ChatCrawlersearch across public Telegram Open the app
E

ETHIO ≈ SCHOOL

сообщение · 2026-07-08 11:30 UTC
F
Фотография
click to show
#ETA የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን በትምህርት ማስረጃ ማረጋገጫ እና የአቻ ግመታ መመሪያ 990/2016 አንቀጽ 5 ንኡስ አንቀጽ 5 ላይ ብቻ ሀ፣ ለ እና ሐ ተብሎ ተጨምሮ በተዘጋጀው ማሻሻያ ረቂቅ ላይ የትምህርት ማኅበረሰቡ እና ባለድርሻ አካላት እስከ ሐምሌ 13/2018 ዓ.ም ከዚህ በታች በተቀመጡት አማራጮች አስተያየታቸውን እንዲሰጡ ጠይቋል። https://forms.gle/ndRhodE2yoHSn2P5A ሊንክን በመጫን አስተያየት መስጫውን ማግኘት ትችላላችሁ፤ አስተያየታችሁን ሞልታችሁ ስትጨርሱ (Submit) የሚለውን በመጫን አስተያየታችሁን መላክ የምትችሉ መሆኑ ተገልጿል። ማሻሻያ የተደረገበትን ረቂቅ አዋጅ በባለሥልጣኑ ድረ-ገፅ www.neta.gov.et ላይ ማግኘት ይቻላል። ለሚኖራችሁ ማንኛውም አስተያየት በባለሥልጣኑ ኢ-ሚይል አድራሻ [email protected] ላይ አስተያየታችሁን ሞልታችሁ መላክ ትችላላችሁ ተብሏል። በአካል ቀርባችሁ መረጃዎችንና አስተያየታችሁን መስጠት ለምትፈልጉ የፊት ለፊት የመወያያ መድረክ በቅርቡ እንደሚያዘጋጅ ባለሥልጣኑ ገልጿል። ለበለጠ መረጃ እና አስተያየት ካለዎት      👇👇👇 [https://t.me/allethioschool] [https://t.me/allethioschool]
152 ·

Вся лента · оригинал в Telegram

Open in Telegram Feed t.me/s Каталог площадок Искать в ChatCrawler

A snapshot of an open public feed from the search index ChatCrawler — “Google for public Telegram”; refreshed as the venue is crawled. Times are UTC.

Public content only, official Telegram API. About · FAQ · What we do not do · Remove a page · Catalog