ChatCrawlersearch across public Telegram Open the app
E

ETHIO ≈ SCHOOL

сообщение · 2026-06-05 12:25 UTC
F
Фотография
click to show
#MoE ትምህርት ሚኒስቴር “ኤጀንቲክ መምህር ረዳት” የተሰኘ የሰው ሰራሽ አስተውሎት መተግበሪያ አበልፅጎ በሙከራ ደረጃ ሥራ ላይ አውሏል። Agentic AI Teacher Assistant የተባለው መተግበሪያው፣ ሙሉ በሙሉ ያለ ኢንተርኔት የሚሠራ፣ ራሱን ችሎ ውሳኔዎችን ማመንጨት የሚችል እና የሁለተኛ ደረጃ መምህራንን የሥራ ጫና የሚቀንስ መሆኑ ተገልጿል፡፡ መተግበሪያው በውስጥ አቅም የበለፀገና በአካባቢያዊ ኮምፒውተር (Local Machine) ላይ በቀላሉ ተጭኖ የሚሠራ መሆኑን በሚኒስቴሩ ‎የአይሲቲና ዲጂታል ትምህርት መሪ ስራ አስፈጻሚ ዘላለም አሰፋ (ዶ/ር) ተናግረዋል። ‎ ‎መተግበሪያው በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት ከ9ኛ-12ኛ ክፍል ያሉትን መፅሐፍቶች በሙሉ ዳታሴት አድርጎ በመውሰድ፣ መፃሕፍቱን ሙሉ በሙሉ እንዲመረምርና እንዲገነዘብ ተደርጎ የተዘጋጀ መሆኑን ገልፀዋል። ‎ ‎መተግበሪያው ምን ምን ይሠራል? ➫ የትምህርት እቅድ (Lesson Plan) ያዘጋጃል፣ ➫ የፈተና ጥያቄዎችና አሳይመንቶችን ያመነጫል፣ ➫ ማስተማሪያ ስልቶችን (Pedagogical Strategies) በራሱ ማቀናጀት ይችላል። መተግበሪያው በማንኛውም ላፕቶፕ ወይም ዴስክቶፕ ላይ ተጭኖ የሚሠራ ሲሆን፤ ‎በተመረጡ ትምህርት ቤቶች ተሞክሮ አጥጋቢ ውጤት ማስገኘቱ ተመላክቷል፡፡ መተግበሪያውን ለመጠቀም ምንም አይነት ወርሃዊ የኢንተርኔት ካርድ፣ የኔትዎርክ ዝርጋታ ወይም የኤአይ አጠቃቀም ክፍያ እንደማይጠይቅ በሚኒስቴሩ ‎የአይሲቲ አማካሪ ሙሉነህ አጥናፉ (ዶ/ር) አስረድተዋል። ‎ ከሁሉም ክልሎች ለተውጣጡ መምህራን እና የቴክኖሎጂ ባለሙያዎች በመተግበሪያው አጠቃቀም ዙሪያ ስልጠና መሰጠቱ ተገልጿል። ለበለጠ መረጃ      👇👇👇 [https://t.me/allethioschool] [https://t.me/allethioschool]
151 ·

Вся лента · оригинал в Telegram

Open in Telegram Feed t.me/s Каталог площадок Искать в ChatCrawler

A snapshot of an open public feed from the search index ChatCrawler — “Google for public Telegram”; refreshed as the venue is crawled. Times are UTC.

Public content only, official Telegram API. About · FAQ · What we do not do · Remove a page · Catalog