Ссылка
click to show
click to show
#ቀልድ_መስለው_ነገር_ግን_ወንጀል_የሆኑ_ድርጊቶች ‼️
****
1. የሰውን ፎቶ/ቪዲዮ መለጠፍ
ድርጊቱ፦ መንገድ ላይ ያዩትን ጠብ ወይም አስቂኝ ነገር ያለ ባለቤቱ ፈቃድ ቀርጾ ፌስቡክ ላይ መለጠፍ።
ውጤቱ፦ የግል ነፃነትን መጣስ ተብሎ ያስከስሳል።
2. የሀሰት ወሬ ማሰራጨት
ድርጊቱ፦ "እውነት ይመስላል" ብለው መረጃን ሳያረጋግጡ "Share" ማድረግ።
ውጤቱ፦ ሀ, በሀሰተኛና ጥላቻ ንግግርን የማሰራጨት ተጠያቂነት
ለ,የኮምፒውተር ወንጀል አዋጅን መጣስ እና የሰላም መታወክ ተጠያቂነት።
3. በኮሜንት መሳደብ
ድርጊቱ፦ በፖስት ስር ሰዎችን በብሄር፣ በሃይማኖት ወይም በግል ማንነታቸው መስደብ።
ውጤቱ፦ የጥላቻ ንግግር እና ስም ማጥፋት ወንጀል።
4. ያለፈቃድ ገንዘብ ማሰባሰብ
ድርጊቱ፦ "ለታመመ ሰው እርዳታ" በሚል የባንክ አካውንት እየለጠፉ በሶሻል ሚዲያ ገንዘብ መለመን።
ውጤቱ፦ ያለፈቃድ የገንዘብ ማሰባሰብ እና የማጭበርበር ጥርጣሬ።
5. የሰው ዲዛይን መስረቅ
ድርጊቱ፦ የሌላ ሰውን ሎጎ ወይም የፈጠራ ስራ "የእኔ ነው" ብሎ መጠቀም።
ውጤቱ፦ የቅጂ መብት (Copyright) ጥሰት ክስ።
6. የግል መልዕክትን ማጋራት (Screenshot)
ድርጊቱ፦ በ "Inbox" የተላከልዎትን ሚስጥራዊ መልዕክት ያለ ሰውየው ፈቃድ ለሰው እንዲታይ ፖስት ማድረግ።
ውጤቱ፦ የግል ሚስጥርን ማባከን (Privacy violation)።
ማሳሰቢያ፦ በኢንተርኔት የምንለጥፈው ነገር ሁሉ "ዲጂታል አሻራ" ስላለው በሕግ ፊት ማስረጃ ሆኖ ሊቀርብ ይችላል።
https://t.me/ethiopianlawse
91 ·