Фотография
click to show
click to show
የጤና ባለሙያዎች የሙያ ፈቃድ ፈተና በነሐሴ ወር 2018 ዓ.ም ይሰጣል። - ጤና ሚኒስቴር
ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በመጀመሪያ ዲግሪ ለተመረቃችሁ የጤና ባለሙያዎች የሙያ ፈቃድ ፈተና በነሐሴ ወር 2018 ዓ.ም ለመስጠት ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የጤና ሚኒስቴር ገልጿል።
በመሆኑም መረጃችሁን ወደ ሲስተም ያላስገባችሁ ነባር እና አዲስ ተመዛኞች ከሰኔ 30 እስከ ሐምሌ 17/2018 ዓ.ም ድረስ ብቻ https://hple.moh.gov.et/ ላይ በመግባት የብሔራዊ መታወቂያ መለያ ቁጥር (FAN 16 Digit) በማስገባት አስፈላጊ መረጃዎችን በማሟላት ለምዝገባ እንድትዘጋጁ ሚኒስቴሩ አሳስቧል፡፡
መረጃ የማስተሳሰር ሂደት እንዳለቀ የፈተና ጣቢያ መረጣ ሂደት እንደሚቀጥል ተገልጿል፡፡
🔔 በሰኔ 2018 ዓ.ም የመውጫ ፈተና ተፈትናችሁ ያለፉችሁ ተመዛኞች የስም ዝርዝራችሁን በተማራችሁበት ተቋም አማካኝነት ወደ ሲስተም ማስጫን ይጠበቅባችኋል ተብሏል።
ለበለጠ መረጃ እና
አስተያየት ካለዎት
👇👇👇
[https://t.me/allethioschool]
[https://t.me/allethioschool]
137 ·