Аудио
Hamlet_Beljun_MENFES_KIDUS_መንፈስ_ቅዱስ_New_Ethiopian_Gos.m4a · 5.7 MB · click to show 💬በጌታ ደጋግማችሁ ስሙት🥹🙏🏿ብትችሉ ስልካችሁን ዝጉት እና ካልሆነም notification of አድርጋችሁ በማስተዋል ቢያንስ ሁለቴ አድምጡት🔂😭🎧🙌🏾
✍መቼስ ለበዓል ቤተሰቦቻችንን ዘመዶቻችንን ጎደኞቻችንን ወዘተ አውርተናል ብቻ ብዙ ብለን ተብለን የለ እስቲ አሁን በእርጋታ በሙሉ ልብ ሆነን በዚህ መዝሙር ከመንፈስ ቅዱስ ጋር እናውራ! 🤍🤍🧎♀🧎♂
ስሙእና ምኑን ከምኑ አደርገዋለሁ
ህይወቴ ያላንተ ድቅድቅ ጨለማ ነው
ምኑ ከምኑ ይሆንልኛል
ያላንተ እኮ ቀኑም ይጨልምብኛል።
አፍ አለው ይነገር ኑሮዬ
እንዴት እንደመራኸኝ ትላንትናዬ
ሕይወቴን ሰጥቼህ አላፈርኩም
እጆችህ ላይ ምንም ነገር አይበላሽም።
እኔ አላውቅበትም አኗኗሩን አካሄዱን አደራረጉን
እኔንለኔ አትተው አትተወኝ አሳልፈህ እኔንለኔ አትስጠኝ
እኔ አላውቅበትም አኗኗሩን አካሄዱን አደራረጉን
እኔንለእኔ አትተው አትተወኝ አንተው ራስህ በመንገድህ ምራኝ።
ይሄው እጆቼን ያዘኝ እና
እስከወሰንክልኝ የሕይወት ጎዳና
መንፈስ ቅዱስ እለት እለት ሙላኝ
የኔን አስጥለህ የአንተን ብቻ አስታጥቀኝ።
አፍ አለው ይነገር ኑሮዬ
እንዴት እንደመራኸኝ ትላንትናዬ
ሕይወቴን ሰጥቼህ አላፈርኩም
እጆችህ ላይ ምንም ነገር አይበላሽም።
በምንም አትተካም በቤቴ
አንተኮ ዋና ነህ በህይወቴ።
ፈቃድህ ይቅደመኝ እከተላለሁ
እውነት ሆይ አንተ እታመናለ።
ክርስትናዬን ምወደው
የኢየሱስዬን መምጣት ምናፍቀው
በተስፋ እምነት የምፀናው
መንፈስ ቅዱስ ከኔ ጋር ስላለህ ነው
መንፈስ ቅዱስ ሕይወቴ መንፈስ ቅዱስ
መንፈስ ቅዱስ ወዳጄ መንፈስ ቅዱስ
መንፈስ ቅዱስ መሪዬ መንፈስ ቅዱስ
መንፈስ ቅዱስ ፅናቴ መንፈስ ቅዱስ
1.6K ·