Фотография
click to show
click to show
#Update
የብቃት ምዘና ፈተና ለመውሰድ በመጠባበቅ ላይ የምትገኙ የጤና ባለሙያዎች ከዛሬ ግንቦት 20/2018 ዓ.ም ጀምሮ የፈተና ጣቢያ ምርጫ እንድታደርጉ ተብሏል፡፡
ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በመጀመሪያ ዲግሪ ተመርቃችሁ የብቃት ምዘና ፈተና ለመጀመሪያ ጊዜ ወይም በድጋሜ ለመውሰድ ስማችሁን ከፋይዳ ቁጥራችሁ ጋር አስተሳሰራችሁ በመጠባበቅ ላይ የምትገኙ የጤና ሙያ ተመራቂዎች ከግንቦት 20-26/2018 ዓ.ም ድረስ ብቻ https://hple.moh.gov.et/ ላይ በመግባት የFayda ቁጥራችሁን እና Password በማስገባት የፈተና ጣቢያ እንድትመርጡ ሚኒስቴሩ አሳስቧል፡፡
እያንዳንዱ የፈተና ጣቢያ በየሙያ መስኩ ማስተናገድ በሚችለው ከፍተኛ የተመዛኝ ቁጥር ልክ ገደብ ስለተቀመጠለት፣ የፈተና ጣቢያ ምርጫ ቀድማችሁ በማጠናቀቅ ተጠቃሚ መሆን የምትችሉ መሆኑ ተገልጿል፡፡
ለብቃት ምዘና ፈተና የመፈተኛ ጣቢያ መምረጥ የምትችሉት ስማችሁን ከፋይዳ ቁጥር ጋር ያያያዛችሁ ተመዛኞች ብቻ እንሆናችሁ ተመላክቷል፡፡
በምዝገባ ወቅት ለሚገጥማችሁ ማንኛውም ችግር በነጻ የስልክ መስመር 952 በመደወል ከዚያም 3 ቁጥርን በመጫን በቀጥታ እገዛ ማግኘት ትችላላችሁ ተብሏል፡፡
ጤና ሚኒስቴር የጤና ባለሙያዎች የብቃት ምዘና ፈተናን በሰኔ ወር 2018 ዓ.ም ለመስጠት እየተዘጋጀ ይገኛል፡፡
ለበለጠ መረጃ እና
አስተያየት ካለዎት
👇👇👇
[https://t.me/allethioschool]
[https://t.me/allethioschool]
235 ·