ChatCrawlersearch across public Telegram Open the app
E

ETHIO ≈ SCHOOL

сообщение · 2026-01-16 06:01 UTC
F
Фотография
click to show
#TVTI #ExitExam በፌዴራል ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት በዋናው ግቢ እና በሥሩ በሚገኙ የሳተላይት ተቋማት በ2018 ዓ.ም ተከታታይ ፕሮግራም አንደኛ ሴሚስቴር ተመራቂዎች እንዲሁም በ2015፣ 2016 እና 2017 ዓ.ም የተሰጠውን የመውጫ ፈተና ተፈትናችሁ ማለፊያ ውጤት ያላመጣችሁ ተማሪዎች የመውጫ ፈተና ለመውሰድ የምዝገባ ጊዜ ከጥር 09-22/2018 ዓ.ም መሆኑን ኢንስቲትዩቱ አሳውቋል፡፡ የምዝገባ ቦታ፦ ➫ በ2018 ዓ.ም አንደኛ ሴሚስቴር ለምትጨርሱ ተከታታይ ፕሮግራም ተመራቂዎች ምዝገባው በምትማሩበት ግቢ በየትምህርት ክፍላችሁ ይሆናል፡፡ ➫ በሳተላይት ተቋማት ለምትጨርሱ ተከታታይ ፕሮግራም ተመራቂዎች በሳተላይት አስተባባሪዎች አማካኝነት በየሳተላይቱ ይሆናል፡፡ ➫ በ2015፣ 2016 እና በ2017 ዓ.ም የተሰጠውን የመዉጫ ፈተና ተፈትናችሁ ማለፊያ ዉጤት ያላመጣላችሁ ለሁሉም ዲፓርትመንት ተማሪዎች የምዝገባ ቦታ በዋናው ግቢ ICT Department ህንፃ ቁጥር 2፣ 1ኛ ፎቅ ይሆናል፡፡ የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት የመውጫ ፈተና የሚሰጥባቸው ዩኒቨርሲቲዎች፦ ድሬ ዳዋ ዩኒቨርሲቲ፣ አርሲ ዩኒቨርሲቲ፣ ራያ ዩኒቨርሲቲ፣ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ፣ ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ (ፖሊ ቴክኒክ ኢንስቲትዩት) ፣ ኮምቦልቻ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት እና የፌዴራል ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት ዋናው ግቢ በምዝገባ ወቅት ፈተናውን መውሰድ የምትፈልጉበትን ማዕከል በመምረጥ ምዝገባ ማድረግ ይኖርባችኋል ተብሏል፡፡ 🔔 ፈተናውን ለመውሰድ የፋይዳ መታወቂያ እንደ ቅድመ ሁኔታ መቀመጡን አውቃችሁ ከወዲሁ እንድትዘጋጁ ኢንስቲትዩቱ አሳስቧል፡፡ ለተጨማሪ መረጃ፦ 0912043138 / 0974272609 / 0985414699 ለበለጠ      👇👇👇 [https://t.me/allethioschool]
266 ·

Вся лента · оригинал в Telegram

Open in Telegram Feed t.me/s Каталог площадок Искать в ChatCrawler

A snapshot of an open public feed from the search index ChatCrawler — “Google for public Telegram”; refreshed as the venue is crawled. Times are UTC.

Public content only, official Telegram API. About · FAQ · What we do not do · Remove a page · Catalog