M
22 August 2026
I
Аудио
Lante ayikebdhm .mp3 · 11.7 MB · click to show Аудио
Negus eko new .mp3 · 6.9 MB · click to show Аудио
Yetnsaew ken .mp3 · 9.4 MB · click to show 346 · 23 August 2026
(ትንቢተ ሕዝቅኤል ምዕራፍ 37)
----------
7፤ እንዳዘዘኝም ትንቢት ተናገርሁ፤ ስናገርም ድምፅ ሆነ፥ እነሆም፥ መናወጥ ሆነ፥ አጥንቶችም አጥንት ከአጥንት ጋር ተቀራረቡ።
8፤ እኔም አየሁ፥ እነሆም፥ ጅማት ነበረባቸው ሥጋም ወጣ ቁርበትም በላያቸው ተዘረጋ፥ ትንፋሽ ግን አልነበረባቸውም።
9፤ እርሱም። የሰው ልጅ ሆይ፥ ትንቢት ተናገር፥ ለነፋስ ትንቢት ተናገር፥ ለነፋስም። ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል። ነፋስ ሆይ፥ ከአራቱ ነፋሳት ዘንድ ና፥ እነዚህም የተገደሉት በሕይወት ይኖሩ ዘንድ እፍ በልባቸው በል አለኝ።
10፤ እንዳዘዘኝም ትንቢት ተናገርሁ፥ ትንፋሽም ገባባቸው ሕያዋንም ሆኑ፥ እጅግም ታላቅ ሠራዊት ሆነው በእግራቸው ቆሙ።
@matalapochurch2 244 · (ወደ ቆላስይስ ሰዎች ምዕራፍ 2)
----------
2፤ ልባቸው እንዲጸናና፥ በፍቅርም ተባብረው በማስተዋል ወደሚገኝበት ወደ መረዳት ባለ ጠግነት ሁሉ እንዲደርሱ የእግዚአብሔርንም ምሥጢር እርሱንም ክርስቶስን እንዲያውቁ እጋደላለሁ።
3፤ የተሰወረ የጥበብና የእውቀት መዝገብ ሁሉ በእርሱ ነውና።
4፤ ማንም በሚያባብል ቃል እንዳያስታችሁ ይህን እላለሁ።
5፤ በሥጋ ምንም እንኳ ብርቅ፥ በመንፈስ ከእናንተ ጋር ነኝና፥ ሥርዓታችሁንም በክርስቶስም ያለውን የእምነታችሁን ጽናት እያየሁ ደስ ይለኛል።
6፤ እንግዲህ ጌታን ክርስቶስ ኢየሱስን እንደ ተቀበላችሁት በእርሱ ተመላለሱ።
7፤ ሥር ሰዳችሁ በእርሱ ታነጹ፥ እንደ ተማራችሁም በሃይማኖት ጽኑ፥ ምስጋናም ይብዛላችሁ።
8፤ እንደ ክርስቶስ ትምህርት ሳይሆን፥ እንደ ሰው ወግና እንደ ዓለማዊ እንደ መጀመሪያ ትምህርት ባለ በፍልስፍና በከንቱም መታለል ማንም እንዳይማርካችሁ ተጠበቁ።
9፤ በእርሱ የመለኮት ሙላት ሁሉ በሰውነት ተገልጦ ይኖራልና።
@matalapochurch2 250 · (ወደ ቆላስይስ ሰዎች ምዕራፍ 2)
----------
10፤ ለአለቅነትና ለሥልጣንም ሁሉ ራስ በሆነ በእርሱ ሆናችሁ ተሞልታችኋል።
11፤ የሥጋንም ሰውነት በመገፈፍ፥ በክርስቶስ መገረዝ፥ በእጅ ባልተደረገ መገረዝ በእርሱ ሆናችሁ ደግሞ ተገረዛችሁ።
12፤ በጥምቀትም ከእርሱ ጋር ተቀብራችሁ፥ በጥምቀት ደግሞ፥ ከሙታን ባስነሣው በእግዚአብሔር አሠራር በማመናችሁ፥ ከእርሱ ጋር ተነሣችሁ።
13፤ እናንተም በበደላችሁና ሥጋችሁን ባለመገረዝ ሙታን በሆናችሁ ጊዜ፥ ከእርሱ ጋር ሕይወትን ሰጣችሁ። በደላችሁን ሁሉ ይቅር አላችሁ።
14፤ በእኛ ላይ የነበረውን የሚቃወመንንም በትእዛዛት የተጻፈውን የዕዳ ጽሕፈት ደመሰሰው። እርሱንም በመስቀል ጠርቆ ከመንገድ አስወግዶታል።
@matalapochurch2 259 · I
(ወደ ቆላስይስ ሰዎች ምዕራፍ 2)
----------
2፤ ልባቸው እንዲጸናና፥ በፍቅርም ተባብረው በማስተዋል ወደሚገኝበት ወደ መረዳት ባለ ጠግነት ሁሉ እንዲደርሱ የእግዚአብሔርንም ምሥጢር እርሱንም ክርስቶስን እንዲያውቁ እጋደላለሁ።
3፤ የተሰወረ የጥበብና የእውቀት መዝገብ ሁሉ በእርሱ ነውና።
4፤ ማንም በሚያባብል ቃል እንዳያስታችሁ ይህን እላለሁ።
5፤ በሥጋ ምንም እንኳ ብርቅ፥ በመንፈስ ከእናንተ ጋር ነኝና፥ ሥርዓታችሁንም በክርስቶስም ያለውን የእምነታችሁን ጽናት እያየሁ ደስ ይለኛል።
6፤ እንግዲህ ጌታን ክርስቶስ ኢየሱስን እንደ ተቀበላችሁት በእርሱ ተመላለሱ።
7፤ ሥር ሰዳችሁ በእርሱ ታነጹ፥ እንደ ተማራችሁም በሃይማኖት ጽኑ፥ ምስጋናም ይብዛላችሁ።
8፤ እንደ ክርስቶስ ትምህርት ሳይሆን፥ እንደ ሰው ወግና እንደ ዓለማዊ እንደ መጀመሪያ ትምህርት ባለ በፍልስፍና በከንቱም መታለል ማንም እንዳይማርካችሁ ተጠበቁ።
9፤ በእርሱ የመለኮት ሙላት ሁሉ በሰውነት ተገልጦ ይኖራልና።
@matalapochurch2 271 · 24 August 2026
I
Аудио
ከተጠጋሁት_በላይ_ዙፋንህ_ስሪ_እንድደርስ_1.mp3 · 14.1 MB · click to show የሐዋሳ መዘምራን ልዩ ዝማሬ (በምድር
የሚያስቀረኝ ይቅር)
ካወኩህ በላይ ከተረዳሁ በላይ
እንድትገባኝ እንዳውቅ መንፈስህ ይምጣልኝ
ከተጠጋሁት በላይ ዙፋን ስር እንድደርስ
ከኖርኩትም አስበልጨ ሀሳብህን እንድኖር
ከትናንቱም ይልቅ እንድቀርብህ በይበልጥ
ምኞቴ ነው መሻቴ ወደ ሙላት እንድደርስ
በምድር የሚያስቀረኝ ይቅር
እስክትመጣ ድረስ ልጠንክር
ማደገ በሁሉ እንድገለጥ
መንፈስህ [ጸጋ] እለት እለት ይጨምር
1| መንግስትህን የሚያስናፍቅ ከኖርኩት በላይ የሚያስሮጥ
የኅለኛው ዝናብ ይውረድ ይምጣ በእኔም ላይ
የሚያንሳፈኝ ያለመድኩት ወደ አንተ የሚያደርስ
በእጥፍ ይውረድልን አንተ አንተን የምያሰኝኝ
ከጥማቴ እንድረካ ከርሀቤ እንድታጠግበኝ
ፈልጋለው ኢየሱሴ እንዳይቆም አንተን ማለት
በምድር የሚያስቀረኝ...
2| ወንጌል እንዲደርስ ፍጥረት ሁሉም እንዲድን እንድተርፍ
የመጨረሻውን ስራ እንድትሰራ በሀይልህ
ማራናታ እንዲሆን ቀጠሮአችን እንዲደርስ
በክብርህ በግርማህ በአይኖችህ እንዳይህ
በምድር የሚያስቀረኝ...
ከጥማቴ እንድረካ...
3| እስከዛሬ መጥቻለው አሁን ላይ ደርሸአለው
አግዘኸኝ ኤረድተኸች ፍትህ ቆሚያአለው
የነገዬን እኔ አላውቅም ሀደራ እልሀለው
ናፍቆቴን እስካገኝ ፊትህ እስካይ
ለቀረኝ ጉዞ ሀይልህ ያስፈልገኛል ኢየሱስ
ቀኑን ሙሉ አብሮ የሚያውል ለአፍታ
እንኳን ሳይለይ
ፈልጋለው መንፈስህ ዛሬም አለ የኔ ጥማት
በሀይልህ ተሞልቸ እንድኖር ለፈቃድህ
@matalapochurch2 281 · 26 August 2026
Аудио
ምስጋናውን አወራለው.mp3 · 15.2 MB · click to show መዝሙር
ምስጋናውን አወራለሁ
"ዘምሩ፥ ለአምላካችን ዘምሩ፤ ዘምሩ፥ ለንጉሣችን ዘምሩ። እግዚአብሔር ለምድር ሁሉ ንጉሥ ነውና፤ በማስተዋል ዘምሩ።" (መዝ 47፥6)
ምስጋናውን አወራለው ስለበዛልኝ ምህረት
አንስቶ ስለተሸከመኝ በቀደሙትም ዘመናት
ዝም አልልም በህይወቴ በጎነቱ እየጨመረ
አለኝ ለክብሩ አዲስ ቅኔ አዲስ ዝማሬ ያማረ
መዘመር *2 ሁል ጊዜ ደስ እያለኝ
የኢየሱስ ፍቅሩ እየታየኝ
የአምላኬ ምህረት ትዝ እያለኝ
1 በምድረ በዳ ጥም ባለበት
ሆነኝ ኢየሱስ ምንጭ የህይወት
ደስታዬ በዛ ረክቶ ጥሜ
ስሙን ላክብር ደጋግሜ
በብዙ እረዳኝ ምህረቱ
ቆሜአለው በድል በፊቱ
ስለእርሱ አለኝ የሚወራ
ታላቅ አድርጉት ከእኔ ጋራ
ምህረት የበዛልኝ የተሸከመኝ እኔ ነኝ
በብዙ የረዳኝ የአምላኬን በጎነት ያየሁኝ
ስለዚህ ብዙ ክብር አለኝ
ለኢየሱስ ብዙ ክብር አለኝ
ለእርሱማ ብዙ ክብር አለኝ
ብዙ ክብር አለኝ
2 በጩህቴ ድምፅ እየራራ
ቀኙ አበረታኝ እንዳልፈራ
እንቅፋቱንም አሰወግዶ
በድንቅ መራኝ የሱስ ወዶ
መታመኛ ለደህንነቴ
እሱ ነው ኢየሱስ መድሀኒቴ
ፅኑ አለት የማያስፈራ
አለኝ ለስሙ ብዙ ክብር
3 በፍቅሩ ብዛት ተቤዠኝ
ርህራሄው በዛልኝ
በጭንቄ እርሱ ተጨነቀ
እፉን ከእኔ እያራቀ
በምህረቱ ጥላ ስር
አሳድሮኛል በክብር
በጎነቱን ቆሜ አስባለው
ድንቅ ስራው ዘምራለሁ
@matalapochurch2 236 · I
Аудио
አድስ ቅኔን አመጣለሁ BHU (1).mp3 · 5.6 MB · click to show አድስ ቅኔን አመጣለሁ
ለኢየሱሴ ሰዋለታለሁ
ተቀበል እንካ የእኔን ምስጋና
ተቀበል እንካ የእኔን እልልታ
ተቀበል እንካ የእኔን ዝማሬ
የሚገባውን የአፌን ፍሬ
፩. ምላስ ከንፈሮቼ ያመሰግናሉ
ልዑልን በዜማ ያገለግላሉ
ክብሬ ነህ እያሉ ኦሆሆ
እግዚአብሔርን ሁልጊዜ እባርካለሁ ሁልጊዜ ሁለ
ኢየሱሴን ሁልጊዜ እባርካለሁ ሁልጊዜ ሁለ
ምስጋናን መሰዋት አገልግሎቴ ነው
ምስጋና ላንተ ይገባሃል
ክብር _ ላንተ ይገባሃል
እልልታ ላንተ ይገባሃል
ስለሆንከው ከሁሉ በላይ
፪.ክብሬ ነው ዝማሬ ላንተ እዘምራለሁ
እድሉን አግንቼ እንዴት ዝም እላለሁ አመሰግናለሁ
ለእርሱ ምሰጠው የሚመጥነው ባጣ
ለእርሱ ምሆነውን ባጣ
ምስጋና በልቤ ሞልቷል ይፈስላታል
እልልታ በውስጤ ሞልቷል ይፈስላታል
♡ ㅤ ⎙ㅤ ⌲ ✉️
ˡᶦᵏᵉ ˢᵃᵛᵉ
@matalapochurch2 255 · 27 August 2026
Аудио
ልዩ ነዉ ፍቅርህ.mp3 · 8.8 MB · click to show ዋና የሆንኩኝ ኃጢአተኛ
ድካሜ ከሰው ሁሉ የበረታ
ጥፋቴ ገኖ ነፍሴን ለሞት ያስገዛ
ለዚህ ሁሉ ስርየት አገኘሁ ባንተ ጌታ
ላረክልኝ ልከፍል አስቤ
አጣሁልህ ፈላልጌ
ምን ልስጥህ ምን ልክፈልህ
ፍቅርህ ኢየሱስ ውስጤን ሞልቷል
ምን ልስጥህ ምን ልክፈልህ
ፍቅርህ ጌታ ማርኮኛል
ክንደ ብርቱ ሆነህ ሳለህ
ወርደህ ደቀቅህ ለእኔ ብለህ
እድሜ ዘመኔን ላንተ ብገዛ
አልከፍለውም ያንተን ውለታ
ዘመኔን በሙሉ ላንተ ብገዛ
ልከፍል አልችልም ያንተን ውለታ
ክብርህን የተውከው ለእኔ ለደካማ
ገና ከፍጥረቴ ሳለው ኃጢአተኛ
በደም ቃልኪዳንህ ልጅ አረከኝና
የፍቅርህን ጥግ አየሁ በመስቀልህ ስራ
ምን አይነት ፍቅር ነው
ምን አይነት መውደድ
ለእኔ ያሳየኸው ለእኔ የከፈልከው
በመስቀል ላይ ደክመሀል
ልዩ ነው ፍቅርህ ልዩ ነው
ድንቅ ነው ኢየሱስ ለእኔ ያረከው
ግሩም ነው ፍቅርህ ግሩም ነው
ድንቅ ነው ኢየሱስ ለእኔ ያረከው
እወድድሃለሁ ወድጄሃለሁ ፍቅርህ
ኢየሱስ የእውነት ነው
እወድድሃለሁ እገዛልሀለው
እድሜ ዘመኔን ሰጥቼሀለሁ
@matalapochurch2 198 · I
Аудио
Apostolic_songs_%E1%8B%B0%E1%88%98%E1%8A%93%E1%8B%8D_%E1%8B% · 11.1 MB · click to show ካደረከኝ ስራህን ዘማሪ
ካደረከኝ የአንተን ፍቅር አውሪ
ካደረከኝ ምህረትን ዘማሪ
ካደረከኝ የአንተን ስራ አውሪ
በገናን ይዤ በዜማ ቃል
ስለ አንተ ላውራ ስምህን ልግለጥ
ከዘላለም ሞት እንዳዳንከኝ
ቅኔ ይመስክር ይንገርልኝ
1በአህዛብ መካከል አደራረግህ
ለሰው ልጅ ያለህ ታላቅ ፍቅርህ
ከመታወቅም በላይ በሚያልፈው
እንዴት ባለ ፍቅር እንደወደድከው
ብቻህን አምላክ አንተ እንደሆንክ
ዜማዬ ቃልህን በግልፅ ይስበክ
ብቻህን አዳኝ አንተ እንደሆንክ
ዜማዬ ቃልህን በግልፅ ይስበክ
2 የምትታገስ ነፍስ እንዳይጠፋ
የፍጥረት ሁሉ ብቸኛ ተስፋ
ከአንተ በቀር ጌታ እንደሌለ
በስምህ ልሳን ስርየት እንዳለ
በዝማርዬ እንድነግረው
አሁንም ሀይልን እጠማለሁ
ይውረድ ያ ክብርህ *2
በገናዬን ይዤ ስቆም በፊትህ
ይውረድ ያ ክብርህ
ይምጣ ያ ሀይልህ *2
እውነቱን ስነግር ስዘምርልህ
ይምጣ ያ ሀይልህ
መቆም ማገልገል እስኪሳነኝ
ከቀድሞ ይልቅ ክብርህ ይንካኝ
ደመናው ወርዶ ቤትህን ይሙላ
እኔም ልዘምር ስለአንተ ላውራ
ከሰልፉ በፊት ቀድሜ ምህረትን ካዘመርከኝ
ጠላት ቂመኛን ለማጥፋት ምስጋናን ካኖርክብኝ
ሀሴት እያደረኩ በደስታ ለክብርህ እዘምራለሁ
የከበረ ምስራቹን በዜማዬ አውጃለሁ
"""""ይውረድ ያ ክብርህ"""""""
@matalapochurch2 203 · 28 August 2026
Аудио
ስለእኔ ምን ትላለህ.mp3 · 20.7 MB · click to show 😭😭😭😭😭😭😭
አሁን ብትመጣ ወደ አንተ ልትወስደኝ
ከሆንኩኝ በሰማይ የምትቀበለኝ
በቃልህ ብርሃን ልቤን ስትመረምረው
እውነተኛ ንፁህ ሆኖ ካገኘኸው
አንተን ደስ ካለህ ህይወቴን ስታየው
ይሄ ነው መሻቴ ምን እፈልጋለሁ
ሰው ብቻ ነው ወይስ አንተም
የምትለኝ ጻድቅ ፍፁም
ሽንገላ ነው ወይስ ህይወት
በልቤ ውስጥ ይኑር እውነት
ኢየሱስ አንተስ ለኔ መልስ አለህ ወይ
ጠላቴ ሲከሰኝ ትነግረዋለህ ወይ
ቅን ናት ቅን ነው
ፍፁም ናት ፍፁም ነው
ጻድቅ ናት ጻድቅ ነው ትላለህ ወይ
በአንደበቴ ከምናገረው
በአደባባይ ላይ ከማሳያው
የልቤ ሀሳብ የተሰወረው
የጓዳ ኑሮዬ አንተ ምታየው
ደስ ያሰኝሃል ወይ ስትመዝነው
ቃልህ ነው ሚዛኔ የምለካበት
አንተ ነው የማየው እንደመስታወት
የሚለይ ነገሬን በፀጋህ እየጣልኩት
ፈፅሜ ልመስልህ የምተጋው በህይወት
የእምነቴ ራስና ፈፃሚ ህይወቴ ኢየሱስ አንተ ነህ
ፍለጋህን ዘውትር ልከተል ክብርህ ከራቀኝ ምን አለኝ
አይተካውም ምንም ነገር መንፈስህ በውስጤ ይኑር
ብቻህን ፀንተህ ንገስበት ይህ ልቤ ዙፋንህ ይሁን
ልቤን እንካ ጌታ ሆይ ልቤን እንካ
ልቤን እንካ ኢየሱስ ሆይ ልቤን እንካ
ልቤን እንካ ጌታ ሆይ ልቤን ያዘው
በዘመኔ ሁሉ ያዘው
ከማውቀውም በላይ ጥልቅ ነው
አንተ ነህ የምትመረምረው
የህይወት መውጫ የሆነውን
አባቴ ሰጠውህ ልቤን
ካንተ ሌላ እንዳልል በዘመኔ ሁሉ
@matalapochurch2 202 · I
Аудио
ኢየሱስ መጣ.mp3 · 12.3 MB · click to show 😭😭😢😭😭
ለብዙ ዘመን በህመም ተይዤ
ቀንበር ተጭኖኝ አቅም አጥቼ
እየሱስ መጣ ህመሜን ፈወሰው
ኢየሱስ መጣ ቀንበሬን ሰበረው
ኢየሱስ መጣ ሸክሜን አነሳው
ኢየሱስ መጣ እስርቴን ፈታው
ነቀፌታዬን ችግሬን እየሱስ አንስቷል
የሞተው ነገሬ ደግሞ ህይወት ዘርቷል
ስሜንም ቀይሮ ለክብር አድርጎታል
ወጥመድንም ሰብሮ በድል አቁሞኛል
ማዕበል ወጀቡ እጅጉን ሲበረታ
ለመውደቅ ስስገመገም የሱስ እጁን ዘረጋ
በስልጣንም ቃሉ ማዕበሉ ፀጥ አለ
ተራምዶ በወጀቡ እግሬንም አፀና
የሚረዳኝ የለም ከእኔ አትራቅ ብዬ ተማፀንኩት
ጭንቀት ስትቀርበኝ አጥብቄ ጠራሁት
ጩህቴንም ሰምቶ ዘንበልም አለልኝ
በበረታች ክንዱ አምላኬ ታደገኝ
@matalapochurch2 222 · 29 August 2026
Аудио
እፈልግሃለሁ እህት ታድን እንግዳ.mp3 · 10.5 MB · click to show ጠዋት በማለዳ እፈልግሃለሁ
በቀትሩ ጊዜ እፈልግሃለሁ
ሲመሽም ሲጨልም አንተን በልቤ
ፈፅሞ አልረሳህም ለሊት በሃሳቤ
እፈልግሃለሁ 2*
እወድሃለሁ
አቅም ብርታቴ
ችሎታ ጉልበቴ
ጥበብ እውቀቴ
የሱስ ማስተዋሌ
እፈልግሃለሁ 2*
እወድሃለሁ
የሱስ የሱስ ይላል ልቤ
አንተ ንጉስ ነህ የልቤ
ከብረህ ያለኸው በሕይወቴ ላይ
መተኪያ የለህ በምድር በሰማይ
እፈልግሃለሁ 2*
እወድሃለሁ
ነገር ሲሞላ ሲሳካልኝ
አንተ ነህ የምትናፍቀኝ
የሚታይ ሳይኖር ሲጎልብኝ
የሱስ የሱስ እላለሁኝ
ጠዋት በማለዳ እፈልግሃለሁ
በቀትሩ ጊዜ እፈልግሃለሁ
ሲመሽም ሲጨልም አንተን በልቤ
ፈፅሞ አልረሳህም ለሊት በሃሳቤ
እፈልግሃለሁ 2*
እወድሃለሁ
የዘላለሜ ነህ የዘለአለሜ 2*
የሕይወቴ መጀመሪያ
አንተ ነህ የኔ መደምደሚያ 2*
@matalapochurch2 177 · I
Аудио
ላመስግንህ በዜማ (1).mp3 · 13.4 MB · click to show 😱😭😱FORMER UNION OF MARANATHA CHOIR - HOSSANA 2026
😱 ድንቅ መዝሙር 🙊🙊
የቀድሞ_የማራናታ_ህብረት_መዘምራን
ዝማሬ ላመስግንህ_በዜማ
ጊዜ እያለፈ ዘመን አስቆጠርኩ
ኢየሱስ ምህረት አረዳኝ አቆመኝ |2×
የመከርከኝ የረዳኸኝ አለው ያልከኝ
ዛሬ ሳስተውል ብዙ ውለታ ትዝ እያለኝ |2×
ላመስግን በዜማ ድምፅን ኢየሱስ ላሰማ
ከልቤ ነው ውዳሴ ኤረዳሄኝ ኢየሱሴ {ንጉሴ} |2×
ሳልቆጥብ ሳላሳንስ እባርክሃለሁ ተባረክ
ሳልቆጥብ ሳላሳንስ አከብሪሃለው ኢየሱስ ክበር
ተባረክ የእኔ ጌታ ተባረክ መድኃኒቴ
ተባረክ የእኔ ኢየሱስ ተባረክ መድኃኒቴ
ከልጅነቴ ይሄው እስከዛሬ
እጅን ይዘሄው ነበረ ጉዞዬን
ግሩም መምህር ነህ አስተምረኸኛል
እጆችህ አፍርሰው ሠራርቶልኛል
🎶...ኣሀ ሀ ሀ ሀ...🎶 ልቀደስልህ
ኢየሱስ አንተን ብቻ ላምልክህ
🎶...ኣሀ ሀ ሀ ሀ...🎶 በምንም ሁነታ
ፍትህ ቀሪቤ ልስገድልህ ጌታ
ሳልቆጥብ ሳላሳንስ...
የሞትኩለት ካንተ አስበልጨ
ባገኝ እያልኩት እጅጉን ጓጓቼ
ሙሉ ደስታ አይሆንም የዝአለም ነገር
አይበጀኝ ለህይወቴ ስጠኝ እግዚአብሔር
🎶...ኣሀ ሀ ሀ ሀ...🎶 ሕሳብ አላሰላም
🎶...ኣሀ ሀ ሀ ሀ...🎶 እምነቴም አይጎልም
🎶...ኣሀ ሀ ሀ ሀ...🎶 ማዕበሉን አላይም
ኢየሱስ አንተ ተስፋዬ ነህ ሁሌ
ሳልቆጥብ ሳላሳንስ...
@matalapochurch2 166 · R
Hey there Abush, and welcome to Matala-Apo-Church2❤️❤️Discussion! How are you?
30 August 2026
Аудио
መሪጸካ_እየ_አነስ_!!!,,,ትግርኛ_መዝሙር_Abel_Demsie_Apostolic_church_መ12 · 4.9 MB · click to show 🎉🎉ድንቅ የትግርኛ መዝሙር
መሪፀካዬ አነስ ካብ ኩሉ አብሊፀ
ኩሉ ሀላፋይ እዩ በጊዜ ዝተወሰነ
የሱስይ ክበር ንዘለአለም
ከማኣስ ፍፁም ካልእ የለን
መሪፀ ልበይ ንዓኻ ሂበካ
ንጉሰይ አብ ልዕለይ ሸይሞካ
ፈሊጠዬ አነ የለ ዝመስለካ
አስተውዒለዬ አነ ከምዘ የለ ዝወዳደረካ
ተረዲኤዬ አነ ከምህ የለ ዝመስለካ
ንስኻስ ፍሉይ ኢኻ *2 የለን ከማኻ
ንስኻሽ ዓቢ ኢኻ *2 ካልአይ ዘይብልካ
ንስኻስ ፍቅሪ ኢኻ *2 ልበይ ዝማረኽካ
ዝረድኢኒ የለን ከማካ ካባይ አይትርሀቅ
ንዓካ መሪፀ አብ በትካ ዘልአለም ክነብር
ካብ አልማዝ ንላዕሊ ካብ ወርቂ ዕንቂ ከምርካብ
ንስኻ የሱስ ፍሉይ ኢሃ ብካሊይ አይትትካእ
ገፅካ አብርሃለይ ሪኤዮ ከፀግብ
ንስኻስ ፍሉይ.....
ብዙይ ብኣኻ ከቢድ እዩ ንዓይ ምንባር
ዓሳ ካብ ባህሪ ወፂኡ ህያው ከምዘይከውን
ናይ ምንባረይ ምኽንያት ንዓይ ሂወት ትንፋሰይ
የሱስይ ንስኻኢኻ ዋህሲ ናይ ምንባረይ
የሱሰይ አይትርሓሽ ካብ ጎነይ
ብጅኣካ ካልእ አአኳ ዘይብለይ
ናተይ ኢኻ አነውን ናትካ
ክበርለይ ዘለአለም በይንኻ
ፈሊጠዬ አነ ከምዛ የለ ዝመሰለካ
አስተውዒለይ እነ ከምዘ የለ ዝውዳደረካ
@matalapochurch2 150 · (ወደ ቆላስይስ ሰዎች ምዕራፍ 4)
----------
2፤ ከማመስገን ጋር በጸሎት እየነቃችሁ ለእርሱ ትጉ።
. . .
5፤ ዘመኑን እየዋጃችሁ፥ በውጭ ባሉቱ ዘንድ በጥበብ ተመላለሱ።
6፤ ለእያንዳንዱ እንዴት እንድትመልሱ እንደሚገባችሁ ታውቁ ዘንድ ንግግራችሁ ሁልጊዜ፥ በጨው እንደ ተቀመመ፥ በጸጋ ይሁን።
@matalapochurch2 157 · I
(ኦሪት ዘጸአት ምዕራፍ 15)
----------
12፤ ቀኝህን ዘረጋህ፥ ምድርም ዋጠቻቸው።
13፤ በቸርነትህ የተቤዠሃቸውን ሕዝብህን መራህ፤
በኃይልህ ወደ ቅዱስ ማደሪያህ አገባሃቸው።
14፤ አሕዛብ ሰሙ፥ ተንቀጠቀጡም፤
በፍልስጥኤም የሚኖሩትን ምጥ ያዛቸው።
15፤ የዚያን ጊዜ የኤዶም አለቆች ደነገጡ፤ የሞአብን ኃያላን መንቀጥቀጥ ያዛቸው፤ በከነዓን የሚኖሩ ሁሉ ቀለጡ።
16፤ አቤቱ፥ ሕዝብህ እስኪያልፍ ድረስ፥ የተቤዠኸው ሕዝብ እስኪያልፍ ድረስ፥ ፍርሃትና ድንጋጤ ወደቀባቸው፤ በክንድህ ብርታት እንደ ድንጋይ ዝም አሉ።
17፤ አቤቱ፥ አንተ ታስገባቸዋለህ፥ በርስትህ ተራራም ትተክላቸዋለህ፥ አቤቱ፥ ለማደሪያህ ባደረግኸው ስፍራ፥ አቤቱ፥ እጆችህ ባዘጋጁት መቅደስ።
18፤ እግዚአብሔር ለዘላለሙ እስከ ፍጻሜ ይነግሣል።
@matalapochurch2 171 · 31 August 2026
I
Аудио
የመገረም ጥግ.mp3 · 11.4 MB · click to show አዲስ መዝሙር
የመገረም ጥግ
የማራናታ መዘመራን ህብረት
/UNION OF MARANATHA CHOIR/ HOSSANA 2026
ሰማይ ዙፋንህ ምድር መርገጫ
ምን ስፍራ አለ አንተን መግለጫ
በጥልቁ ምትገኝ በእሳትም ያለህ
የተባሉ አማልክት ሁሉ ሚንቀጠቀጡልህ
የመገረም ጥግ ልክ የድንቅነት
የማትገመት በቦታ አንተን ለመለካት
ልዩ እዚህ ጋ ብቻ የማይሉህ
ልዩ የምትገኝ ከሙላት ሁሉ
በባህር ላይ የተራመድክ
ማዕበል ወጀቡ ለቃልህ የሚታዘዙልህ
ሁን ብቻ ስላልከው ተዘረጋ ሰማይ
ምድርም ፀናች ሰምታ ሚገባውን
ማለፍ ሲሆን ያንተ በግርማህ
ተራሮች በእልልታ ድንጋዮች ሚያወሩልህ
ፍጡሩ ባያመሰግንህ ሚያከብሩ አሉ ፍጥረታት
ግዑዝ የሆነውም ይገዛል ያደንቅሀል
አይጎድልም ከክብርህ የሰው ምስጋና መጉደል
ሁሉ ላንተ ሆነዋል ተፈጥረዋል ያከብሩሀል
የክብርህን መጠን ያወቁ የተረዱ
ሌት ተቀን ቅዱስ ይላሉ ክብር ለአንዱ
ለነገሰው በሀይል በክብር በዙፋኑ ላይ
ምስጋና አምልኮ እያሉ ለተገባው
ዛሬም በዙፋንህ በክብርህ ከፍታ
ከቀድሞውም ይልቅ ክበር ጌታ
አይነስ አይጉደል ከጥንቱ ከልክ
ትናንትናም ዛሬም እስከ ዘለዓለም ያው ስለሆንክ
@matalapochurch2
@matalapochurch2 145 · 1 September 2026
Аудио
beki....besemayat lay.mp3 · 5.0 MB · click to show በሰማያት ላይ ክብርህ ገኖ
ስምህም ከስሞች በላይ ሆኖ
ሳትለውጥ ከፍ ብለህ
ጸንተህ በዙፋንህ ትኖራለህ
ባለዝናዎች ሲረሱ
ሰማይና ምድር ሲያልፉ
ኢየሱስ ግን ከፍ ከፍ ብለህ
ጸንተህ በዚፋንህ ትኖራለህ
አንተን ጠርተው እስራኤላውያን
ምድረ በዳውን ተጉዘዋል
በመንገዳቸው ድል አርገዋል
የአህዛብን ርስት ወርሰዋል
@matalapochurch2 97 · I
Аудио
ለቀረቡ.m4a · 8.0 MB · click to show ለቀረቡ ለተጠጉ በእውነት ካንተ ዘንድ ፀጋ አለ*4
ፀጋ አለ ሚደግፍ
ፀጋ አለ ሚያሻግር
ፀጋ አለ ሚያሳርፍ
አለምን ሚያሸነፍ(ዘመኑን ሚያሸንፍ)
ፊትህን በፆም በምልጃ ለሚሹ
በዝቅታ ከእግርህ ስር ለቆዩ
በተስፋ አንተን ለሚጠባበቁ
ለትሁታን ፀጋን ትሰጣለህ
ዝቅ ልበል ከእግርህ ስር
ትሁት መሆን ካንተ ልማር
ፀጋ እንዲሰራ በህይወቴ
ልቤን ስበርልኝ አባቴ
በዚ ክፉ አስጨናቂ ዘመን
ከቀድሞ ይልቅ ፀጋህን ልለምን
ስጋን ከመሻቱ ጋር ለመስቀል
ዝቅ ብዬ ፀጋህን ልቀበል
ዝቅ ልበል.......
ወደ ፀጋ ዙፋን በእምነት ቀርቤ
ቶሎ ሚከበኝን ሀጥያት አራግፌ
ሀይሌንም ወደ አንተ ይበልጥ አስጠጋና
ፀጋህን ልቀበል በፀሎት ልበርታና
@matalapochurch2 114 · 2 September 2026
I
Аудио
Hedalew elay.m4a · 7.3 MB · click to show ዘማሪት አስተዋይ አባቴ
ዝማሬ እኔ አመሰግናለሁ
እምነቴ ቢፈተን መከራው እጅግ ቢበዛ
አንተን በማለቴ ሁሉም በኔ ላይ ቢነሳ
አቋራች አልሻም አልፈልግም ከአንተ ሌላ
አልፈራም በፍፁም አልለይ አልል ወደ ኋላ
እንደ ሙሉ ደስታ እቆጥረዋለሁ
እንደ ሙሉ ሀሰት እቆጥረዋለሁ
እንደ ሙሉ እረፍት እቆጥረዋለሁ
ይሆነኛልና ለዘላለም ክብር
እኔ አመሰግናለሁ በዚህ ሁሉ መሀል
እኔ አመሰግናለሁ ስለሆነው በኔ ላይ
እኔ አመሰግናለሁ አጠንክሮኛልና
እኔ አመሰግናለሁ ላንተ እንድነሳ ሰርቶኛል
እግ/ርን ለሚወዱ እንደ ሀሳቡም ለተጠሩ
ነገር ሁሉ ለበጎ እንድደረግ እናውቃለን
የክብርን የዘላለም ብዛት ከመጠን ይልቅ ልያደርግልኝ
መውደቀ መመታት ለኔ ለመልካም ሆነልኝ
ጽዮንን በብዙ መከራ እንድገባ ግድ ይለኛል
የዛሬው መሰደደ ለነገዬ ስንቄ ነውና
አላማውን በኔ ላይ ሚፈጽመው እሱ ነው
ታሪኬ በእጁ ነው ከጥንት ያውቀዋል ሚሆነውን
ድንጋዩ እንደሰብ የሚሟሟለት
ማን ይቃወመዋል ስሰራ ታምራት
ህይወቴ ቢታጀብ በብዙ ፈተና
ድል የነሳው አክሊል ይቀበላልና
አልልም ወደታች አላቀረቅርም
ድንኳኔን ለቅቄ መሄዴ አይቀርም
ዛሬ ወይም ነገ መብረሬ አይቀርም
በል ስጋዬ ስማኝ ቤት አለኝ በሰማይ
አክሊል ይጠብቀኛል እላይ
አክሊል ይጠብቀኛል በሰማይ
ቤት አለኝ በሰማይ
ሄዳለሁ እላይ
ቤት አለኝ በሰማይ
@matalapochurch2 82 ·
A snapshot of an open public feed from the search index
ChatCrawler — “Google for public Telegram”; refreshed as the venue is crawled.
Times are UTC.
Public content only, official Telegram API.
About ·
FAQ ·
What we do not do ·
Remove a page ·
Catalog