Фотография
click to show
click to show
መቐለ ዩኒቨርሲቲ በአማራጭ የመምህራን ስልጠና ፕሮግራም ለመሰልጠን ያመለከቱና የመጀመሪያ ዙር ማጣሪያ ያለፉ አመልካቾች ተጨማሪ ማረጋገጫ ማስገባት እንደሚጠበቅባቸው አሳውቋል፡፡
በዚህም የመቐለ ዩኒቨርሲቲ ኤዱኬሽን ሳይንስ ትምህርት ቤት ያወጣው አመልካቾች ዝርዝር ላይ "to be verified" የተባላችሁ በሙሉ፣ የመጀመሪያ ዲግሪ ሰርተፊኬታችሁን እስከ ጥር 17/2018 ዓ.ም ለትምህርት ቤቱ እንድታስገቡ ተብሏል፡፡
እስከተጠቀሰው ቀን ድረስ ሰነዳቸውን የማያስገቡ አመልካቾች በሌሎች ዕጩዎች እንደሚተኩ ዩኒቨርሲቲው ገልጿል፡፡
የመቐለ ዩኒቨርሲቲ አመልካቾች ዝርዝር 👇🏻
https://drive.google.com/file/d/1N6_CNkRjWZeX4LQXIDQGOxRx-4P8wbc-/view
መቐለ ዩኒቨርሲቲ በአምስት የትምህርት ዘርፎች ማለትም ባዮሎጂ፣ ፊዚክስ፣ ኬሚስትሪ፣ እንግሊዝኛ እና ሒሳብ መስኮች በእያንዳንዳቸው 40 አመልካቾችን እንደሚቀበል አስረድቷል፡፡
ለአንድ ዓመት የሚሰጠው ’አማራጭ የመምህራን ስልጠና ፕሮግራም’ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ በኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ፣ በጅማ ዩኒቨርሲቲ፣ በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ፣ በመቐለ ዩኒቨርሲቲ እና በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ተግባራዊ እየተደረገ ይገኛል።
ለበለጠ መረጃ እና
አስተያየት ካለዎት
👇👇👇
[https://t.me/allethioschool]
[https://t.me/allethioschool]
278 ·