ChatCrawlersearch across public Telegram Open the app
ወ

ወጣትነት እና ክርስትና/Youth and Christianity /

16 849 members
T
ታሪክ ሰሪው መልዕክተኛ ሁላችንም የራሳችን ታሪክ አለን። የብዙዎቻችን ተመሳሳይ ቢሆንም የአንዳንድ ሰዎች ግን ተፅፎ ለሌሎች መማርያ ይሆናል፤ በጥሩም በመጥፎም መንገድ። ዘላለም የሚኖር የለም፤ atleast እዚህ ምድር ላይ። ጥቂት ጊዜ ነው የተሰጠን። ያንዳንዶቻችን ደግሞ ከጥቂቱም ያነሰ ነው። እኔ አንድ ነገር አምናለው ሁላችንም መልዕክተኞች ነን፣ መልዕክቱ ደግሞ አንድ ነው፣ የምናቀርበው ግን በተለያየ መንገድ ነው። ታሪክ ሰሪው መልዕክተኛ ማነው? በመሰረቱ ታሪክ በኗሪው የሚከወን በፈጣሪው ደግሞ የሚቀረፅ የሚሰራ ነው። እኔ ከተወለድኩበት ጊዜ ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ ታሪኬን ኖሬዋለው። እኔ ብቻ ማውቀው፣ ለሌሎች የተገለጠ እና ከሌሎች ጋር በጋራ የኖርኩት(ቤተሰብ፣ ጓደኛ...) ህይወትና ታሪክ አለኝ። ይህ በብዙዎቻችን ህይወት ላይ ያለ ነገር ነው። እድሜ መቁጠር በራሱ ታሪክ ሊሆን ይችላል ግን ታሪክ በዚህ ብቻ የሚያበቃ ነገር አይደለም። ታሪክ ይሰራል። ታሪክ ይሰራል ማለት ምን ማለት ነው? መሰረት፦ በመሰረቱ ታሪክ እኛ control የምናደርገው ነገር አይደለም። control የማናደርገውን ነገር ደግሞ በፈለግነው መንገድ ማስኬድና መስራት አንችልም። የየዕለት ኑሯችን እኛ እንደምንፈልገው ላይሆንልን ይችላል። ተፈጥሮ በራሱ ከኛ አዕምሮ በላይ ነው፤ even የራሳችንን ማንነት control ለማድረግ ትልቅ ተግዳሮት ነው። ታሪክ መስራት ማለት የምንፈልገውን ህይወት መኖርም አይደለም። መኖር እንደማንችል ደግሞ ግልፅ ነው። ስለዚህ ታሪክ መስራት ምንድነው ምን ማለት ነው? ከዛ በፊት ስለእግዚአብሔር አንድ ነገር ልንገራችሁ... 📖መፅሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሔር ቃል ነው። መፅሐፍ ቅዱስ የብዙ ሰዎች ታሪክ ያለበት መልእክት፣ ራእይ፣ ቅኔ፣ ወንጌላት፣ ትንቢት እና የመሳሰሉት ያሉበት መፅሐፍ ነው። ነገር ግን ወጥ መልዕክቱ አንድ ነው። በዚህ ሁሉ ግን እግዚአብሔር ከዘፍጥረት እስከ ራእይ በተለያዩ ሰዎች ታሪክ ውስጥ አንድ ወጥ የፍቅር ታሪክን ተረከ። እግዚአብሔር አይገርምም? የብዙ ሰዎችን ውድቀትና ድል፣ ሞትና ህይወት፣ ክፋትና መልካምነት ገጣጥሞ የሚፈልገውን የራሱን የፍቅር ታሪክ ፃፈ። ምን ልላችሁ ነው እንደ እግዚአብሔር ያለ የለም፤ እንደ እግዚአብሔር ያለ ታሪክ ሰሪም የለም። ጥሩ ጥሩዉን መርጦ ብቻ ሳይሆን በደካማውም፣ በማይችለውም፣ ክፉ በሆነውም፣ በአጥፊውም፣ በጨካኙም፣ በሌባውም፣ ራሱን በማይገዛውም ታሪክ መስራት ይችላል፤ እርሱ እግዚአብሔር ነውና በነገሮች አይገደብም። አንተ ማነህ? አንቺስ ማን ነሽ? ታሪክህ ምንድነው? ታሪክሽ ምንድነው? እንደኔ እድሜ እየቆጠራችሁ ከሆነ እና ህይወት እንደመራችን እየሄድን ከሆነ ትንሽ ተረጋግተን ማሰብ ያለብን ይመስለኛል። አዎ 10ም ይሁን 20፣ 30፣ 40 በየትኛውም እድሜ ውስጥ ብንሆን ያለንበትን ቆም ብለን ማሰቡ አይከፋም። ባለንበት ቦታ እዚህ ምን እየሰራሁ ነው? ለምን ኢትዮጵያ? ለምንስ ተፈጠርኩ? ማለት ተፈጥሯዊ ነው፤ ሁሉም ነገር ምክንያት ስላለው። ምክንያት ካለው ደግሞ ዉጤት አለው፣ ዉጤቱ ደግሞ የምንኖረው የምንሰራው ታሪክ ነው። ሞተን ስንቀበር የህይወት ታሪካችን ይነበባል። ያሳካነው፣ ያካበትነው፣...። አሁን ብንሞት ምንድነው የሚነበብልን??? መሰረት፦ በመሰረቱ ታሪካችን ሁለት ተመልካች አለው። ሰውና እግዚአብሔር ሶስተኛውን ለዛሬ እንለፈው። በሰው አይንና በእግዚአብሔር አይን ታሪካችን ምን ይመስላል?.....ለማሰብ ያክል ነው እንጂ እርግጠኛ ሆነን እንዲህ ነው ማለት አንችልም። ነገር ግን በሰው ፊት ያለንን ህይወትና ከእግዚአብሔር ጋር ያለንን ህብረት ማሰብ በጣም አስፈላጊ ነው
987 ·
ሊ
ለምጠራኝ አንተ #ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ ለምትጠራኝ አንተ እምቢ እንዳልል እኔ ማስተዋልን አድለኝ በሕይወት ዘመኔ መክረህ አስተምረህ ፍቅር የገለፅክልኝ የስማሁትን ቃል ለህይወት አርግልኝ(፪) *** ለምትጠራኝ አንተ ኃጥያቴን በሙሉ ባንተ ፊት ጥያለሁ ለምጠራኝ አንተ በደሌን ክፋቴን እኔ እናዘዛለሁ ለምጠራኝ አንተ የማትዘነጋኝ ነህ በዘመኔ ሁሉ ለምጠራኝ አንተ ማረኝ ይቅር በለኝ ይብቃኝ መበደሉ *** ለምትጠራኝ አንተ ካፍህ የወጣው ቃል ያረሰርሰኛል ለምጠራኝ አንተ ሕግህን አድምጨ ህይወት ሁኖልኛል ለምጠራኝ አንተ እንደ አንበሳ አድብቷል ያ ክፉ ጥላቴ ለምጠራኝ አንተ ከልቤ እንዳይ ነቅለው ጠብቀኝ አባቴ *** ለምትጠራኝ አንተ ወጀብ ቢይልብኝ ቢከብደኝ ፈተና ለምጠራኝ አንተ አምላኬ ያንተ ምክር ትፀናለችና ለምጠራኝ አንተ ጌታውን የጠበቀ ይከብራል ብለሀል ለምጠራኝ አንተ ነቂ የሌለው እምነት ከልቤ ተክለሀል *** የምትጠራኝ አንተ ድምፅህን ስምቼ ልቤ እንዳይከብድብኝ ለምጠራኝ አንተ ያስተማርከኝ ሁሉ ፍርድ እንዳይሆንብኝ ለምጠራኝ አንተ በስጠከኝ ፀጋ እጠነቀቃለሁ ለምጠራኝ አንተ ከቶ እንዳትወስድብኝ በእንባ ደምድሜአለሁ *** የምጠራኝ አንተ እምቢ እንዳልል እኔ ማስተዋል አድለኝ በሕይወት ዘመኔ መክረህ አስተምረህ ፍቅር የገለፅክልኝ የስማሁትን ቃል ለህይወት አርግልኝ(፪) ✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥   ╭══•|❀:✧๑✞✞๑✧❀|:══╮    👇ሼር በማድረግ ለወዳጆ ያጋሩ‼️      📱ሼር // 𝐒𝐇𝐀𝐑𝐄🌐 💚  @yeorthodoxmezmur  💚 💛 @yeorthodoxmezmur   💛 ❤️  @yeorthodoxmezmur  ❤️    ╰══•❀:✧๑✞✞๑✧❀|:══╯ ✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
1.8K ·
𝕰
ክፍለ ትምሕርት አምስት ኦሪት ዘፍጥረት ከምዕራፍ አራት እስከ ስድስት አዳምም ሚስቱን ሔዋንን ዐወቀ ፀነሰችም፥ቃየንንም ወለደች።ርሷም፦ወንድ ልጅ ከእግዚአብሔር አገኘሁ አለች።ደግሞም ወንድሙን አቤል2ን ወለደች።አቤልም በግ ጠባቂ ነበረ ቃየንም ምድርን የሚያርስ ነበረ።ዘፍ 4:1-2 አዳም ሄዋንን አወቃት ማለቱ በዘር በሩካቤ ተገናኛት ማለት እንጂ በአካል ሳያውቃት ኖሮ አሁን አቃት ማለቱ አይደለም። ቃየል:- ማለት ተጋብኦ ማለት ነው። ከአባት ዘር ከእናት ደም የተወለደ ማለት ነው። አንድም:-ቃየል ማለት ጥሪት ማለት ነው አንድም:-ቃየል ማለት መስተገብረ ምድር ማለት ነው።ምድርን አርሶ የሚኖር ስለሆነ።"ወቃየንሰ መስተገብረ ምድር ኮነ"እንዲል። አንድም:-ቃየል ማለት በኩረ ቀታልያን ማለት ነው።የመጀመሪያ ገዳይ ማለት ነው።አቤልን ገድሏልና።"ተንሥአ ቃየን ላዕለ አቤል እኁሁ ወበተሎ" እንዲል። አቤል:- ማለት ደመና ማለት ነው ደመና ተሰብስቦ ዝናብ እንዲሰጥ አቤልም ለእናት ለአባቱ ታዛዥ ቅን አገልጋይ ነበር። አንድም:- አቤል ማለት በግዕ ማለት ነው።አቤል የዋህ ነበርና። አንድም:-አቤል ማለት ኖላዌ አባግዕ ማለት ነው።በጎችን የሚጠብቅ ሲል። "ወኮነ አቤል ኖላዌ አባግዕ" እንዲል። አንድም:-አቤል ማለት በኩረ ቅቱላን ማለት ነው።በመጀመሪያ የተገደለ ማለት ነው።     ምዕራፍ አምስት የትውል ሐረግ #አዳም 230 ዘመን ከኖረ በኋላ ሴትን ወለደ ይላል።ሴትን ወለደ ሲል ቀድሞ ያልወለደ ሆኖ አይደለም በአቤል ምትክ ስለወለደው እንጂ። ከአዳም በኋላ ሴትም ሔኖስን ወለደ አለ ለምን ቢሉ:-በአቤል እንዳይቆጠር አቤል ሞቷል ወቃየነሰ እንዳይቆጠር በእግዚአብሔር ተረግሞ ከአዳም ተለይቶ ለብቻው ሄዷልና በሴት ተቆጠረ።   #የያሬድ ልጅ ሔኖክ የአዳም ሰባተኛ ትውልድ እግዚአብሔርን ማስደሰቱ ተሰወረ እንጂ አንዳችም ሰው አላገኘውም አልሞተምም። "ወፈለሰ እስመ እግዚአብሔር ከበቶ ውስተ ገነት"  ዘፍ 5:24 እንዲል።     #በአቤል ሞት እንዳለ ቢታወቆም በሔኖክ ደግሞ ትንሣኤ መኖሩ ታወቀ ተረዳ። ሔኖክ:-ማለት የታደሰ ማለት ነው።አዳም አትብላ የተባለውን በልቶ ከገነት እንደወጣና ብልየተ ሥጋ(የሥጋ መከራን)እንዳመጣ ሔኖክ ደግሞ ከመብል ተከልክሎ ተሐድሶ ሥጋን (የሥጋን መታደስ) አምጥቷልና።   ቅዳ.ማር 3:4 ሔኖክ ሞትን እንዳያይ በእምነት ተወሰደ፥እግዚአብሔርም ስለ ወሰደው አልተገኘም።ሳይወሰድ እግዚአብሔርን ደስ እንዳሠኘ ተመስክሮለታልና ዕብ 11:5 እንዲል።   ✍ዲ/ን ቴዎድሮስ ሲሳይ   በቀጣይ ምዕራፍ ስድስትን እንመለከታለን። መልካም ቆይታ
2.5K ·
ሁ
Replymessage unavailable
Ehen lij aklw block argut beye group sir eyezore endeh eyale yetaleyaye hasab eyachebebere nw hulum group lay admin kechalk ban argut  ..endeh yemeyacheberu sewch tetenkeku betseb selamachu yibza Ehw belela acc keyero meta eh lij lemin ban ataregutem silemakw nw adminoch ban argut ere ante fetarih fira hay ende beye group sir aykedehm
𝕰
ክፍለ ትምሕርት ስድስት ኦሪት ዘፍጥረት ምዕራፍ ስድስት ስለ ክፉ ሰዎችና ስለ ጥፋት ውኃ የተነገረ ቃል #የሰው ልጆች በምድሪቱ ላይ እየበዙ በሄዱ ቁጥር ኃጢያተቸው እየበዛ መጣ።ይህ ኃጢያትም ከመላእክት ደረጃ ደርሰው የነበሩ ደቂቀ ሴት (የሴት ልጆች) የወደቁበት ኃጢአት ነው። ይኽ ኃጢአት ደቂቀ ቃየል ሲሰሩት ቆይተዋል። #ይህም ኃጢአት ዝሙት ሲሆን ቀን ሳይመርጡ ዘመድ ሳይለዩ እንደ እንሳት ሆነው በዝሙት ኃጢአት ዐይነ ልቡናቸው ታውሮ ነበር ።ከመላእክት ደረጃ ደርሰው ከነበሩት አንዱ ስማዝያስ ከበዓቱ ወጥቶ እነርሱ ተመልክቶ ቢመለሰ የዝሙት መንፈስ አደረበት። በኋላም ለመላእክቱ "ንዑ ንረድ ወንንሣእ አሐተ አሐተ :ኑ እኛምን ከቃየል ልጆች አንዳንድ እንውሰድ ብሎ ቢላቸው የሰይጣን ዝሙት መንፈስ አደረባቸው በኋላም ደቂቀ ሴት ከደብር ቅዱስ ወርደው ከደቂቀ ቃየል ጋር በዝሙት ወደቁ።መዝሙረኛው ዳዊት ሲናገር "ይሔይስ ተሰፍዎ በእግዚአብሔር እምተሰፍዎ በመላእክት : "በመላእክት ተስፋ ከማድረግ በእግዚአብሔር ተስፋ ማድረግ ይበልጣል ዳግመኛ ማዳን በማይችሉ በሰው ልጆች አትታመኑ።" መዝ 117:8 መዝ 145:3 #መላእክት ያላቸው የሴት ልጆች ሲኾኑ የሰው ልጆች ያላቸው ደግሞ የቃየል ልጆች ናቸው። አማልክትም ተብለዋል። መዝ 81:6-8 ዳግመኛም ሔኖክ ደቂቀ ሴትን መላእክት ይላቸዋል። ሔኖክ 5:37-40 መንፈሶቻቸውም ያለው ያለውም በእነርሱ ላይ ያደረውን ርኩስ መንፈስ ነው።መላእክት የተባሉበት ምክንያት ከሰው ተለይተው በደብር ቅዱስ በቅድስና በንጽሕና ይኖሩ ነበርና መላእክት አላቸው እንጂ መላእክት የተባሉ በኢዮር ራማ ኤረር ያሉ ቅዱሳን መላእክትን አይደለም። ደብር ቅዱስንም የንጹሐን መኖሪያ በመሆኑ ሰማያት ብሎ ጠርቶታል።ሔኖክ 2:45 /9:7 ነገር ግን በእነዚሆ ስም ተጠቅሞ መላእክትን ማንቋሸሽ አይገባም።በመላእክት ዘንድ እንኳንስ የረከሰ ዝሙት ቀርቶ መጋባቶ መዋለድ እንደሌለ ይታወቃል። ማቴ 22:30/ማር 12:25 እግዚአብሔርም ሰውን በምድር ላይ በመፍጠሩ ተጸጸተ፥በልቡም ዐዘነ ዘፍ 6:6 #ተጸጸተ ማለቱ እግዚአብሔር እንደ ሰው ልጆች ባላደረኩት ባልሰራሁት ብሎ በባሕሪይው የሚጸጸት አምላክ ሆኖ አይደለም። "እምቅድመ ይፍጥሮ ለአዳም የአምር ግብሮ":አዳምን ከመፍጠሩ አስቀድሞ ስራውን ያውቀዋል።" እንዲል ኪዳን ዘነግህ 2:5 ነገር ግን ተጸጸተ ማለቱ የሰብዓ ትካትን ኃጢአት በደል አይቶ ወደ ንስሓ ሊመልሰው ወዶ አዘነለት ራራለት ሲል ነው።ይህም ይታወቅ ዘንድ ለጻድቅ ኖኅ "ግበር ታቦተ በዘትድኅን":የምትድንባቶ መርከብ ስራ ብሎ አዘዘው።"ዘፍ 6:14 በማለት ንስሐን አዘጋጅቶ ከጥፋቱ ውኃ እንዲድኑ መልእክተን ልኮላቸው ነበር።ሰብዓ ትካት ግን 120 ዘመን ቢሰጣቸው 100 ዘሙተን ጨፍረን በ20 ንስሐ እንገባለን ብለው አሾፉበት ተሳለቁበት በኋላ ኖኅ ተባእት እና አንስት እያደረገ ወደ መርከቡ ከእንሰሳት ከምድር አራዊት እና አእዋፋት ሁሉ መርጦ አስገብቷቸዋል።ይህም ዘራቸው ከምድር እንዳይጠፋ ነበር። #በዚህም ኖኅ የእግዚአብሔር ትዕዛዝ ሰምቶ ሦስት ክፍል ያላትን መርከብ ሰርቷል።መላእክትም ተራድተውታል። "ወገብረ ኖኅ መጥቅዐ እምዕፀወ አክያስያስ :ኖኅ አክያስያስ ከሚባል እንጨት ደወል ሰራ። ይህንንም ደውል ቁመቱን ሁለት ክንድ ከስንዝር ወርዱን አንድ ክንድ ከስንዝር አድርጎ ሰርቶታል።በቀንም ሦስት ጊዜ ይደውለው ነበር በነግህ ለስራ ተነሱ ሲል በቀትር ለምግበ ሥጋ ተሰባሰቡ ሲል በሠርክ በየቦታችሁ ሂዱ ግቡ ለማለት በመጨረሻ ደግሞ መርከቧን ሰርቶ ሲጨርስ ደውሎታል። ለጊዜው ነው እንጂ ፍጻሜው ግን....በቤተ
2.5K ·
ሊ
Видео
click to show
የእግዚአብሔር ቤተሰቦቼ እንደምን አላችሁ የአምላክ ቸርነት የድንግል ማርያም አማላጅነት አይለየን አይለያችው ♥️♥️♥️🙏 :-ጥያቄ ነበረኝ ፍቃደኛ ከሆናችው ልጠይቅ???
ፍ
27💞, የ 21 አማላጂቷ🥰💖ጠይቅ
እሺ እግዚአብሔር ይስጥልን 🙏 ወንድማማች የሆኑ ጓደኛቼ አሉና በቅርብ እናታቸውን በአደገኛ በሽታ ምክንያት በሞት አጡ ስለዚህ እኔ በቻልኩት ያህል አማከርኩኝ እስካሁን ወደራሳቸው ወደቀድመው አልተመለሱም ፤ እባካችሁ ወገኖች ጓደኞቼን ልያጣው ነውና እነሱን እንድያረጋጋ ምክርም ታርክም ብሆን ላኩልን💔💔💔🙏
2
አ
H
"ቃሉ ሕይወትን ይለውጣል፤ መጻሕፍት እምነትን ያጸናሉ።" በቀሲስ ታምራት ውቤ የተጻፉና የተተረጎሙ መንፈሳዊ መጻሕፍት ምረቃ መርሐ ግብር ላይ በመገኘት ለመንፈሳዊ እድገትዎ የሚጠቅሙ መጻሕፍትን ያግኙ። 📅 ቀን፦ ሐምሌ 5፣ 2018 ዓ.ም 🕗 ሰዓት፦ ከቀኑ 8፡00 ጀምሮ 📍 ቦታ፦ ቦሌ መድኃኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን አዳራሽ እርስዎንና ወዳጆችዎን በፍቅር እንጋብዛለን! #ቀሲስታምራትውቤ #ETOC #Sober #መጻሕፍትምረቃ #EpiphaniaTube
H
⛪📝⛪📝⛪📝⛪📝⛪📝⛪ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! ከመጻሕፍት :-📖 "ከራእየ ኒፎን" የተወሰደ የይቅርታ ፏፏቴ የርኅራኄ ባለጠጋ የሆንክ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ! ፊትህን ከእኔ አትመልስ፤ ማረኝ፤ ይቅርም በለኝ ፡፡ ጌታ ሆይ “አላውቅህም አትበለኝ !' ጌታ ሆይ እስከዛሬ የት ነበርክ?' ብለህም አትቆጣብኝ ፡፡ በኃጢአት የቆሸሽሁ ፧ በበደል እንደ ጢስ የጠቆርሁ ፤ ሕግህን በመተላለፍ የበሰበስሁ ፤ ፍቅርህን በመርሳት የተዋረድሁ ፤ በርኵሰት የሸተትሁ፤ በዲያብሎስ ምክር የጠፋሁ ፤ ሰዎች በሚሠሩት አስነዋሪ ሥራም ዋነኛ የሆንኩ የማልጠቅም ትቢያና ጉድፍ ልጅህን አትናቀኝ፤ ከፊትህም አፍሬ አልመለስ ፡፡ መምህሬ ሆይ ! ከእኔ አትራቅ ፤ ራራልኝ ፤ አድነኝም ፡፡ ሰው ወዳጅ ሆይ “አንተ የኃጢአተኛን በንስሐ ከክፉ መንገዱ መመለሱን እንጂ መጥፋቱን እንደማትሻ' አውቃለሁና ተመልሰህ እስክትረዳኝና ምሕረትህን እስካገኝ አላርፍም ፡፡" 📖 ራእየ ኒፎን መጽሐፍ ✍️ በቀሲስ ታምራት ውቤ የተተረጎመ ⛪📝⛪📝⛪📝⛪📝⛪📝⛪
ሊ
ምንም እንኳ በለስም ባታፈራ፥ በወይንም ሐረግ ፍሬ ባይገኝ፥ የወይራ ሥራ ቢጐድል፥ እርሾችም ሰብልን ባይሰጡ፥ በጎች ከበረቱ ቢጠፉ፥ ላሞችም በጋጡ ውስጥ ባይገኙ፥ እኔ ግን በእግዚአብሔር ደስ ይለኛል፣ በመድኃኒቴ አምላክ ሐሤት አደርጋለሁ። ትንቢተ ዕንባቆም 3:17-18
F
🕊[  †  እንኳን ለአጋእዝተ ዓለም ሥላሴ እና ለቅዱሳን አበው አብርሃም: አባ ሲኖዳ እና አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ  †   ] 🕊   †  ሥሉስ ቅዱስ   †   🕊 በአንድነቱ ምንታዌ [ሁለትነት] : በሦስትነቱ ርባዔ [አራትነት] የሌለበት የዘለዓለም አምላክ: የፍጥረታት ሁሉ ፈጣሪ እግዚአብሔር ነው:: አብ : ወልድ : መንፈስ ቅዱስ በስም: በአካል: በግብር ሦስትነት: በባሕርይ: በሕልውናና በፈቃድ አንድነት የጸኑ ናቸው:: በዚህ ጊዜ ተገኙ: በዚህ ጊዜ ያልፋሉ አይባሉም:: መጀመሪያም መጨረሻም እነርሱ ናቸውና:: ርሕሩሐን ናቸውና በእናት ሥርዓት " ቅድስት_ሥላሴ " እንላቸዋለን:: የሚጠላቸው [የማያምንባቸውን] አይጠሉም:: የሚወዳቸውን ግን እጽፍ ድርብ ይወዱታል:: በቤቱም መጥተው ያድራሉ:: ከፍጥረታት ወገን ከእመቤታችን ቀጥሎ የአብርሃምን ያህል በሥላሴ ዘንድ የተወደደ ፍጡር የለም:: አባታችን ቅዱስ አብርሃም የደግነት ሁሉ አባት ነውና በኬብሮን በመምሬ ዛፍ ሥር ሥላሴን ተቀብሎ አስተናግዷል:: ሥላሴ አኀዜ ዓለም [ዓለምን በእጁ የያዘ] ነው:: ነገር ግን በፍቅር ለሚሻው በፍቅር ይመጣል:: አባታችን አብርሃም በ፺፱ [99] ዓመቱ: እናታችን ሣራ በ፹፱ [89] ዓመቷ ሥላሴን በድንኩዋናቸው አስተናገዱ:: አብርሃም እግራቸውን አጠበ:: [ወይ መታደል!] በጀርባውም አዘላቸው:: [ድንቅ አባት!] ምሳቸውንም አቀረበላቸው:: እንደሚበሉ ሆኑለት:: በዚያው ዕለትም የይስሐቅን መወለድ አበሠሩት:: ቅድስት ሣራ ሳቀች:: እንደ ዘንድሮ ወገኖቻችን የማሾፍ አይደለም:: ደስታና ጉጉት የፈጠረው እንጂ:: ሥላሴ "ምንት አስሐቃ ለሣራ በባሕቲታ" ብለው ነበርና በዚህም ምክንያት ነው "ይስሐቅ" የተባለው:: ሥላሴን ያስተናገደች ድንኩዋን [ሐይመት] የድንግል እመቤታችን ማርያም ምሳሌ ናት:: በድንግል ላይ አብ ለአጽንኦ: መንፈስ ቅዱስ ለአንጽሖ: ወልድ በተለየ አካሉ ለሥጋዌ በእርሷ ላይ አርፈዋል / አድረዋልና:: 🕊   †  ታላቁ አባ ሲኖዳ  †   🕊 የባሕታውን ሁሉ አለቃቸው ታላቁ ቅዱስ ሲኖዳ :- ¤ በ፬ [4] ኛው መቶ ክ/ዘመን የተወለደ ¤ በእናቱ ማሕጸን ሳለ መላእክት በሰይፈ እሳት ይጠብቁት የነበረ ¤ የታላቅነት ትንቢት የተነገረለት ¤ ገና ሳይወለድ ሥውራን አበው የሰገዱለት ¤ በሕጻን ሰውነቱ ጾምና ጸሎትን የጀመረ ¤ የልጅነት ቁርስና ምሳውን ለነዳያን ያካፍል የነበረ ¤ በ፱ [9] ዓመቱ ወደ በርሃ የመነነ ¤ የአባ አብጐል ደቀ መዝሙር የሆነ አባት ነው:: ሲመነኩስም በእግዚአብሔር ትእዛዝ የሠለስቱ_ደቂቅ አስኬማ: የኤልያስ ቆብዕ እና የመጥምቁ ዮሐንስ ቅናትን [መታጠቂያ] ከያሉበት መላእክት አምጥተውለት የመነኮሰ ¤ ዓለምን በሙሉ በጸሎቱ ይጠብቅ የነበረ ¤ የግብፅን በርሃ በብርሃን የሞላ ¤ በርካታ ድርሰቶችን የደረሰ ¤ ያለ ማቇረጥ በየቀኑ ከ፻ [100] ዓመታት በላይ ከጌታችን ክርስቶስ ጋር የተነጋገረ ¤ ደመናትን ተጭኖ ይሔድ የነበረና ¤ ያለ ዕረፍት ለ፩፻፲፩ [111] ዓመታት ከ፪ [2] ወራት ፈጣሪውን ያገለገለ አባት ነው:: በዚህም ምክንያት አንድ ቀን ገዳማውያን ሁሉ እየሰሙ እንዲህ የሚል ቃል ከሰማይ መጣ:: "ሲኖዳ ተሠይመ አርሲመትሪዳ "[ሲኖዳ አርሲመትሪዳ ሆኗል:: ማለትም ለባሕታውያን ሁሉ አለቃ ሁኖ ተመርጧል ማለት ነው::] ቅዱሱ የጌታችንን እግር እያጠበም ይጠጣ ነበር:: በዚህች ዕለት በ፩፻፳ [120] ዓመቱ ጌታችን ወርዶ ሲያሳርገው አቡነ ኪሮስ "ታላቅ ምሰሶ [ታላቅ ዛፍ] ወደቀ" ብለው አልቅሰዋል:: ሲኖዳ ማለት "ደግ ሰው" ማለት ነው:: 🕊   † አባ_ጊዮርጊስ_ዘጋስጫ  †  🕊 
F
ስራ የማስገባት እና የማስቀጠር አቅሙ ያላቹ የእግዚአብሔር አምላክ ቤተሰቦች አግዙኝ በድንግል ማርያም ስም ተባበሩኝ 🙏
"
online ስራ የምትፈልጉ አናግሩኝ በአፕ ነው የሚሰራው የ invitation ስራ ነው
Archive by month
Open in Telegram Каталог площадок Искать в ChatCrawler

A snapshot of an open public feed from the search index ChatCrawler — “Google for public Telegram”; refreshed as the venue is crawled. Times are UTC.

Public content only, official Telegram API. About · FAQ · What we do not do · Remove a page · Catalog