Фотография
click to show
click to show
#ተጨማሪ
ከሰኔ 17-19/2018 ዓ.ም የሚሰጠውን የጤና ባለሙያዎች የብቃት ምዘና ፈተና የምትወስዱ ተመዛኞች ማክሰኞ ሰኔ 16/2018 ዓ.ም ከሰዓት 8፡00 ሰዓት በመፈተኛ ጣቢያ በመገኘት ስለፈተናው አሰጣጥ ቅድመ ገለጻ መከታተል ይኖርባችኋል ተብሏል፡፡
የተመዛኞች ስም እና የተመደቡበትን የፈተና ማዕከል ዝርዝር በ https://t.me/M0H_EThiopia/2842 እና https://t.me/M0H_EThiopia/2851 ላይ ማየት ይችላሉ፡፡
በፈተናው ወቅት የብሔራዊ መታወቂያ እንዲሁም ሲስተሙ የሚሰጠውን QR Code ያለው የፈተና መግቢያ (ስሊፕ) ፕሪንት አድርጋችሁ መያዝ ይኖርባችኋል፡፡
ምንም አይነት የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያ (ስልክ፣ የእጅ ሰዓት፣ መነፅር (የተረጋገጠ የዕይታ ችግር ከሌለ በስተቀር)፣ ቦርሳ እና ሌሎች እቃዎች፣ ምንም አይነት ማጣቀሻዎች እና ባዶ ወረቀቶች እንዲሁም ምግብ ወይም መጠጥ (የተረጋገጠ የጤና ችግር ከሌለ በስተቀር) ይዞ ወደ ፈተና ክፍል መግባት አይፈቀድም፡፡
በፈተናው ወቅት ተመዛኞች በሁለቱም ክፍለ ጊዜ (ጠዋት እና ከሰዓት) የፈተና ክፍሉን ለቀው ከመውጣታቸው በፊት አቴንዳንስ ላይ መፈረም ይጠበቅባቸዋል።
ተመዛኞች ስማቸው ከተጠቀሰበት የመፈተኛ ጣቢያ ውጪ በፍጹም ፈተናውን መውሰድ አይፈቀድም፡፡
ለበለጠ መረጃ እና
አስተያየት ካለዎት
👇👇👇
[https://t.me/allethioschool]
[https://t.me/allethioschool]
231 ·