Ссылка
click to show
click to show
በኤሌክትሪክ አደጋ ምክንያት ለሚደርስ ጉዳት ተገልጋዮች ከአገልግሎት ሰጪው እውቅና እና ፈቃድ ውጭ በራሳቸው በሚዘረጉት የኤሌክትሪክ መስመር ለሚደርሰው ጉዳት አገልግሎት ሰጪው ተቋም ተጠያቂ አይሆንም።
እንደ ኤሌክትሪክ አደጋ ባሉ የቴክኒክ ጉዳዮች ላይ የአደጋውን መንስኤ ለማወቅ በፖሊስ የሚደረግ የባለሙያ (Forensic) ምርመራ ከፍተኛ የማስረጃነት ዋጋ (High Probative Value) አለው። ይህንን የባለሙያ ምርመራ ውጤት ያለ በቂ ምክንያት ወደ ጎን በማለት ውሳኔ መስጠት መሠረታዊ የሕግ ስህተት ነው።
አገልግሎት ሰጪው ኃላፊነት የሚኖርበት እሱ ራሱ በዘረጋውና ባለቤት በሆነበት መስመር ላይ ለሚደርስ ጉዳት ብቻ ነው። በተገልጋዮች ጥፋት ለሚደርስ አደጋ ተቋሙ ካሣ የመክፈል ግዴታ የለበትም።
የኤሌክትሪክ ኃይል ባለቤት መሆን ብቻውን ኃላፊነትን አያስከትልም፤ ኃላፊነት ሊኖር የሚችለው ተገቢው ጥንቃቄ ካልተደረገ እና ጥፋት ከተፈጸመ ብቻ ነው።
ሰ/መ/ቁ.175142 (ግንቦት 24 ቀን 2012 ዓ.ም)https://t.me/ethiopianlawse
292 ·