Фотография
click to show
click to show
በቀጣይ ራስ ገዝ ሆነው የሚቋቋሙ የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ለሚያደርጉት የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች ግብዓት የሚሆን የሽግግር ረቂቅ መመሪያ ላይ ምክክር ተደረገ።
በመጪው ዓመት ራስ ገዝ ለመሆን እየሠሩ የሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች፥ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በተጀመረው ራስ ገዝ የመሆን ሂደት የተገኙ ተሞክሮዎች እና ፈተናዎችን በመለየት በቂ ዝግጅት እንዲያደርጉ የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) አሳስበዋል።
በመድረኩ ለመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የራስ ገዝነት ሽግግር የተዘጋጀው ረቂቅ መመሪያ ውይይት ተደርጎበታል።
ረቂቅ ሰነዱ ለራስ ገዝነት ሽግግር የሚያበቁ መስፈርቶችና ልዩ ልዩ ድንጋጌዎች የተካተቱበት ሲሆን፤ ዩኒቨርሲቲዎች በዚህ ረቂቅ መመሪያ እየተመዘኑ ሽግግር የሚያደርጉ መሆኑ ተገልጿል።
በመድረኩ በቀጣይ ራስ ገዝ በመሆን ለሚቋቋሙ ዩኒቨርሲቲዎች ተሞክሮ እንዲሆን የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የራስ ገዝነት ሽግግርን የተመለከተ የዳሰሳ ጥናት ቀርቦ ወይይት ተደርጎበታል።
ለበለጠ መረጃ እና
አስተያየት ካለዎት
👇👇👇
[https://t.me/allethioschool]
[https://t.me/allethioschool]
168 ·