ChatCrawlersearch across public Telegram Open the app
E

ETHIO ≈ SCHOOL

сообщение · 2025-12-18 06:11 UTC
F
Фотография
click to show
#ጥቆማ የኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት ከደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር ሀገር አቀፍ የግእዝ ጉባኤ ከሚያዚያ 15-17/2018 ዓ.ም ያካሒዳል፡፡ ለጉባኤው የሚሆኑ የምርምር ጽሑፎችን ከስር በተገለፁት የምርምር ጭብጦች ዙሪያ እንዲያቀርቡ ተጋብዘዋል፡፡ የምርምር ጭብጦች፦ ➫ የጊዜ እሳቤ እና የዘመን መንፈስ በፍልስፍና እና በግእዝ ሥነ ጽሑፍ፣ ➫ የዘመን ስሌትና ጥንታዊ የሥነ ፈለክ (አስትሮኖሚ) ምርምር፣ ➫ ሰው መሆን፣ ባህል፣ እምነት እና ጊዜ በግእዝ ሥነ ጽሑፍ፣ ➫ የኢትዮጵያ የዘመን ቀመር በግዕዝ ድርሳናት፣ ➫ የአቡሻኽር የዘመን አቆጣጠርና የእቆጣጠሩ ብልኃት፣ ➫ የዘመን አከፋፈልና የጊዜ እሳቤ በሥነ ተፈጥሮ ጥናት በቅዱስ ያሬድ ሥራዎች፣ ➫ የግዕዝ የሒሳብ ስሌት ከዘመናዊ የሒሳብ ስሌት ጋር ሲነፃፀር፣ ➫ የግዕዝ ፊደልና ቀመረ ፊደል፣ ➫ የገዳማት አስተዋጽኦ በጥንታዊው የዘመን ስሌት፣ ➫ የግእዝ ስነ-ጽሁፋዊ ሀብቶች ጥበቃ ከኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ አንጻር፣ የአኅጽሮተ ጽሑፍ ማስረከቢያ ጊዜ፦ ከታህሳስ 1-20/2018 ዓ.ም የተመረጡ የምርመር ጽሑፎች ማሳወቂያ ጊዜ፦ ታህሳስ 25/2018 ዓ.ም ሙሉ ጽሑፍ ለጉባኤው አዘጋጆች የሚላክበት ጊዜ፦ ከመጋቢት 25-30/2018 ዓ.ም የምርምር ሥራዎች የሚላኩበት አድራሻ፦ ➫ በኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት አቶ መኮንን ከፋለ ስልክ ቁ. 0933225306 ኢሜይል፦ [email protected] ➫ በደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ዐፄ ዘርዓ ያዕቆብ የባህል፣ ታሪክ እና ቋንቋ ልማት ማዕከል ኢሜይል፦[email protected] የሚቀርቡ ጥናቶች ከዚህ በፊት ያልቀረቡና ያልታተሙ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡ ለበለጠ      👇👇👇 [https://t.me/allethioschool]
163 ·

Вся лента · оригинал в Telegram

Open in Telegram Feed t.me/s Каталог площадок Искать в ChatCrawler

A snapshot of an open public feed from the search index ChatCrawler — “Google for public Telegram”; refreshed as the venue is crawled. Times are UTC.

Public content only, official Telegram API. About · FAQ · What we do not do · Remove a page · Catalog