[[[[[[[ *የዘጠና ዘጠኝ ነገደ መላእክት የምልጃ ፀሎት*]]]]]]]
አቤቱ አምላክ ሆይ በዘጠና ዘጠኝ ነገደ መላእክት የምልጃ ፀሎት አማካይነት በምድራዊ ፀርሐ መቅደስህ የማቀርብልህን ፀሎት በሰማያዊት ጽርሐ ቅድሳትህ ተቀበለኝ።
አቤቱ!ህሱሯን ርኩሳን አጋንንት እኔን ለማስደንገጥና ለማሸበር በተሰበሰቡት ጉባኤ ላይ ዘጠና ዘጠኙ ነገደ መላእክት ደርሰው አፍ አፋቸውን መዘው አስፈሪ የሠረገላ ድምፅ እያሰሙ ለጥፋታቸው ይረባረቡባቸው አሜን።
*ይህም እንደ ቸርነትህ እንጂ እንደ በደሌ አይሁን!!!!*
፩ ፤ *ሰአሉ ለነ*፦ መባርቅትን የተጎናፀፋችሁ ዘጠና ዘጠኝ ነገደ መላእክት ሆይ፤እግዚአብሔር በቸርነቱ ይጠብቀን በረድኤትም ይጎብኘን ዘንድ ለምኑልን ማልዱን አሜን።
፪ ፤ *ሰአሉ ለነ*፦መባርቅትን የተላበሳችሁ ዘጠና ዘጠኝ ነገደ መላእክት ሆይ ፥እሳተ መለኮትን በማህፀኗ ስለ ተሸከመች ስለ እመቤታችን ማርያም በየዕለቱና በሰአቱ ጸሎተ ምህላችንን አሳርጉልን አሜን።
፫ *ሰአሉ ለነ*፦ መባርቅትን የተሸለማችሁ ዘጠና ዘጠኙ ነገደ መላእክት ሆይ እግዚአብሔር ከተቃጣ መአት ከታዘዘ መቅሠፍት ይሰውረን ዘንድ የአምላክ እናቱ የሆነች ስለ እመቤታችን ጸሎታችንን አሳርጉልን አሜን።
፬ *ሰአሉ ለነ*፦ዘጠና ዘጠኙ ነገደ መላእክት ሆይ ጌታ እየሱስን በግእዘ ህፀናት ስለ አሳደጋቸው ስለ ማርያም አግኝቶ ከማጣት ከወዳጅ ጠላት እግዚአብሔር ያድነን ዘንድ ፀሎተ ምህላችንን አሳርጉልን አሜን።
፭ *ሰአሉ ለነ*፦ዘጠና ዘጠኙ ነገደ መላእክት ሆይ ከአልጋ አጣብቆ፥በስቃይ አስጨንቆ ፥ጅማትን ሸምቅቆ ፥ከሚገድል ልዩ በሽታ መንበሩን በሚያጥኑ ስለ ሱራፍኤል ብሎ እግዚአብሔር ይጠብቀን ዘንድ በየእለቱ እና በየሰአቱ ፀሎታችንን አሳርጉልን አሜን።
፮ *ሰአሉ ለነ፦*የእግዚአብሔር የዙፋኑ ተሸካሚ የሆናችሁ አርባዕቱ እንስሳ ሆይ ሰውነትን አመንምኖ መልክአ ገፅ አዝግኖ የአካልን ክፍል አጠቃቅኖ ከሚገድል ኤዱስ ወጌዱስ ከሚባል ፅኑዕ ደዌና ዘመናዊ በሽታ የጌትነቱ አዳራሽ አገልጋዮች ስለሆነ ስምኅላችንን ብሎ እግዚአብሔር ይጠብቀን ዘንድ በየእለቱ እና በየእለቱ ምኅላችንን አሳርጉልን አሜን!!
*ሰአሉ ለነ፦* የእግዚአብሔር መናብርቱ እንስሳውያን አርባዕቱ ሆይ የሰውነትን የአካል አዕጹቅ መልምሎና ቆራርጦ መያዣ መጨበጫ እጅ መሄጃ መርገጫ እግር ከሚያሳጣ ደዌ ሥጋ እግዚአብሔር ያድነን ዘንድ ስለ ሰባቱ ሊቃናት በየእለቱ እና በየሰአቱ ፀሎተ ምህላችንን አሳርጉልን አሜን!!!
*ሰአሉ ለነ፦*ዘጠና ዘጠኙ ነገደ መላእክት ሆይ እስትንፋስን አፍኖ ደምን ዘግቶ በደም ስር ተሰራጭቶ ውስጣዊ አካልን ተቆራኝቶ ከሚኖር ከደዌ ቁራኛ እግዚአብሔር ይሰውረን ዘንድ የጌታችን መፀነሱን እና መወለዱን እያሳሰባችሁ ምኅላችንን አሳርጉልን አሜን።
*ሰአሉ ለነ፦*ዘጠና ዘጠኙ ነገደ መላእክት ሆይ
፤አቋምን ከሚያናጋ፥አንደበትን ከሚዘጋ ፤ነገርን ከሚያዘናጋ፥ልዩ የሰይጣን ተንኮል እግዚአብሔር ይጠብቀን ዘንድ የወልድን ስነ ግዝረቱንና ስመ ጥምቀቱን እያሳሰባችሁ ፀሎተ ምኅላችንን አሳርጉልን አሜን!!
*ሰአሉ ለነ፦*ዘጠና ዘጠኙ ነገደ መላእክት ሆይ ጨጎራን ከሚያኮማትር ፥አንጀትን ከሚያሳርር ፥ናላን ከሚያዞር፥አእምሮን ከሚያደነዝዝ ፥ልዩ በሽታ እግዚአብሔር ያድነን ዘንድ የወልድን ስነ ፆሙን ህገ ትምህርቱን እያሳሰባችሁ ፀሎታችንን ወደ ፈጠሪ አቅርቡልን አሜን!!።
*ሰአሉ ለነ፦*ዘጠና ዘጠኙ ነገደ መላእክት ሆይ አእምሮ አሳጥቶ ከሚያሯርጥ፥ልብስን አስጥሎ ከሚያስፈረጥጥ ከወገን ከዘመድ ከሚያስፈነግጥ፤ልዩ የሰይጣን ወጥመድ እግዚአብሔር ይጠብቀን ዘንድ የወልድን ፀዋትወ መከራውን መገረፉን መገፈፉን እያሳሰባችሁ ፀሎታችንን ከፈጣሪ ፊት አድርሱልን አሜን።
*ሰአሉ ለነ፦*ዘጠና ዘጠኙ ነገደ መላእክት ሆይ በሰይጣናዊ ግፊት ተገፋፍቶ ገደል ከመውደቅ፥ባህር ከመጥለቅ፥በገመድ ከመታነቅ እግዚአብሔር ይጠብቀን ዘንድ የወልዱን ፅፍአተ ገጹን ኲርዓተ ርእሱን (
ፉቱን መፀፋት ፥የራሱን መመታት )እያሳሰባችሁ ፀሎተ መኅላችንን
ቅድመ እግዚአብሔር አድርሱልን አሜን!!።
*ሰአሉ ለነ፦*ዘጠና ዘጠኝ ነገደ መላእክት ሆይ ፥ሰውነትን ከሚያፌዝ አእምሮን ከሚያደነዝዝ ኑሮን ከሚያቆረቁዝ፥አስተሳሰብን ከሚመርዝ ልዩ የጠላት መርዝ እግዚአብሔር ይጠብቀን ዘንድ የወልድን ሥነ ስቅለቱን ግፍዓ ሞቱን እያሳሰባችሁ ልመናችሁንን በስላሴ ዙፋን አቅርቡልን አሜን።
*ሰአሉ ለነ፦*ዘጠና ዘጠኝ ነገደ መላእክት ሆይ ከሰይጣን ርኲስ እስትንፋስ የተነሣ ዓይንን ከሚያስፈጥጥ ጥርስን ከሚያስገጥጥ ፥ወገብን ከሚያጎብጥ ከልዩ መፃጒዓ ደዌ እግዚአብሔር ይጠብቀን ዘንድ የወልድን ክብረ ትንሣኤውን ፥ኃይለ ዕርገቱን እያሳሰባችሁ ጸሎተ ምኅላችንን ከአምላካችን ፊት አድርሱልን አሜን!።
*ሰአሉ ለነ፦*ዘጠና ዘጠኙ ነገዱ መላእክት ሆይ ከልዩ ልዩ ሰይጣናዊ የተንኮል መጥመድ ከኀሰተኛ ፍርድ ለማምለጥ እግዚአብሔር ይረዳን ዘንድ እግዚአብሔር ይረዳን ዘንድ እግዚአብሔር ከመፍጠር ያረፈባት እለት ቀዳሚትንና ብርሃነ ትንሣኤውን የገለጸባት እለተ እሁድን ሁለቱን ሰንበታት እያሳሰባችሁ ምኅላችንን ከአብ ከወልድ ከመንፈስ ቅዱስ የዘፋን አንፃር አድርሱልን አሜን!።
*ሰአሉ ለነ፦*ዘጠና ዘጠኙ ነገደ መላእክት ሆይ ሰላምን ለማግኘት ህይወትን ለመገብየት እግዚአብሔር በቀና ጎዳና ይመራን ዘንድ የወልድን በግርማ መንግስት ዳግም መምጣት እያሳሰባችሁ ችግራችንን ለፈጣሪ አሳውቁልን አሜን!!.።
*ሰአሉ ለነ፦*በልብሰ መባርቅት የተጌጣችሁ ዘጠና ዘጠኙ ነገደ መላእክት ሆይ በሰላም ወጥተን በሰላም እንገባ፥ዘንድ እያሳሰባችሁ እግዚአብሔር ኃጢአታችንን ይቅር እንዲለን በየእለቱ እና በየሰአቱ የምናቀርበውን ፀሎተ ምኅላ ወደ ሰማይ አሳርጉልን አሜን!።
*ሰአሉ ለነ፦*ሁላችሁ ነገደ መላእክት ሆይ በፍፁም ልመና ማልዱልን ልመናችሁ ሐሰት ያልተቀላቀለበት ምቀኝነት የሌለበት እግዚአብሔር ዘንድ ፍፁም ተቀባይነት ያለው ነውና!።
*አቤቱ ፈጣሪዬ ሆይ፦*የማህበረ መላእክትን ሁሉ የምልጃ ፀሎት ተቀብለህ *ኦርቶዶክስ ተዋህዶ የፀሎት እና የንስሐ መርከብን ከጠላት ዲያብሎስ ፈተና* ኢትዮጵያን ከወራሪ ጠላት እኛን ሕዝቦችህንም ከጦርነት ፥ከረኃብና ከመቅሠፍት በሀገርና በመንግሥት በሰው ሕይወትና በንብረት ላይ ከሚደርሰው አሠቃቂና አስጨናቂ ነገር ሁሉ ሠውረን አሜን።