Фотография
click to show
click to show
በአማራ ክልል ከ27 ሺህ በላይ ለሚሆኑ መምህራን እና የትምህርት ቤት አመራሮች የሙያ ፈቃድ ምዘና ይሰጣል።
በአማራ ክልል በዚህ ዓመት ከ27 ሺህ በላይ ለሚሆኑ መምህራን እና የትምህርት ቤት አመራሮች የሙያ ፈቃድ ምዘና ለመስጠት እየተሠራ መሆኑን የክልሉ ትምህርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ ደምስ እንድሪስ ገልፀዋል።
ለ21,669 ነባር እና 5,559 ከመምህራን ትምህርት ኮሌጅ ለሚመረቁ እጩ መምህራን ምዘና እንደሚሰጥ እንደሚሰጥ ምክትል ኃላፊው ጠቁመዋል።
መምህራኑ እና የትምህርት ቤት አመራሮቹ የሙያ ፈቃድ ምዘና ማረጋገጫ ሰርተፊኬት መያዛቸው የበለጠ ተወዳዳሪ ለመሆን ያስችላቸዋል ተብሏል።
በሞዴል እና አዳሪ ትምህርት ቤቶች ለማስተማር መምህራን ከሚጠየቁት ማስረጃዎች መካካል የሙያ ፈቃድ ምዘና ማረጋገጫ ሰርቲፊኬት መሆኑ ይታወቃል።
ትክክለኛ መረጃ የምትገኙበት የ 12ኛ
ለበለጠ መረጃ እና
አስተያየት ካለዎት
👇👇👇
[https://t.me/allethioschool]
[https://t.me/allethioschool]
237 ·