Ссылка
click to show
click to show
#ExitExamComplaints
ሰሞኑን የተሰጠውን የ2018 ዓ.ም የቅድመ-ምረቃ የመውጫ ፈተናን ከ224 ሺህ በላይ ተማሪዎች መውሰዳቸውን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት መግለፁ ይታወቃል።
በሀገር አቀፍ ደረጃ በ88 ማዕከላት እና በ287 የፈተና አይነቶች በተሰጠው ፈተና ላይ ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች እና የትምህርት ክፍሎች "ቅሬታ አለን" ያሉ ተፈታኞች ቅሬታቸውን አቅርበዋል።
የፋርማሲ ተማሪዎች "የፈተናው ጥያቄዎች አስቀድመው ተሰርቀው ለተወሰኑ ተማሪዎች ተሰራጭተዋል" የሚል ቅሬታ አቅርበዋል።
ኃላፊነት በማይሰማቸው አካላት አማካኝነት ፈተናው ቀድሞ ወጥቶ መሰራጨቱን የሚያሳዩ መረጃዎች እንዳላቸው ቅሬታ አቅራቢዎቹ ገልፀዋል። ይህ መሆኑም በከፍተኛ ጥረትና በራሳቸው ልፋት የተፈተኑ ተማሪዎችን ስነ-ልቦና የጎዳና ፍትሃዊነትን የጎደለው ተግባር መሆኑን ጠቁመዋል። የሚመለከታቸው የበላይ አካላት እንዚህ ጉዳይ ላይ ምርመራ እንዲያደርጉና ምላሽ እንዲሰጡበት ጠይቀዋል።
ሌላው፣ በአንዳንድ የትምህርት ዘርፍ ውስጥ ካሉ ተፈታኞች ዘንድ የተነሳው ቅሬታ ፈተናው ከተቀመጠው የይዘት መመሪያ (Blueprint) ውጪ መውጣቱ ነው።
ከባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በተላከ የቅሬታ መልዕክት የሂሳብ፣ የፊዚክስ፣ የጂኦሎጂ እና የሰርቬይንግ ኢንጂነሪንግ የተለያዩ ጥያቄዎች ከተቀመጠው መመሪያ (Blueprint) ጋር የማይጣጣሙ ሆነው እንዳገኟቸው ገልፀዋል። በተመሳሳይ ከቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በተላኩ መልዕክቶች የእንስሳት ጤና (DVM) የመውጫ ፈተና የተለያዩ ጥያቆዎች ከBlueprint ጋር የማይገናኙ እንደሆኑ አመልክተዋል።
ከዚህ ባለፈ መልስ የሌላቸው ስህተት የሆኑ ጥያቄዎች እንደነበሩ ተመሳሳይ ምርጫዎች መደገማቸውንም ተማሪዎች ጠቁመዋል። በአንዳንድ የትምህርት ዘርፎች ላይ የሰዓት እጥረት እንደነበር ተፈታኞቹ ጠቁመዋል።
በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ (ASTU) እና በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲዎች ያጋጠመው ተደጋጋሚ የመብራት መቋረጥ በፈተናው ሂደት ላይ እንቅፋት እንደነበር የገለፁ ተፈታኞች ነበሩ። በተለይም በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ የጤና ኢንፎርማቲክስ ተማሪዎች ፈተና ወቅት መብራት አራት ጊዜ በመጥፋቱ ምክንያት የባከነው ሰዓት ሳይተካላቸው ቀርቶ፣ የ100 ጥያቄዎችን ፈተና በአንድ ሰዓት ውስጥ ብቻ እንዲያጠናቅቁ መገደዳቸውን ተማሪዎቹ ገልፀዋል።
በተመሳሳይ እንደ አካውንቲንግ ባሉ የሂሳብ ስሌት በሚጠይቁ ዘርፎች ካልኩሌተር እና የማሰቢያ ወረቀት መከልከላቸው ጥያቄዎችን በግምት ለማጥቆር እንደዳረጋቸውና ከፍተኛ ጫና እንደፈጠረባቸው ተማሪዎቹ ለቲክቫህ አብራርተዋል።
ተፈታኞቹ ትምህርት ሚኒስቴር እና የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት የነበሩትን እንቅፋቶች ፈትሸው ፍትሃዊ መፍትሄ እንዲሰጡ፣ ስህተት ያለባቸው ጥያቄዎች እንዲመረመሩ እና ውጤት ሲገለጽ ያጋጠሙትን የቴክኒክ ችግሮች ታሳቢ ያደረገ እንዲሆን ጠይቀዋል።
እስካሁን ድረስ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት በተነሱት ቅሬታዎች ላይ ያለው ነገር የለም። መ/ቤቱ ትናንት ባወጣው አጭር መግለጫ፣ ፈተናው "በሰላም መጠናቀቁን" ብቻ ገልጿል። አገልግሎቱ በተነሱት ጉዳዮች ላይ የሚያወጣውን መረጃ የምናደርሳችሁ ይሆናል።
ለበለጠ መረጃ እና
አስተያየት ካለዎት
👇👇👇
[https://t.me/allethioschool]
[https://t.me/allethioschool]
131 ·