Фотография
click to show
click to show
#OSCE
ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በ Anesthesia ሙያ በመጀመሪያ ዲግሪ ተመርቃችሁ ታህሳስ 24/2018 ዓ.ም የተሰጠውን የጽሁፍ የብቃት ምዘና ፈተና አልፋችሁ የተግባር ፈተና (OSCE) ለመውሰድ ምዝገባ ያጠናቀቃችሁ፤ የተግባር ፈተናው አርብ ጥር 15/2018 ዓ.ም ይሰጣል፡፡
➫ በፈተናው ዕለት ማንነታችሁን የሚገልጽ መታወቂያ (የቀበሌ መታወቂያ፣ ፓስፖርት፣ መንጃ ፍቃድ ወይም ሌላ በግልጽ የሚታይ ህጋዊ መታወቂያ) ይዛችሁ መገኘት ይኖርባችኋል፡፡
➫ ምንም አይነት የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያ (ስልክ፣ የእጅ ሰዓት፣ መነጽር (የተረጋገጠ የዕይታ ችግር ከሌለ በስተቀር)፣ ይዞ መግባት አይፈቀድም፡፡
➫ ማንኛውም ተመዛኝ ወደ ፈተና ጣቢያ ሲሔድ ሲስተሙ የሚሰጠውን QR Code ያለው የፈተና መግቢያ (ስሊፕ) Print አድርጎ ካልያዘ ፈተናውን መውሰድ የማይችል መሆኑ ተገልጿል፡፡
➫ ተመዛኞች ስማችሁ ከተጠቀሰበት የመፈተኛ ጣቢያ (ተቋም) ውጪ በፍጹም ፈተናውን መውሰድ አይፈቀድም፡፡ (ከላይ የተያያዘውን ዝርዝር ይመልከቱ፡፡)
➫ ተመዛኞች ለፈተናው ቅድመ ገለጻ ነገ ጥር 14/2018 ዓ.ም በ8፡00 ሰዓት ላይ በመረጡት የፈተና ጣቢያ መገኘት ይጠበቅባችኋል።
ለበለጠ መረጃ እና
አስተያየት ካለዎት
👇👇👇
[https://t.me/allethioschool]
[https://t.me/allethioschool]
309 ·