ChatCrawlersearch across public Telegram Open the app
E

ETHIO ≈ SCHOOL

сообщение · 2026-01-03 07:00 UTC
F
Фотография
click to show
#ጥቆማ ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በ2018 የትምህርት ዘመን በሁለተኛው ወሰነ ትምህርት በግል ከፍለው ወይም በመስሪያ ቤታቸው ስፖንሰር አድራጊነት ከፍለው መማር ለሚፈልጉ በመደበኛው እና በማታው መርሐግብር የ2ኛ ዲግሪ እና የ3ኛ ዲግሪ አመልካቾችን ተቀብሎ ማስተማር ይፈልጋል፡፡ የማመልከቻ ጊዜ፦ ከታህሳስ 24/2018 ዓ.ም እስከ የካቲት 10/2018 ዓ.ም የትምህርት መስኮች ዝርዝር እና የመግቢያ መስፈርቶችን ከዩኒቨርሲቲው ሬጅስትራር ድረ-ገጽ https://bdu.edu.et/registrar/ መመልከት ይችላሉ፡፡ የመመዝገቢያ ጊዜ የካቲት 26 እና 27/2018 ዓ.ም ሲሆን፤ ትምህርት የካቲት 30/2018 ዓ.ም ይጀምራል ተብሏል፡፡ ⤴️ ዩኒቨርሲቲው የማንበቢያና መመራመሪያ ቢሮ እንዲሁም የዶርም አገልግሎት የሚሰጥ መሆኑ ተገልጿል። 20 ተማሪዎች በኖርዌይ የልማትና ትብብር ድርጅት የገንዘብ ድጋፍ በተጀመረው የስነ-ትምህርት የሁለተኛ ዲግሪ፥ በሒሳብ እና በሳይንስ ስነ-ማስተማር (MED in Educational Sciences: Teaching of Mathematics and MED in Educational Sciences: Teaching of Science Subjects) ፕሮግራሞች ቅበላ የሚሰጣቸው ይሆናል። ለምዝገባ የሚያስፈልጉ ሰነዶች/ማስረጃዎች፦ ➫ የትምህርት ማስረጃ ዋናውና ኮፒው፣ ➫ ኦፊሻል ትራንስክሪፕት፣ ➫ በመስሪያ ቤት ስፖንሰርነት ለሚያመለክቱ አመልካቾች ከሚሰሩበት መስሪያ ቤት የስፖንሰርሽፕ ደብዳቤ፣ ➫ ለማመልከቻ የተከፈለበት ደረሰኝ ብር 300፣ ➫ የድኅረ-ምረቃ ፕሮግራም መግቢያ ፈተና (NGAT) የማለፊያ ውጤት። ለበለጠ መረጃ እና አስተያየት ካለዎት      👇👇👇 [https://t.me/allethioschool] [https://t.me/allethioschool]
250 ·

Вся лента · оригинал в Telegram

Open in Telegram Feed t.me/s Каталог площадок Искать в ChatCrawler

A snapshot of an open public feed from the search index ChatCrawler — “Google for public Telegram”; refreshed as the venue is crawled. Times are UTC.

Public content only, official Telegram API. About · FAQ · What we do not do · Remove a page · Catalog