ChatCrawlersearch across public Telegram Open the app

ስለ ሕግ እንወያይ

сообщение · 2026-09-17 11:24 UTC
I
Ссылка
click to show
⏳ በሕግ ገደብ (በይርጋ) ፈጽሞ የማይታገዱ እና በማንኛውም ጊዜ ክስ ሊቀርብባቸው የሚችሉ 17 ወሳኝ የሕግ ጉዳዮች! ብዙውን ጊዜ በሕጋችን ውስጥ ይርጋ የሚባል መርህ አለ። ይህም ማለት አንድ ሰው መብቱ ሲነካ በሕግ በተቀመጠለት የተወሰነ የጊዜ ገደብ ውስጥ ክስ ካላቀረበ ጊዜው ካለፈ በኋላ መብቱ በይርጋ ታግዶ ፍርድ ቤት መስተናገድ አይችልም። ይሁን እንጂ ማኅበረሰቡ ሊያውቀው የሚገባ እጅግ አስገራሚ የሕግ እውነታ አለ፤ አንዳንድ ጉዳዮች የፈለገውን ያህል ዓመታት ቢቆጠሩ እንኳ ፈጽሞ በይርጋ አይታገዱም! በማንኛውም ዘመን እና ጊዜ ክስ አቅርቦ መብትን ማስከበር ይቻላል። የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት እና የተለያዩ አዋጆች ፈጽሞ በይርጋ እንደማይታገዱ ጉዳዮች እነሆ፦ • እናት የምታቀርበው የልጅነት መካድ ክስ አንዲት እናት የልጅዋ አባት የተመዘገበው ሰው እውነተኛ አባቱ አለመሆኑን በመግለጽ የምታቀርበው የመካድ ክስ በይርጋ አይታገድም። (📍 ሰ/መ/ቁ 167286፣ መጋቢት 27 ቀን 2011 ዓ.ም) • የድምፅ እና የአካባቢ ብክለት ከአጠገብዎ ካሉ ፋብሪካዎች፣ ጭፈራ ቤቶች ወይም ጎረቤቶች የሚመነጭ ቀጣይነት ያለው የድምፅና የአየር ብክለት ወይም ረብሻን ለማስቆም የሚቀርብ ክስ በማንኛውም ጊዜ ይቻላል። (📍 የፍትሐብሔር ሕግ አንቀጽ 1225፣ ቅጽ 11፣ መ/ቁ 42824) • መመሪያዎች ከሕግ ውጭ መውጣታቸውን መቃወም የተለያዩ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች የሚያወጧቸው መመሪያዎች ከአገሪቱ አዋጆችና ሕጎች ውጭ መሆናቸውን በመቃወም የሚቀርብ የሕግ የበላይነት ክስ በጊዜ አይገደብም። (📍 በአስተዳደር ሥነ-ሥርዓት አዋጅ ቁጥር 1183/2020 አንቀጽ 53 እና ተከታዮቹ) • መፋለም መብት ክስ አንድ ሰው የእውነተኛ ባለቤትነት መብቱን (የቤት ወይም የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ፎርሙን) ይዞ፣ ንብረቱን በሕገ-ወጥ መንገድ ከያዘበት ሰው ላይ ለማስመለስ የሚያቀርበው ክስ የዘመን ገደብ የለውም። (📍 ቅጽ 10፣ መ/ቁ 43600 እና የፌዴሬሽን ምክር ቤት መ/ቁ 67/2011) • በሕግ አግባብ የተጣራ የውርስ ሀብት ክፍፍል ክስ አንድ የውርስ ንብረት በሕጉ በተቀመጠው አግባብ በውርስ አጣሪ ሙሉ በሙሉ ተለይቶና ተጣርቶ ካለቀ በኋላ፣ ወራሾች ድርሻቸውን ለመካፈል የሚያቀርቡት ክስ በማንኛውም ጊዜ ይስተናገዳል። (📍 ቅጽ 10፣ መ/ቁ 38533) • በአደራ የተሰጠ ዕቃን መልሶ የማስመለስ ክስ በውሉ ላይ ግልጽ የጊዜ ገደብ ሳይቀመጥ በአደራ የተቀመጠን ንብረት ወይም ዕቃ ከአደራ ተቀባዩ እጅ በማንኛውም ጊዜ አስከብሮ ለማስመለስ የሚቀርብ ክስ በይርጋ አይታገድም። (📍 ቅጽ 10፣ መ/ቁ 48048) • ቀጣይነት ያለው የውል መጣስ አንድ ወገን በገባው ውል መሠረት መፈጸም ያለበትን ግዴታ በየቀኑ እየጣሰ በቀጠለበት ሁኔታ፣ ድርጊቱን ለማስቆም የሚቀርብ ክስ ድርጊቱ እስካልቆመ ድረስ በይርጋ አይታገድም። (📍 ቅጽ 6፣ መ/ቁ 28686) • ሕገ-ወጥ ውል  ከልማድ፣ ከሞራል ወይም ከሕግ ውጭ የተደረገ ፍጹም ሕገ-ወጥ ውል (ለምሳሌ የሰው አካል ለመሸጥ የተደረገ ውል) ገና ከመነሻው ፈራሽ (Void) ስለሆነ፣ ውድቅነቱን ለማወጅ የሚቀርብ ክስ የጊዜ ገደብ የለውም። (📍 ቅጽ 12፣ መ/ቁ 43226) 🚀 ይህንን እጅግ ወሳኝ የሕግ መረጃ ለወዳጅ ዘመድዎ ያጋሩ (Share)፤ መብታቸውን በማንኛውም ጊዜ ማስከበር እንደሚችሉ ግንዛቤ ይፍጠሩላቸው! መሰል ጠቃሚ የሕግ መረጃዎች በፍጥነት እንዲደርስዎትም ገጻችንን ይከተሉ። https://t.me/ethiopianlawse
46 ·

Вся лента · оригинал в Telegram

Open in Telegram Каталог площадок Искать в ChatCrawler

A snapshot of an open public feed from the search index ChatCrawler — “Google for public Telegram”; refreshed as the venue is crawled. Times are UTC.

Public content only, official Telegram API. About · FAQ · What we do not do · Remove a page · Catalog