ChatCrawlersearch across public Telegram Open the app
E

ETHIO ≈ SCHOOL

сообщение · 2026-01-18 07:10 UTC
F
Фотография
click to show
የድኅረ-ምረቃ ትምህርት የመግቢያ ፈተና (NGAT) በየትኞቹ ዩኒቨርሲቲዎች ይሰጣል? በዚህ ወር እንደሚሰጥ የሚጠበቀው የድኅረ-ምረቃ ትምህርት የመግቢያ ፈተና (NGAT) ምዝገባ መጀመሩ ይታወቃል። ምዝገባው እስከ ጥር 15/2018 ዓ.ም እንደሚቆይ ተገልጿል። 12 ዩኒቨርሲቲዎች ለፈተና ጣቢያነት የተመረጡ መሆናቸውን ከትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት የተገኘው መረጃ ያሳያል። ተመዝጋቢዎች ከታች ከተዘረዘሩ ዩኒቨርሲቲዎች መካከል በአቅራቢያቸው ያለውን ወይም የሚፈልጉትን ለመፈተኛ ጣቢያነት እንዲመርጡ አገልግሎቱ አሳስቧል። ምዝገባው ሲጠናቀቅ በእያንዳንዱ የፈተና ጣቢያ ቢያንስ 25 ተፈታኞች ካላመለከቱበት እንደፈተና ጣቢያ የማይወሰድ መሆኑ ተጠቁሟል። ለፈተና ጣቢያነት የተመረጡ ዩኒቨርሲቲዎች፦ ➫ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ➫ አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ➫ ጅማ ዩኒቨርሲቲ ➫ መቐለ ዩኒቨርሲቲ ➫ ወሎ ዩኒቨርሲቲ ➫ ወለጋ ዩኒቨርሲቲ ➫ ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ➫ ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ➫ ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ➫ አሶሳ ዩኒቨርሲቲ ➫ ጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ ➫ ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ 📌Share&forward📌          📌Join📌           👇👇👇 💯 @merejamnch 💯 💯 @merejamnch 💯
261 ·

Вся лента · оригинал в Telegram

Open in Telegram Feed t.me/s Каталог площадок Искать в ChatCrawler

A snapshot of an open public feed from the search index ChatCrawler — “Google for public Telegram”; refreshed as the venue is crawled. Times are UTC.

Public content only, official Telegram API. About · FAQ · What we do not do · Remove a page · Catalog