ChatCrawlersearch across public Telegram Open the app
E

ETHIO ≈ SCHOOL

сообщение · 2026-06-09 14:30 UTC
F
Фотография
click to show
የ2018 ዓ.ም የከፍተኛ ትምህርት የቅድመ-ምረቃ የመውጫ ፈተና በ52 ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስጥ ይሰጣል፡፡   የመውጫ ፈተናው ከ48ቱ የመንግሥት ዩኒቨርሲዎች በተጨማሪ በኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ፣ በኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ፣ በኢትዮጵያ ፐብሊክ ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ፣ በኦሮሚያ ስቴት ዩኒቨርሲቲ፣ በቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት እንዲሁም በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሌኒየም ሕክምና ኮሌጅ እንደሚሰጥ በትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት የወጣው የፈተና መስጫ መርሐግብሩ ያሳያል፡፡ የመውጫ ፈተናው ከሰኔ 04-12/2018 ዓ.ም የሚሰጥ ሲሆን፤ ስለፈተናው አጠቃላይ ገለጻ ለተፈታኞች እንደሚሰጥ በመርሐግብሩ ላይ ተመላክቷል፡፡   ተፈታኞች ፈተናው ከሚጀመርበት አንድ ቀን አስቀድመው በተመደቡበት ዩኒቨርሲቲ/ከፍተኛ ትምህርት ተቋም በመገኘት የመፈተኛ ክፍላቸውን ሊያዩ ይገባል ተብሏል፡፡     ፈተናውን ለመውሰድ የተመዘገባችሁ ተፈታኞች የግል መረጃችሁን በራስ በማረጋገጥ የፈተና መግቢያ ትኬታችሁን ፕሪንት በማለት መያዝ ይጠበቅባችኋል፡፡   ለበለጠ መረጃ እና አስተያየት ካለዎት      👇👇👇 [https://t.me/allethioschool] [https://t.me/allethioschool]
295 ·

Вся лента · оригинал в Telegram

Open in Telegram Feed t.me/s Каталог площадок Искать в ChatCrawler

A snapshot of an open public feed from the search index ChatCrawler — “Google for public Telegram”; refreshed as the venue is crawled. Times are UTC.

Public content only, official Telegram API. About · FAQ · What we do not do · Remove a page · Catalog