ChatCrawlersearch across public Telegram Open the app
ማ

ማታኒያ ቲዩብ

258 members
13 August 2026
14 August 2026
15 August 2026
16 August 2026
17 August 2026
18 August 2026
19 August 2026
20 August 2026
23 August 2026
24 August 2026
25 August 2026
Фотография
click to show
አረጋጊው መልአክ ቅዱስ ገብርኤል እንዲህ ነው ለሠለስቱ ደቂቅ በእሳት መካከል አብሯቸው የቆመ በእሳት እንዳይቃጠሉ እሳቱን ያበረደላቸው የሚረዳቸው ቅዱስገብርኤል ። ስሙ ድንቅ መካር ኃያል የሚባለውን ከድንቅ እናት የተወለደውን የድንቁን ሕጻን ወልደ እግዚአብሔርን ልደት እንዲያበሥር የተመረጠ ቅዱስገብርኤል ። ለዳንኤል ምሥጢር የተረጎመለት ሱባኤ የቆጠረለት የትንቢቱን ማኅተም ያሳወቀው ቅዱስ ገብርኤል ለሰማዕታት ጠል አውርዶ፣ እሳት አብርዶ፣ አንበሳ አሰግዶ፣ በዓላውያን ነገሥታት ፊት የሚረዳቸው ቅዱስገብርኤል ነው ። ቅዱስ ገብርኤል ሆይ ከፍፁም ጥፋት እንድን ዘንድ ክንፍህን ጋርድልን 🤲💚💛❤️
49 ·
Аудио
6082726593_1.mp3 · 5.8 MB · click to show
     ስሙ ገብርኤል ነው ከእሳት የሚያወጣ፤ ብስራትና ደስታን ለዓለም የሚያመጣ(፪) እንኳን ከነደደው ገና ከታሰበው፤ ያተርፋል ያድናል ፈጥኖ እእሚደርስ ነው(፪) ከትናንቱ ይልቅ ዛሬ እሚሳሳልኝ፤ በመንገዴ ቀድሞ ነገን ሚጠብቀኝ፤ አሊዝም ጋሻ ጦር አልሻም ወታደር፤ የገብርኤልን ስዕል እሰቅላለሁ ከበር። ገብርኤል ገብርኤል የቤታችን ዘውድ፤ የእናት አባቶቼ መመኪያ ዘመድ።  አ...ዝ...ማ...ች አራተኛ ሆኖ በእሳት ውስጥ ታያችሁ፤ እርሱ ገብርኤል ነው የሚታደጋቸው፤ ከሰው ጋር የሚቆም ለህዝብ የሚራራ፤ ይምጣ ለሀገራችን ከሚካኤል ጋራ ፤ ገብርኤል ገብርኤል ገብርኤል ለሚሉ፤ አበርቺ መልአክ ነው ስሙን ለሚጠሩ።   አ...ዝ...ማ...ች ከመላእክቱ አለም ከራማ ይመጣል፤ ሁሉን ወደመዳን ወደፅድቅ ይመራል፤ ኃያል ነው ገብርኤል የነገዶች መሪ፤ የጽናት ሰባኪ እምነት አስተማሪ። ገብርኤል ገብርኤል ኦ ልዑለ ራማ፤ ለተከዘችው ነፍስ ደስታን የሚያሰማ።             አ...ዝ...ማ...ች በጓዳ ነግሬው በአደባባይ ረዳኝ፤ በሰዎች መካከል ምስክር አረገኝ፤ በምን ፍጥነት አየኝ ኧረ እንዴት ደረሰ፤ ወላፈን ሳይነካኝ እንባዬን አበሰ፤ ገብርኤል ገብርኤል ፀዋሪ ምሕረት፤ ከአደጋ ሚጋርድ ሚመራ ከፊት።
58 ·
26 August 2026
Архив по месяцам
Open in Telegram Feed t.me/s Каталог площадок Искать в ChatCrawler

A snapshot of an open public feed from the search index ChatCrawler — “Google for public Telegram”; refreshed as the venue is crawled. Times are UTC.

Public content only, official Telegram API. About · FAQ · What we do not do · Remove a page · Catalog