Фотография
click to show
click to show
#ጥቆማ
ትምህርት ሚኒስቴር የፌዴራል ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤቶችን በማቋቋም በ2018 ዓ.ም በአምስት ትምህርት ቤቶች ትምህርት ማስጀመሩ ይታወቃል።
በልዩ አዳሪ ትምህርት ቤቶቹ የመማር ማስተማር ሥራ ቢጀመርም በውስን ክፍት ቦታዎች ተጨማሪ ተማሪዎች ለመቀበል መወሰኑን ሚኒስቴሩ ገልጿል።
በመሆኑም በ2017 የ8ኛ ክፍል ትምህርታቸውን ያጠናቀቃችሁና አሁን 9ኛ ክፍል እየተማራችሁ ያላችሁ ተማሪዎች ነፃ የትምህርት ዕድል ተጠቃሚ ለመሆን ማመልከት ትችላላችሁ ተብሏል።
የማመልከቻ ጊዜ፦
ከጥር 02-07/2018 ዓ.ም
የነፃ ትምህርት ዕድሉ ጥቅሞች
➫ ሙሉ የትምህርት ክፍያ ሽፋን ያገኛሉ፣
➫ ነፃ የመኝታ እና የምግብ አገልግሎት፣
➫ የተሟላና ጥራት ያለው ትምህርት
➫ ምቹ የመማሪያ አካባቢ።
አመልካቾች ሊያሟሏቸው የሚገቡ መስፈርቶች፦
➫ በ2017 ዓ.ም 8ኛ ክፍልን ያጠናቀቀ/ች፣
➫ የዲጂታል መታወቂያ (ፋይዳ ) ያለው/ያላ፣
➫ በ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና 85% ወይም ከዚያ በላይ አማካይ ውጤት ያለው/ያላትና አሁን 9ኛ ክፍል እየተማረ ያለ/ያለች።
መስፈርቱን የምታሟሉ ተማሪዎች ምዝገባችሁን ባላችሁበት ሆናችሁ በኦንላይን https://sbs.moe.gov.et/apply መመዝገብ እና አስፈላጊ የተባሉ መረጃዎችን ማያያዝ ይጠበቅባችኋል።
የማስተማር ሥራ የተጀመረባቸው የፌዴራል ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤቶች ጋምቤል፣ ጅግጅጋ፣ ቡኢ (ወልቂጤ)፣ ቦንጋ እና ወሊሶ ናቸው።
ለበለጠ መረጃ እና
አስተያየት ካለዎት
👇👇👇
[https://t.me/allethioschool]
[https://t.me/allethioschool]
391 ·