋል። አንዳንድ የመንግሥት አገልግሎቶችንም እንደግል የገቢ ምንጭ የመጠቀም አሠራር መኖሩን ገልጸዋል።
ይህ ሁኔታ ዜጎች ለአነስተኛ ጉዳይ እንኳን ጊዜያቸውን፣ ጉልበታቸውንና ገንዘባቸውን እንዲያባክኑ እያደረገ መሆኑንም አስረድተዋል።
እነዚህን ችግሮች ለማስተካከል ዜጋን ማዕከል ያደረገ፣ ቀልጣፋና ግልጽ የአገልግሎት አሰጣጥ ሥርዓት ለመዘርጋት ጥረት እየተደረገ መሆኑን አቶ አረጋ ገልጸዋል። በዚህም የሕዝቡን የአገልግሎት ጥያቄ ለመመለስና እንግልትን ለማቃለል በክልሉ የመሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ተቋማት እንዲስፋፉ እንደሚደረግ ጠቁመዋል።
በተቋማት የሚሰጡ አገልግሎቶችን ዘመናዊ፣ ቀልጣፋና ከብልሹ አሠራር የፀዱ ለማድረግ የተጀመሩ ሥራዎችም በቁርጠኝነት እንደሚቀጥሉ አስታውቀዋል።
በተለይም ሙስና ፍትሐዊነትንና እኩልነትን የሚያጓድል፣ የሕዝብን እድገትና ልማት የሚያደናቅፍ በመሆኑ፣ ከመሬት አስተዳደር፣ ከመንግሥት ግዥና ጨረታ፣ ከታክስ እና ከፕሮጀክት አስተዳደር ጋር የተያያዙ የሙስና ችግሮችን ለመፍታት ትኩረት ተሰጥቶ እንደሚሠራ ፕሬዝዳንቱ ገልጸዋል።
ሙስናን መከላከልና የሚፈጠሩ ችግሮችን በዘላቂነት መፍታት የሕዝብን ፍትሐዊ የአገልግሎት ጥያቄ ለመመለስና የልማት ጥረቶችን ለማጠናከር ወሳኝ መሆኑን ጠቅሰው፣ ለችግሩ ውጤታማና ዘላቂ መፍትሔ ማስቀመጥ ወቅቱ የሚጠይቀው ኃላፊነት መሆኑን አስገንዝበዋል።
ትውልድን በሥነምግባር፤ ተቋምን በአሰራር!
የሙስና ወንጀል መጠቆሚያ አማራጮችን፣ ወቅታዊ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት👇🏾
#NCRS ሞባይል መተግበሪያ
#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details?id=com.codewaveet.ecis
#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id659366231
ለሀብት ማሳወቅና ምዝገባ፦ https://feaccears.gov.et/
ዌብሳይት፦ https://www.feacc.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/
ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc
ዩትዩብ፡- https://www.youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
1K · FEAC
Photo
click to show
click to show
Photo
click to show
click to show
Photo
click to show
click to show
Photo
click to show
click to show
Photo
click to show
click to show
Photo
click to show
click to show
Photo
click to show
click to show
Photo
click to show
click to show
Photo
click to show
click to show
Photo
click to show
click to show
Photo
click to show
click to show
Link
click to show
click to show
ለተቋማት የሥነምግባርና ፀረ-ሙስና ሥልጠና ባለሙያዎች የአሰልጣኞች ስልጠና ተሰጠ
********
(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ መስከረም 22/2019 ዓ.ም አዲስ አበባ) የፌዴራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን በዘርፍ ተቋማት ለሚገኙ የሥነምግባርና ፀረ-ሙስና ሥልጠና ባለሙያዎች የአሰልጣኞች ሥልጠና (TOT) ሰጠ።
ሥልጠናው በተቋማት የሚገኙ የሥነምግባርና ፀረ-ሙስና ሥልጠና ባለሙያዎችን የማሰልጠን ክህሎትና አቅም በማሳደግ፣ በየተቋማቱ ሥልጠናዎችን በቀጣይነት እንዲያስፈጽሙ ማዘጋጀትና የኮሚሽኑን የሥነምግባር ግንባታና የፀረ-ሙስና ሥልጠና ተደራሽነት ማስፋትን ያለመ ነው።
የሥነምግባርና ሙስና መከላከል ሥልጠናዎች ውጤታማና ተደራሽ እንዲሆኑ ብቁ አሰልጣኞችን ማፍራት አስፈላጊ በመሆኑ፣ በሥልጠናው የተሳታፊዎችን የማሰልጠን ክህሎት ለማሳደግ ትኩረት ተሰጥቷል። ይህም በተቋማት ውስጥ ሥልጠናዎችን በቀጣይነትና በተሻለ ጥራት ለማካሄድ ያግዛል።
የአሰልጣኞች ሥልጠናውን የአገር አቀፍ የፀረ-ሙስና ምርምር ትስስር አባል ዶ/ር ዮሐንስ ጴጥሮስ የሰጡ ሲሆን፣ ተሳታፊዎች በሥልጠናው ይዘት ላይ ጥያቄዎችንና ሀሳቦችን አንስተዋል።
በመድረኩም የኮሚሽኑ አመራርና የሥራ ኃላፊዎች ለተነሱ ጉዳዮች ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተው፣ ቀጣይ የሥራ አቅጣጫዎችን አስቀምጠዋል።
በሥልጠናው የዘርፍና ተጠሪ ተቋማት የሥነምግባርና ፀረ-ሙስና ሥልጠና ባለሙያዎች እንዲሁም የኮሚሽኑ ባለሙያዎች ተሳትፈዋል።
ሥልጠናው በተቋማት ውስጥ የሥነምግባር ባህልን ለማጠናከር፣ የሙስና መከላከል ግንዛቤን ለማስፋት እና የፀረ-ሙስና ሥራዎችን በተቋማዊ ደረጃ በቀጣይነት ለማስፈጸም የሚያግዝ የሰው ኃይል አቅም ለመፍጠር ወሳኝ ሚና አለው።
ትውልድን በሥነምግባር፤ ተቋምን በአሰራር!
የሙስና ወንጀል መጠቆሚያ አማራጮችን፣ ወቅታዊ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት👇🏾
#NCRS ሞባይል መተግበሪያ
#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details?id=com.codewaveet.ecis
#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id659366231
ለሀብት ማሳወቅና ምዝገባ፦ https://feaccears.gov.et/
ዌብሳይት፦ https://www.feacc.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/
ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc
ዩትዩብ፡- https://www.youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
2 · 980 · FEAC
Photo
click to show
click to show
Photo
click to show
click to show
Photo
click to show
click to show
Photo
click to show
click to show
Photo
click to show
click to show
Link
click to show
click to show
ብልሹ አሠራሮችን ለማስወገድ የሕግ የበላይነትንና ተጠያቂነትን እናጠናክራለን - ርዕሰ መስተዳድር የትምጌታ አስራት (ዶ/ር)
*******
(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ መስከረም 23/2019 ዓ.ም ) የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት በ7ኛው ዙር መስራች ጉባኤ ላይ የትምጌታ አስራት (ዶ/ር)ን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አድርጎ ሰይሟል።
በዚሁ ወቅት ርዕሰ መስተዳድሩ በቀጣዮቹ አምስት ዓመታት ለመከናወን የታቀዱ የሥራ አቅጣጫዎችን ለምክር ቤቱ አባላት አቅርበዋል።
ርዕሰ መስተዳድሩ እንደገለጹት፣ በሕዝብና በመንግሥት የተሰጠንን ኃላፊነት በቅንነትና በታማኝነት ለመወጣት ተዘጋጅተናል። የመንግሥት ውጤታማነትም በንግግር ሳይሆን በዜጎች ሕይወት ላይ በሚመጣው ተጨባጭ ለውጥ እንደሚለካ ገልጸዋል።
ብልሹ አሠራሮችን ለማስወገድም የሕግ የበላይነትን በማጠናከር ተጠያቂነትን ለማስፈን እንደሚሠሩ ጠቁመዋል።
በተለይም ለዜጎች የሚሰጡ አገልግሎቶችን ከብልሹ አሠራርና ከአላስፈላጊ መጓተት ነፃ ለማድረግ የተጀመሩ ዲጂታል አሠራሮችን በማስፋፋት የመልካም አስተዳደር ጥያቄን ለመመለስ ትኩረት እንደሚሰጡም አመልክተዋል።
በተጨማሪም የሕዝብን ችግር የሚያዳምጥ፣ ጥያቄዎችን በፍጥነት የሚመልስና ለሥራው ተጠያቂነትን የሚወስድ አስተዳደር ለመገንባት እንደሚሠሩ አስታውቀዋል።
እነዚህን የሥራ አቅጣጫዎች ለማሳካትና የሕዝቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመቀናጀት በቁርጠኝነት እንደሚሠሩም ርዕሰ መስተዳድሩ ገልጸዋል።
ትውልድን በሥነምግባር፤ ተቋምን በአሰራር!
የሙስና ወንጀል መጠቆሚያ አማራጮችን፣ ወቅታዊ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት👇🏾
#NCRS ሞባይል መተግበሪያ
#ለAndroid ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details?id=com.codewaveet.ecis
#ለApple or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id659366231
ለሀብት ማሳወቅና ምዝገባ፦ https://feaccears.gov.et/
ዌብሳይት፦ https://www.feacc.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/
ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc
ዩትዩብ፡- https://www.youtube.com/@federalethicsanti-corrupti149
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
2 · 804 · FEAC
Photo
click to show
click to show
የመደመር መንግስት ምሥረታ ስለፀረ-ሙስና ትግል ምን አቅጣጫ እና አቋም ይይዛል ብለው ያስባሉ? ገንቢ አስተያየትዎን ይስጡበት!

72 ·