7ኛው መፅሐፌ
የፍትሐብሔር ፍርድ አፈጻፀም የሚለው
ከቀን 12/10/2018 ዓ.ም ጀምሮ በገበያ ላይ ይገኛል፡፡
መፅሐፉ በትልቁ የመፅሐፍ መጠን (በ “B 5”) በ17 ምዕራፎች ተከትቦ በ446 ገፅ ተቀንብቦ ለተደራሲያን እነሆ ጀባ በያለሁኝ፡፡
በዚህ መፅሐፍ ውስጥ የፍርድ ሕይወቱ መፈፀሙ (The life of a decision is an execution) ከሚለው መርህ (“ከሚል መሪ ቃል”) እጅግ በርካታ የሆኑ በፍርድ አፈጻፀም አወዛጋቢ የሆኑ ጉዳዮችን ከሕጉ፣ ከሰበር እና ከፌዴራሽን ምክር ቤት አስገዳጅ የሕግ ትርጉም አንጻር በሰፊው ተዳሰዋል፡፡
መፅሐፉን ልዩ የሚያደረገው
ይህ መፅሐፍ ከዚህ ቀደም ለሕትመት ካበቃዎቸው መፅሐፍት የሚለይበት አንድ ቁልፍ ነጥብ አለ፡፡ ይኸውም የፍርድ አፈጻፀም ችግሮችን ለይቶ ለፍርድ አፈጻፀም መሰረት የሚሆነውን ውሳኔ ከሚሰጠው እና ከአፈጻፀም ችሎቱ እስከ ፍርድ አስፈጻሚ አካል እና ለፍርድ አፈጻፀም ባለድርሻ አካላት እስሆኑት ድረስ መፍትሔዎችን ማስቀመጡ ነው፡፡ በመሆኑም መፅሐፉ ችግር ነቃሽ ብቻ ሳይሆን መፍትሔም አቅራቢም ጭምር መሆኑ ነው፡፡
6.2K ·