Фотография
click to show
click to show
ትምህርት ሚኒስቴር ላለፉት ዓመታት አቋርጦት የቆየውን የመምህራን የክረምት ትምህርት ስልጠና ዘንድሮ ሊጀምር ነው።
በኮቪድ-19፣ በጦርነት እና በተለያዩ ምክንያቶች ተቋርጦ የቆየው የመምህራን የክረምት ትምህርት ስልጠና በዚህ ዓመት ሊጀመር እንደሆነ ተሰምቷል።
የስልጠና ፕሮግራሙ በዲግሪ ፕሮግራም በስምንት የትምህርት አይነቶች በተያዘው ዓመት በድጋሚ ሊጀመር መሆኑ ታውቋል።
እንግሊዝኛ፣ ሒሳብ፣ ኬሚስትሪ፣ ፊዚክስ፣ ባዮሎጂ፣ ጂኦግራፊ፣ ታሪክ እና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ በክረምቱ ወራት ስልጠና የሚሠጥባቸው የትምህርት አይነቶች መሆናቸው ተገልጿል።
የኢትዮ ኮደርስ ስልጠና ያጠናቀቁ እና የሙያ ብቃት ምዘና ያለፉበትን የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መምህራን ለክረምቱ የዲግሪ ፕሮግራም ስልጠና ማመልከት ይችላሉ ተብሏል።
አመልካቾች ከ8ኛ ክፍል ጀምሮ የትምህርት ማስረጃዎቻቸውን ማቅረብ የሚችሉ፣ ቢያንስ የሦስት ዓመት የሥራ ልምድ ያላቸው እና እድሜአቸው ከ50 ያልበለጠ እንዲሆኑ ይጠበቃል።
ትምህርት ሚኒስቴር ባለፉት ሁለት ዓመታት ልዩ የመምህራን እና የትምህርት ቤት አመራሮች የክረምት ስልጠና መስጠቱ ይታወቃል።
ለበለጠ መረጃ እና
አስተያየት ካለዎት
👇👇👇
[https://t.me/allethioschool]
[https://t.me/allethioschool]
166 ·