Фотография
click to show
click to show
በትግራይ ክልል በ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ መልቀቂያ ፈተና የሚወስዱ ተፈታኞች ምዝገባ ተጀምሯል።
የተፈታኞች ምዝገባ ከየካቲት 18-30/2018 ዓ.ም በኦንላይን እንደሚከናወን የክልሉ የትምህርት ጥራት ማረጋገጫ ኤጀንሲ ገልጿል።
በዚህ ዓመት በክልሉ ከ30 ሺህ በላይ ተማሪዎች ሀገር አቀፍ ፈተናውን ይወስዳሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ኤጀንሲው ጠቁሟል።
ተማሪዎች መታወቂያቸውን፣ ስልክ ቁጥራቸውን እና የትምህርት ሰነዶቻቸውን ይዘው ምዝገባ ማድረግ አለባቸው ተብሏል።
በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ያልተመዘገቡ ተማሪዎች ለፈተና እንደማይቀመጡ ኤጀንሲው አሳስቧል።
ለበለጠ መረጃ እና
አስተያየት ካለዎት
👇👇👇
[https://t.me/allethioschool]
[https://t.me/allethioschool]
449 ·