Фотография
click to show
click to show
ታህሳስ 24/2018 ዓ.ም የተሰጠውን የብቃት ምዘና ፈተና የወሰዳችሁ የአንስቴዥያ ሙያ ተመዛኞች ከዛሬ ጥር 05/2018 ዓ.ም ጀምሮ ውጤታችሁን መመልከት የምትችሉ መሆኑን ጤና ሚኒስቴር አሳውቋል።
🔔 በተጨማሪም የጽሁፍ ፈተና ያለፋችሁ ተመዛኞች የተግባር ምዘና ፈተና ለመውሰድ ምዝገባ ጥር 06 እና 07/2018 ዓ.ም ብቻ በኦንላይን http://hpe.moh.gov.et/hple ላይ በመግባት እንድታደርጉ ተብሏል።
ከተጠቀሱት ቀናት ውጪ ምንም ዓይነት የምዝገባ ጥያቄ የማያስተናግድ መሆኑን የገለፀው ሚኒስቴሩ፤ ምዝገባ ስትዳርጉ በመረጣችሁት የፈተና ጣቢያ በፈተናው ወቅት እንድትገኙ አሳስቧል።
እያንዳንዱ የፈተና ጣቢያ ማስተናገድ በሚችለው ከፍተኛ የተመዛኝ ቁጥር ልክ ገደብ ስለተቀመጠለት ተመዛኞች ምዝገባውን ቀድማችሁ በማጠናቀቅ ተጠቃሚ መሆን የምትችሉ መሆኑ ተገልጿል።
ማንኛውም ተመዛኝ ወደ ፈተና ጣቢያ ሲሔድ ሲስተሙ የሚሰጠውን የፈተና መለያ ቁጥር (Registration No) የያዘ ወረቀት (ስሊፕ) Print አድርጎ መያዝ ይጠበቅበታል፡፡
ለበለጠ መረጃ እና
አስተያየት ካለዎት
👇👇👇
[https://t.me/allethioschool]
[https://t.me/allethioschool]
293 ·