Фотография
click to show
click to show
#ጥቆማ
ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በ2018 ዓ.ም ሁለተኛ ሴሚስተር በአማራጭ የመምህራን ስልጠና ፕሮግራም በ Postgraduate Diploma በመደበኛ እና በእረፍት ቀናት መርሐግብር አመልካቾችን ተቀብሎ ማስተማር ይፈልጋል፡፡
የስልጠና ዘርፎች፦
ሒሳብ፣ ባዮሎጂ፣ ኬሚስትሪ፣ የዜግነት ትምህርት፣ ኢኮኖሚክስ፣ እንግሊዝኛ፣ ኢንፎርሜሽን ኮሚዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ፣ ፊዚክስ እና ስፖርት
የማመልከቻ መስፈርቶች፦
➫ ከታወቀ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም በተመሳሳይ ወይም በተዛማጅ የትምህርት መስክ የመጀመሪያ ዲግሪ/ከዚያ በላይ ያለው/ያላት
➫ በመምህርነት ለማገልገል ፍላጎት ያለው/ያላት
➫ ከግል ተቋማት የተመረቃችሁ አመልካቾች የትምህርት ማስረጃችሁን ትክክለኛነት ከትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን ማረጋገጫ ማቅረብ ይጠበቅባችኋል።
የማመልከቻ ጊዜ የሚያበቃው፦
የካቲት 06/2018 ዓ.ም
የማመልከቻ ሁኔታ፦
➫ ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ዋናው ሬጅስትራር ቢሮ ቁ. 41 በሥራ ሰዓት
➫ በኦንላይን ለማመልከት የማመልከቻ ፎርሙን በዩኒቨርሲቲው ድረ-ገጽ (https://portal.hu.edu.et) በመግባትና አካውንት በመፍጠር አስፈላጊ መረጃዎችን መሙላት ይጠበቅባችኋል።
የመደበኛ ፕሮግራም አመልካቾች የመኝታ፣ ምግብ እና ጤና አገልግሎቶች ሙሉ በሙሉ በመንግሥት እንደሚሸፈኑ የተገለፀ ሲሆን፤ የእረፍት ቀናት አመልካቾች የትምህርት ወጪያቸውን በራሳቸው ይሸፍናሉ ተብሏል።
ለበለጠ መረጃ እና
አስተያየት ካለዎት
👇👇👇
[https://t.me/allethioschool]
[https://t.me/allethioschool]
326 ·