Фотография
click to show
click to show
ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ በዋናው ግቢ፣ ቦዲቲ ግቢ እና ዳውሮ ታርጫ ካምፓስ ለአቅም ማሻሻያ (Remedial) ፕሮግራም ለተመደቡ ተማሪዎች አድርጎት የነበረውን ጥሪ በድጋሜ አራዝሟል።
ዩኒቨርሲቲው ታህሳስ 16/2018 ዓ.ም ባወጣው ማስታወቂያ የሪሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች የምዝገባ ጥሪ ወደ ጥር 01/2018 ዓ.ም መራዘሙን መግለፁ ይታወቃል።
ይሁን እንጂ "በተለያየ ምክንያት የመመዝገቢያ ቀኑን ማራዘም አስፈላጊ ሆኖ ስለተገኘ" ለዋናው ግቢ፣ ቦዲቲ ግቢ እና ዳውሮ ታርጫ ካምፓስ የተመደቡ የሪሚዲያል ተማሪዎች ምዝገባ ወደ ጥር 07 እና 08/2018 ዓ.ም የተራዘመ መሆኑን ዩኒቨርሲቲው በዛሬው ዕለት ታህሳስ 29/2018 ዓ.ም ባወጣው ማስታወቂያ ገልጿል። ትምህርት ጥር 11/2018 ዓ.ም (የጥምቀት በዓል ቀን) ይጀመራል ሲልም ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።
ለበለጠ መረጃ እና
አስተያየት ካለዎት
👇👇👇
[https://t.me/allethioschool]
[https://t.me/allethioschool]
244 ·