ChatCrawlersearch across public Telegram Open the app
E

ETHIO ≈ SCHOOL

сообщение · 2026-06-08 12:07 UTC
F
Фотография
click to show
በትምህርት ሚኒስቴር እና በክልል ትምህርት ቢሮዎች ትብብር እየተገነቡ የሚገኙ 1,452 የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን እስከ መጪው ነሐሴ መጨረሻ ድረስ ለማጠናቀቅ እየተሠራ ነው፡፡ - ትምህርት ሚኒስቴር ከአጠቃላይ 1,452 የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች መካከል 726 በትምህርት ሚኒስቴር እና 726 በክልል ትምህርት ቢሮዎች አማካኝነት የሚገነቡ ናቸው። ትምህርት ቤቶቹን በ2019 የትምህርት ዘመን ለአገልግሎት ለማብቃት የግንባታ ሥራዎች እየተከናወኑ መሆናቸውን በሚኒስቴሩ የትምህርት ቤቶች ግንባታ ፕሮጀክት ጽ/ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅ ከተማ መስቀላ (ዶ/ር) ገልፀዋል። እስካሁን በትምህርት ሚኒስቴር እና በክልሎች የሚገነቡ ከ400 በላይ ትምህርት ቤቶች የኮንትራት ስምምነት ከተቋራጮች ጋር ተፈርሞ ወደ ሥራ የተገባ መሆኑን የገለፁት ሥራ አስኪያጁ፤ 25 ትምህርት ቤቶች የግንባታ ሥራቸውን በይፋ መጀመራቸውን አብራርተዋል። በተለያዩ ምክንያቶች የግንባታ ሒደታቸው የዘገየባቸው ክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች፣ ትምህርት ቤቶቹ በተያዘላቸው ጊዜ እንዲጠናቀቁ በቀሪው ጊዜ አስፈላጊውን ትኩረትና ክትትል እንዲያደርጉ ኃላፊው አሳስበዋል። ለበለጠ መረጃ እና አስተያየት ካለዎት      👇👇👇 [https://t.me/allethioschool] [https://t.me/allethioschool]
110 ·

Вся лента · оригинал в Telegram

Open in Telegram Feed t.me/s Каталог площадок Искать в ChatCrawler

A snapshot of an open public feed from the search index ChatCrawler — “Google for public Telegram”; refreshed as the venue is crawled. Times are UTC.

Public content only, official Telegram API. About · FAQ · What we do not do · Remove a page · Catalog