ChatCrawlersearch across public Telegram Open the app
E

ETHIO ≈ SCHOOL

сообщение · 2026-07-02 11:55 UTC
F
Фотография
click to show
በአራት ዘርፎች ከ6ዐ በመቶ በላይ የሚያመጡ የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ራስ ገዝ ይሆናሉ። - ትምህርት ሚኒስቴር የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች በአስተዳዳር፣ በፋይናንስ፣ በሰው ኃይል አደረጃጀት እና በአካዳሚክ መለኪያዎች መሠረት ተገምግመው ከ6ዐ በመቶ በላይ ውጤት ካስመዘገቡ ራስ ገዝ መሆን እንደሚችሉ የትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል፡፡ ራስ ገዝ መሆን የሚፈልግ ዩኒቨርሲቲ የራሱን ተቋማዊ ግለ ግምገማ በማድረግ ወደ ራስ ገዝነት ለመሸጋገር የሚያስችል ውጤት 6ዐ በመቶና ከዚያ በላይ ማገኘቱን ሲያረጋግጥ በዩኒቨርሲቲው ሥራ አመራር ቦርድ አፀድቆ፣ ለትምህርት ሚኒስቴር ግምገማ እንዲካሄድለት በደብዳቤ ጥያቄ ማቅረብ እንዳለበት ሰኔ 19 ቀን 2018 ዓ.ም. በትምህርት ሚኒስቴር የወጣው መመሪያ ያዛል፡፡ ሚኒስቴሩ በመመሪያው መሠረት 60 በመቶና ከዚያ በላይ ላስመዘገበ ተቋም የራስ ገዝነት ሽግግር ሒደት እንዲጀምር ፈቃድ ይሰጣል። ሚኒስቴሩም የቀረበለትን የግምገማ ውጤቱ መሠረት በማድረግ 6ዐ በመቶና ከዚያ በላይ ያገኘ ዩኒቨርሲቲ ወደ ራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲነት የሚያሸጋግረውን የሚፈቅድ የማቋቋሚያ ደንብ ከተቋሙ ጋር ተመካክሮ በማዘጋጀት፣ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት እንዲፀድቅለት ጥያቄ እንደሚያቀርብ በመሪያው ሠፍሯል። የዩኒቨርሲቲው የግምገማ ውጤት ዝቅተኛ ሆኖ ከተገኘ በታዩ ክፍተቶች ላይ የማሻሻያ መርሐግብር ተቋሙ እንዲያዘጋጅ አቅጣጫ በማስቀመጥና ውጤቱን እንዲያሻሽል ክትትል በማድረግ፣ በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ለሁለተኛ ጊዜ ግምገማ እንዲካሄድ ሁኔታዎችን ማመቻቸትም የሚኒስቴሩ ተግባር መሆኑ ተመልክቷል፡፡ #ሪፖርተር ለበለጠ መረጃ እና አስተያየት ካለዎት      👇👇👇 [https://t.me/allethioschool] [https://t.me/allethioschool]
179 ·

Вся лента · оригинал в Telegram

Open in Telegram Feed t.me/s Каталог площадок Искать в ChatCrawler

A snapshot of an open public feed from the search index ChatCrawler — “Google for public Telegram”; refreshed as the venue is crawled. Times are UTC.

Public content only, official Telegram API. About · FAQ · What we do not do · Remove a page · Catalog