ChatCrawlersearch across public Telegram Open the app

ስለ ሕግ እንወያይ

264 members
16 May 2026
I
Ссылка
click to show
በኤሌክትሪክ አደጋ ምክንያት ለሚደርስ ጉዳት ተገልጋዮች ከአገልግሎት ሰጪው እውቅና እና ፈቃድ ውጭ በራሳቸው በሚዘረጉት የኤሌክትሪክ መስመር ለሚደርሰው ጉዳት አገልግሎት ሰጪው ተቋም ተጠያቂ አይሆንም። እንደ ኤሌክትሪክ አደጋ ባሉ የቴክኒክ ጉዳዮች ላይ የአደጋውን መንስኤ ለማወቅ በፖሊስ የሚደረግ የባለሙያ (Forensic) ምርመራ ከፍተኛ የማስረጃነት ዋጋ (High Probative Value) አለው። ይህንን የባለሙያ ምርመራ ውጤት ያለ በቂ ምክንያት ወደ ጎን በማለት ውሳኔ መስጠት መሠረታዊ የሕግ ስህተት ነው። አገልግሎት ሰጪው ኃላፊነት የሚኖርበት እሱ ራሱ በዘረጋውና ባለቤት በሆነበት መስመር ላይ ለሚደርስ ጉዳት ብቻ ነው። በተገልጋዮች ጥፋት ለሚደርስ አደጋ ተቋሙ ካሣ የመክፈል ግዴታ የለበትም። የኤሌክትሪክ ኃይል ባለቤት መሆን ብቻውን ኃላፊነትን አያስከትልም፤ ኃላፊነት ሊኖር የሚችለው ተገቢው ጥንቃቄ ካልተደረገ እና ጥፋት ከተፈጸመ ብቻ ነው። ሰ/መ/ቁ.175142 (ግንቦት 24 ቀን 2012 ዓ.ም)https://t.me/ethiopianlawse
292 ·
20 May 2026
31 May 2026
I
Фотография
click to show
🌍✨ PAN-AFRICANISM AND UBUNTU: BUILDING AFRICAN BROTHERHOOD ✨🌍 Join us for an inspiring day of unity, culture, and meaningful dialogue as we celebrate the spirit of Ubuntu and Pan-Africanism! 🤝🌍 what the event has prepared: 🎤 Engaging Panel Discussions 🎶 Live Music Performances 🎨 Special Guest Artists 📱 Popular TikTok Influencers 🤝 Networking & Interactive Activities 🌍 Conversations on African Identity, Unity, and Progress 👀 Stay tuned to discover our invited guests and special speakers! Where and when? 📅 June 4, 2026 ⏰ 9:00 AM 📍 Ras Mekonen Hall, 6 Killo Main Campus, Addis Ababa University Come connect, learn, celebrate, and be part of a movement dedicated to strengthening African brotherhood and solidarity. #UbuntuUnityClub #PanAfricanism #Ubuntu #AfricanBrotherhood #AAU #UnityInDiversity #AfricaRising
235 ·
3 June 2026
T
We are pleased to announce the Habegar Quiz Competition, which will be aired on EBC (National TV). In partnership with the ProJust Institute of Research Center, the well-known Debebe Hailegebriel Law Office is organizing this academic quiz program for university students. We are inviting 100 Freshman–5th year undergraduate students from public and private universities in Addis Ababa and nearby areas to participate as an audience. The program will be conducted on Tomorrow Thursday ( ሰኔ 27 ) Venue: Abrrhot Library Eligibility 📌 Must be available on 2:30- 6:00 LT on ሰኔ 27 2018 E.C 📌 Must agree to be recorded and appear on TV Benefits 📌 Transport allowance 📌 Opportunity to appear on national television 📌 Opportunity to participate on future competitions For Registration: RSVP. Just send the relevant information on the form https://docs.google.com/forms/d/e/1FAIpQLSdKwZW9BFA_auaBr2VfQWI9DRfhCuBh4Dl-UPY_soLeuBpDtw/viewform?usp=publish-editor YOU ARE ALL INVITED!!!
6 June 2026
I
Фотография
click to show
Фотография
click to show
" ግለሰቡ ሊያመልጥ ሞክሮ ነበር። አሁን ላይ ራሱን አቁስሎ በሆስፒታል ይገኛል " -  የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ አቃቤ ህግ ቢሮ 🔴 " ቤቱ ሲፈተሽ ተጨማሪ አራት ሽጉጦች ተገኝተዋል ! "   በኦሮሚያ ክልል፣ ምዕራብ ሸዋ ዞን ሆለታ ወልመራ ወረዳ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ዳኛን እና ባለቤቱን ችሎት ላይ የገደለ አቅኖ በቀለ የተባለ ተጠርጣሪ ራሱን ካቆሰለ በኋላ በቁጥጥር ስር ውሏል። ችሎት ላይ እያሉ የተገደሉት ዳኛ ወርቄ ፈካንሳ ይባላሉ። የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ አቃቤ ህግ ቢሮ ለሸገር ኤፍ ኤም በሰጠው ቃል ፤ ተጠርጣሪው አልማዝ መኮንን ከተባሉት ባለቤቱ ጋር የነበራቸው የፍቺ ክርክር አልቆ፤ የንብረት ክፍፍል ላይም ውሳኔ ተሰጥቶ ለአፈጻጸም በተያዘ ቀጠሮ ላይ ነው ግድያውን የፈጸመው። ግለሰቡ ከዳኛዋ በተጨማሪ በዚያው ችሎት ላይ አልማዝ መኮንን የተባሉ ባለቤቱንም ገድሏል። ቢሮው " ተጠርጣሪው ግለሰብ ሊያመልጥ ሞክሮ ነበር። አሁን ላይ ራሱን አቁስሎ በሆስፒታል ይገኛል " ሲል ገልጿል። ሰዎች ወደ ፍርድ ቤት ሲገቡ መፈተሽ ያለባቸው ቢሆንም ተጠርጣሪው ግለሰብ ግን #ሽጉጥ እና #ጩቤ ይዞ እንደገባ በኋላ ላይ መታወቁ ተመላክቷል። ቤቱ ሲፈተሽ ተጨማሪ አራት ሽጉጦች ተገኝተዋል። ቢሮው ግለሰቡ እንዴት መሳሪያ ይዞ እንደገባ ለማወቅ ምርመራ መጀመሩ ገልጾ ችሎት የሚያስከብሩ እና የፀጥታ ስራ እንዲሰሩ የተመደቡና ኃላፊነታቸውን በአግባሉ ያልተወጡ ሶስት የፖሊስ አባላት በቁጥጥር ስር እንደዋሉ አሳውቋል። ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የሸገር ኤፍ ኤም ሬድዮ ጣቢያ ነው። ግንቦት 28 ቀን 2018 ዓ/ም @tikvahethiopia
338.3K ·
7 June 2026
I
Case Comment; Yehudit Solomon vs Aynalem Worku File No. 180281   I. Summary of Facts The dispute arise on the inheritance rights claimed by  Woizero Yehudit Solomon, who seeks to inherit the estate of the late Woizero Maseret Welediyab, through her father, whom she alleges is the biological child of the deceased. The applicant claims that her father’s blood relationship with the deceased had been previously acknowledged and documented by a woreda court decision. Based on this, she applied for recognition as a legal heir.However, the respondent, Woizero Aynalem Worku, challenged this claim, asserting that the applicant’s father was never legally or biologically acknowledged as the child of the deceased, and therefore, Yehudit has no legitimate succession rights. This claim led to a chain of litigation across four levels of courts in Oromia and a final review by the Federal Supreme Court Cassation Bench. II. Legal Issues 1. Whether the applicant's father was legally recognized as the biological child of the deceased.or 2. Whether the applicant, as a descendant of the alleged child, qualifies as a rightful heir under Ethiopian succession law. 3. Whether the lower courts committed fundamental legal errors in interpreting the legal relationship between filiation and inheritance. III. Synopsis of Court Judgments Woreda Court (First Instance) of Oromia The woreda court recognized Yehudit’s claim, accepting testimony and documents submitted in support of her father’s filial link to the deceased. It ordered  that Yehudit was entitled to share in the inheritance as a representative heir. Zonal High Court of Oromia The zonal court reversed the woreda court’s decision, emphasizing that the alleged filiation was not substantiated by formal legal documentation such as a birth certificate, court judgment, or official acknowledgment. The court held that inheritance could not proceed without establishing this foundational legal relationship. Regional Appellate Court (Appellate Benc
212 ·
8 June 2026
𝙬
Фотография
click to show
Фотография
click to show
አዲሱ የወንጀል ሥነ-ሥርዓት እና ማስረጃ ሕግ በነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ እስኪወጣ ድረስ ረቂቁን መጠቀም ላይ ጥንቃቄ እንዲኖር የፍትሕ ሚኒስቴር አሳሰበ። የፍትሕ ሚኒስቴር አዲሱ የወንጀል ሥነ-ሥርዓት እና የማስረጃ ሕግ በነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ በይፋ ሥራ ላይ እስኪውል ድረስ፣ በረቂቅ ደረጃ ያሉ ሰነዶችን ለተለያዩ ሙያዊ አገልግሎቶችና ሥልጠናዎች ከመጠቀም እንዲቆጠቡ አሳሰበ። ሚኒስቴሩ ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው፣ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ላለፉት 64 ዓመታት ሲያገለግል የነበረውን የወንጀል ሥነ-ሥርዓት ሕግ በመተካት፣ አዲሱን የወንጀል ሥነ-ሥርዓት እና የማስረጃ ሕግ አዋጅ ቁጥር 1410/2018 መጋቢት 24 ቀን 2018 ዓ.ም ማጽደቁ አስታውሷል። በአሁኑ ወቅት ሕጉን ሙሉ በሙሉ ወደ ተግባር ለማስገባት የሚያስችሉ የመጨረሻ የቃላት ማስተካከያና የሕግ እርማት ሥራዎች (Editorial Works) በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና በፍትሕ ሚኒስቴር አማካኝነት በከፍተኛ ጥንቃቄና ፍጥነት እየተከናወኑ ይገኛሉ ብሏል። ይሁን እንጂ ሕጉ በይፋ ሳይታወጅና ሳይሰራጭ፣ በተለያዩ አካላት ዘንድ በረቂቅ ደረጃ ያሉ ሰነዶችን ለተለያዩ ሙያዊ ተግባራት፣ ለፍትሕ አገልግሎቶችና ለሥልጠናዎች ጥቅም ላይ እየዋሉ መሆኑን መታዘቡን ሚኒስቴሩ ገልጿል። ይህ የመጨረሻው የሕግ እርማት ሥራ ያልተጠናቀቀበትን ሰነድ መጠቀም፣ በአፈጻጸም ላይ የቃላትና የአንቀጾች አለመጣጣምን በመፍጠር በፍትሕ ሥርዓቱ ላይ መደናገር ሊፈጥር እንደሚችል ሚኒስቴሩ አስጠንቅቋል። በመሆኑም ሕጉ በይፋ ታትሞ እስኪወጣ ድረስ ከእንዲህ ዓይነት አጠቃቀሞች ጥንቃቄ እንዲደረግ አሳስቧል። የሕግ እርማት ሥራው ተጠናቆ ሕጉ በነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ ለሕዝብ ተደራሽ ሲሆን፣ በሚኒስቴሩ ድረ-ገጽና በማኅበራዊ ሚዲያ አማራጮች ወዲያውኑ በይፋ እንደሚለቀቅም ተገልጿል። እስከዚያው ግን ሁሉም ባለድርሻ አካላትና የሕግ ባለሙያዎች በትዕግሥት እንዲጠባበቁና አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርጉ ሚኒስቴሩ ጥሪ አቅርቧል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ አዲስ አበባ ሰኔ 1 ቀን 2018 ዓ/ም @tikvahethiopia
19 June 2026
I
7ኛው መፅሐፌ የፍትሐብሔር ፍርድ አፈጻፀም የሚለው ከቀን 12/10/2018 ዓ.ም ጀምሮ በገበያ ላይ ይገኛል፡፡ መፅሐፉ በትልቁ የመፅሐፍ መጠን (በ “B 5”) በ17 ምዕራፎች ተከትቦ በ446 ገፅ ተቀንብቦ ለተደራሲያን እነሆ ጀባ በያለሁኝ፡፡ በዚህ መፅሐፍ ውስጥ የፍርድ ሕይወቱ መፈፀሙ (The life of a decision is an execution) ከሚለው መርህ (“ከሚል መሪ ቃል”) እጅግ በርካታ የሆኑ በፍርድ አፈጻፀም አወዛጋቢ የሆኑ ጉዳዮችን ከሕጉ፣ ከሰበር እና ከፌዴራሽን ምክር ቤት አስገዳጅ የሕግ ትርጉም አንጻር በሰፊው ተዳሰዋል፡፡ መፅሐፉን ልዩ የሚያደረገው ይህ መፅሐፍ ከዚህ ቀደም ለሕትመት ካበቃዎቸው መፅሐፍት የሚለይበት አንድ ቁልፍ ነጥብ አለ፡፡ ይኸውም የፍርድ አፈጻፀም ችግሮችን ለይቶ ለፍርድ አፈጻፀም መሰረት የሚሆነውን ውሳኔ ከሚሰጠው እና ከአፈጻፀም ችሎቱ እስከ ፍርድ አስፈጻሚ አካል እና ለፍርድ አፈጻፀም ባለድርሻ አካላት እስሆኑት ድረስ መፍትሔዎችን ማስቀመጡ ነው፡፡ በመሆኑም መፅሐፉ ችግር ነቃሽ ብቻ ሳይሆን መፍትሔም አቅራቢም ጭምር መሆኑ ነው፡፡
6.2K ·
22 June 2026
27 June 2026
I
"ወዳጀ ሴት ልጅን እንኳን አንተ ፍጡሩ ፈጣሪዋም በስጦታዎቹ አላረካትምና አረካታለሁ ብለህ አትልፋ! ለምሳሌ፦ 👉ፈጣሪ ቆንጆ ጥፍር ሰጥቷት እያለ አልረካ ብላ ሰው ሰራሽ ጥፍር ትደርብበታለች! 👉ቆንጆ ፀጉር ሰጥቶ ፈጥሯት እያለ በፈጣሪው አላረካ ብላ ሂዩማን ሄር ትቀጥልበታለች! 👉እንስሳቱንም አትክልቱንም ብይ ብሎ ፈቅዶላት እያለ ሁሉም አላረካት ብሎ የተከለከለችውን እፀበለስን በላች! 👉ቆንጆ ቅርፅ ሰጥቶ ፈጥሯት እያለ አልረካ ብላ የፕላስቲክ ዳሌ ትደርብበታለች! 👉ቆንጆ ቅንድብ ሰጥቶ ፈጥሯት እያለ አልረካ ብላ በእርሳስ ስትለቀልቀው ታረፍዳለች! 👉ምርጥ ሽፋሽፍት ሰጥቶ ፈጥሯት እያለ ያንሳል ብላ ተጨማሪ ታስተክልበታለች! 👉ምርጥ የሆነ ቆዳ ሰጥቶ ፈጥሯት እያለ አልረካ ብላ ዱቄትና ቅባት ስትደዘድዝበት ትውላለች! 👉ቆንጆ ቁመት ሰጥቶ ፈጥሯት አያለ አልረካ ብላ የበለጠ ለመርዘም ስትል በሂል ጫማ ስትመናቀር ትውላለች! 👉ውብ አፍንጫ ሰጥቶ ፈጥሯት እያለ አልረካ ብላ ሰርጀሪ ታሰራለች! እናም ወዳጄ!… አንተም ምንም ነገር ብትሰጣት አይበቃም ብላ መጨመሯ አይቀርምና ለምን አላረካኃትም ብለህ አትጨነቅ።" _ [ ሮበርት ሙጋቤ ] እኔ አላልኩም 😁😁
359 ·
8 July 2026
I
በህግ አምላክ ይህን የማጨበርበሪያ መልዕክት አንሱልን።
9 July 2026
1 September 2026
14 September 2026
I
Ссылка
click to show
#ቀልድ_መስለው_ነገር_ግን_ወንጀል_የሆኑ_ድርጊቶች ‼️ **** 1. የሰውን ፎቶ/ቪዲዮ መለጠፍ ድርጊቱ፦ መንገድ ላይ ያዩትን ጠብ ወይም አስቂኝ ነገር ያለ ባለቤቱ ፈቃድ ቀርጾ ፌስቡክ ላይ መለጠፍ። ውጤቱ፦ የግል ነፃነትን መጣስ ተብሎ ያስከስሳል። 2. የሀሰት ወሬ ማሰራጨት ድርጊቱ፦ "እውነት ይመስላል" ብለው መረጃን ሳያረጋግጡ "Share" ማድረግ። ውጤቱ፦ ሀ, በሀሰተኛና ጥላቻ ንግግርን         የማሰራጨት ተጠያቂነት ለ,የኮምፒውተር ወንጀል አዋጅን መጣስ እና የሰላም መታወክ ተጠያቂነት። 3. በኮሜንት መሳደብ ድርጊቱ፦ በፖስት ስር ሰዎችን በብሄር፣ በሃይማኖት ወይም በግል ማንነታቸው መስደብ። ውጤቱ፦ የጥላቻ ንግግር እና ስም ማጥፋት ወንጀል። 4. ያለፈቃድ ገንዘብ ማሰባሰብ ድርጊቱ፦ "ለታመመ ሰው እርዳታ" በሚል የባንክ አካውንት እየለጠፉ በሶሻል ሚዲያ ገንዘብ መለመን። ውጤቱ፦ ያለፈቃድ የገንዘብ ማሰባሰብ እና የማጭበርበር ጥርጣሬ። 5. የሰው ዲዛይን መስረቅ ድርጊቱ፦ የሌላ ሰውን ሎጎ ወይም የፈጠራ ስራ "የእኔ ነው" ብሎ መጠቀም። ውጤቱ፦ የቅጂ መብት (Copyright) ጥሰት ክስ። 6. የግል መልዕክትን ማጋራት (Screenshot) ድርጊቱ፦ በ "Inbox" የተላከልዎትን ሚስጥራዊ መልዕክት ያለ ሰውየው ፈቃድ ለሰው እንዲታይ ፖስት ማድረግ። ውጤቱ፦ የግል ሚስጥርን ማባከን (Privacy violation)። ማሳሰቢያ፦ በኢንተርኔት የምንለጥፈው ነገር ሁሉ "ዲጂታል አሻራ" ስላለው በሕግ ፊት ማስረጃ ሆኖ ሊቀርብ ይችላል። https://t.me/ethiopianlawse
91 ·
15 September 2026
I
I
የዳኝነት ክፍያ የማይከፈልባቸው ጉዳዮች ⚖️ በሌሎች ሕጎች የተደነገጉት እንደተጠበቀ ሆኖ ከዚህ በታች በተጠቀሱት ጉዳዮች ላይ የዳኝነት ክፍያ አይከፈልም 🚫💸 1. የቀለብ ክፍያና የልጅ አስተዳደግን አስመልክቶ የሚቀርብ አቤቱታ 👨‍👩‍👧 2. በሴቶች፣ በሕጻናት፣ በእረጋዊያን፣ ኣካል ጉዳተኞችን እንዲሁም ሌሎች ለመብት ጥሰት ተጋላጭ የሆኑ የኀብረተሰብ ክፍሎችን በተመለከተ የሚቀርብ የሕዝብ ጥቅምን ለማስክበር ወይም አካልን ነጻ ለማውጣት እና ሌሎች የወል ሰብዓዊ መብታቸዉን ለማስክበር በሲቪል ማኅበራት አማካይነት የሚቀርብ ክስ፤ 🤝 3. የአካባቢ ጥበቃና እንክብካቤን በሚመለከት የሚቀርቡ ጉዳዮችን፤ 🌱 4. በሕግ አግባብ በድሃ ደንብ እንዲከራከር በፍርድ ቤት የተወሰነለት ሰው 🏛️ 5. በወንጀል ጉዳይ የሚቀርብ ክርክር 🚔 6. አግባብነት ባለዉ ሕግ መሰረት አንድ ሰራተኛ በግሉ በአስተዳደር አካል የተሰጠው ውሳኔ በፍርድ ቤት እንዲከለስለት ለሚያቀርበዉ እቤቱታ 📄
72 ·
17 September 2026
I
Ссылка
click to show
⏳ በሕግ ገደብ (በይርጋ) ፈጽሞ የማይታገዱ እና በማንኛውም ጊዜ ክስ ሊቀርብባቸው የሚችሉ 17 ወሳኝ የሕግ ጉዳዮች! ብዙውን ጊዜ በሕጋችን ውስጥ ይርጋ የሚባል መርህ አለ። ይህም ማለት አንድ ሰው መብቱ ሲነካ በሕግ በተቀመጠለት የተወሰነ የጊዜ ገደብ ውስጥ ክስ ካላቀረበ ጊዜው ካለፈ በኋላ መብቱ በይርጋ ታግዶ ፍርድ ቤት መስተናገድ አይችልም። ይሁን እንጂ ማኅበረሰቡ ሊያውቀው የሚገባ እጅግ አስገራሚ የሕግ እውነታ አለ፤ አንዳንድ ጉዳዮች የፈለገውን ያህል ዓመታት ቢቆጠሩ እንኳ ፈጽሞ በይርጋ አይታገዱም! በማንኛውም ዘመን እና ጊዜ ክስ አቅርቦ መብትን ማስከበር ይቻላል። የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት እና የተለያዩ አዋጆች ፈጽሞ በይርጋ እንደማይታገዱ ጉዳዮች እነሆ፦ • እናት የምታቀርበው የልጅነት መካድ ክስ አንዲት እናት የልጅዋ አባት የተመዘገበው ሰው እውነተኛ አባቱ አለመሆኑን በመግለጽ የምታቀርበው የመካድ ክስ በይርጋ አይታገድም። (📍 ሰ/መ/ቁ 167286፣ መጋቢት 27 ቀን 2011 ዓ.ም) • የድምፅ እና የአካባቢ ብክለት ከአጠገብዎ ካሉ ፋብሪካዎች፣ ጭፈራ ቤቶች ወይም ጎረቤቶች የሚመነጭ ቀጣይነት ያለው የድምፅና የአየር ብክለት ወይም ረብሻን ለማስቆም የሚቀርብ ክስ በማንኛውም ጊዜ ይቻላል። (📍 የፍትሐብሔር ሕግ አንቀጽ 1225፣ ቅጽ 11፣ መ/ቁ 42824) • መመሪያዎች ከሕግ ውጭ መውጣታቸውን መቃወም የተለያዩ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች የሚያወጧቸው መመሪያዎች ከአገሪቱ አዋጆችና ሕጎች ውጭ መሆናቸውን በመቃወም የሚቀርብ የሕግ የበላይነት ክስ በጊዜ አይገደብም። (📍 በአስተዳደር ሥነ-ሥርዓት አዋጅ ቁጥር 1183/2020 አንቀጽ 53 እና ተከታዮቹ) • መፋለም መብት ክስ አንድ ሰው የእውነተኛ ባለቤትነት መብቱን (የቤት ወይም የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ፎርሙን) ይዞ፣ ንብረቱን በሕገ-ወጥ መንገድ ከያዘበት ሰው ላይ ለማስመለስ የሚያቀርበው ክስ የዘመን ገደብ የለውም። (📍 ቅጽ 10፣ መ/ቁ 43600 እና የፌዴሬሽን ምክር ቤት መ/ቁ 67/2011) • በሕግ አግባብ የተጣራ የውርስ ሀብት ክፍፍል ክስ አንድ የውርስ ንብረት በሕጉ በተቀመጠው አግባብ በውርስ አጣሪ ሙሉ በሙሉ ተለይቶና ተጣርቶ ካለቀ በኋላ፣ ወራሾች ድርሻቸውን ለመካፈል የሚያቀርቡት ክስ በማንኛውም ጊዜ ይስተናገዳል። (📍 ቅጽ 10፣ መ/ቁ 38533) • በአደራ የተሰጠ ዕቃን መልሶ የማስመለስ ክስ በውሉ ላይ ግልጽ የጊዜ ገደብ ሳይቀመጥ በአደራ የተቀመጠን ንብረት ወይም ዕቃ ከአደራ ተቀባዩ እጅ በማንኛውም ጊዜ አስከብሮ ለማስመለስ የሚቀርብ ክስ በይርጋ አይታገድም። (📍 ቅጽ 10፣ መ/ቁ 48048) • ቀጣይነት ያለው የውል መጣስ አንድ ወገን በገባው ውል መሠረት መፈጸም ያለበትን ግዴታ በየቀኑ እየጣሰ በቀጠለበት ሁኔታ፣ ድርጊቱን ለማስቆም የሚቀርብ ክስ ድርጊቱ እስካልቆመ ድረስ በይርጋ አይታገድም። (📍 ቅጽ 6፣ መ/ቁ 28686) • ሕገ-ወጥ ውል  ከልማድ፣ ከሞራል ወይም ከሕግ ውጭ የተደረገ ፍጹም ሕገ-ወጥ ውል (ለምሳሌ የሰው አካል ለመሸጥ የተደረገ ውል) ገና ከመነሻው ፈራሽ (Void) ስለሆነ፣ ውድቅነቱን ለማወጅ የሚቀርብ ክስ የጊዜ ገደብ የለውም። (📍 ቅጽ 12፣ መ/ቁ 43226) 🚀 ይህንን እጅግ ወሳኝ የሕግ መረጃ ለወዳጅ ዘመድዎ ያጋሩ (Share)፤ መብታቸውን በማንኛውም ጊዜ ማስከበር እንደሚችሉ ግንዛቤ ይፍጠሩላቸው! መሰል ጠቃሚ የሕግ መረጃዎች በፍጥነት እንዲደርስዎትም ገጻችንን ይከተሉ። https://t.me/ethiopianlawse
46 ·
Архив по месяцам
Open in Telegram Каталог площадок Искать в ChatCrawler

A snapshot of an open public feed from the search index ChatCrawler — “Google for public Telegram”; refreshed as the venue is crawled. Times are UTC.

Public content only, official Telegram API. About · FAQ · What we do not do · Remove a page · Catalog