Фотография
click to show
click to show
ተራዝሟል!
ትምህርት ሚኒስቴር ትምህርት ባስጀመረባቸው የፌዴራል ልዩ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ባሉ ጥቂት ክፍት ቦታዎች ተጨማሪ ተማሪዎችን (አሁን 9ኛ ክፍል ገብተው እየተማሩ ካሉ ተማሪዎች መካከል በማወዳደር) ተቀብሎ ማስተማር ይፈልጋል።
የምዝገባ ጊዜው እንዲጨመር አንዳንድ ክልሎች በጠየቁት መሰረት እስከ ጥር 20/2018 ዓ.ም የተራዘመ መሆኑን ሚኒስቴሩ አሳውቋል፡፡
የነጻ ትምህርት ዕድሉ ጥቅሞች፦
➫ ሙሉ የትምህርት ክፍያ ሸፋን
➫ ነጻ የመኝታ እና የምግብ አገልግሎቶች
➫ ልዩ ስርዓተ ትምህርት የሚከተል ጥራት ያለው ትምህርት
➫ ምቹ የመማሪያ አካባቢ
አመልካቾች ሊያሟሏቸው የሚገቡ መስፈርቶች፦
➫ በ2017 ዓ.ም 8ኛ ክፍልን ያጠናቀቀ/ች፣
➫ የዲጂታል መታወቂያ (ፋይዳ) ያለው/ያላት፣
➫ በ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና 85% ወይም ከዚያ በላይ አማካይ ውጤት ያለው/ያላትና አሁን 9ኛ ክፍል እየተማረ ያለ/ያለች።
መስፈርቱን የምታሟሉ ተማሪዎች ምዝገባችሁን ባላችሁበት ሆናችሁ በኦንላይን https://sbs.moe.gov.et/apply መመዝገብ እና አስፈላጊ የተባሉ መረጃዎችን ማያያዝ ይጠበቅባችኋል።
የማስተማር ሥራ የተጀመረባቸው የፌዴራል ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤቶች ጋምቤል፣ ጅግጅጋ፣ ቡኢ (ወልቂጤ)፣ ቦንጋ እና ወሊሶ ናቸው።
ለፈተና የሚቀርቡ ተማሪዎች ዝርዝር እና የፈተና ጊዜ ወደፊት ይገለጻል ተብሏል፡፡
ለበለጠ መረጃ እና
አስተያየት ካለዎት
👇👇👇
[https://t.me/allethioschool]
[https://t.me/allethioschool]
400 ·