ChatCrawlersearch across public Telegram Open the app
E

ETHIO ≈ SCHOOL

сообщение · 2026-07-10 13:16 UTC
F
Фотография
click to show
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ትምህርታቸውን በመከታተል ላይ የሚገኙ ከትግራይ ክልል የመጡ ተማሪዎች፣ የክረምት ወራት የእረፍት ጊዚያቸውን በዩኒቨርሲቲው እንዲቆዩ ዩኒቨርሲቲው ፈቅዷል፡፡ ተማሪዎቹ በትግራይ ክልል አለ ባሉት "አስገዳጅ የውትድርና ምልመላ" እና የፀጥታ ስጋት ምክንያት ወደ ቤተሰቦቻቸው መመለስ እንደማይችሉ በመግለፅ የዩኒቨርሲቲው አስተዳደር በክረምት የዕረፍት ወራት የማደሪያ አገልግሎት (Dormitory Service) እንዲፈቅድላቸው በቲክቫህ ኢትዮጵያ በኩል ጥሪ አቅርበው ነበር፡፡ ተማሪዎቹ ወደ ትግራይ የሚሔዱ ከሆነ ትምህርታቸው ሊቋርጥባቸው እንደሚችልም ስጋታቸውን ገልፀው ነበር፡፡ አሁን ላይ ተማሪዎቹ እስከሚቀጥለው የትምህርት ዓመት ድረስ አስፈላጊውን የምግብ እና የዶርም አገልግሎት እያገኙ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እንዲቆዩ የተፈቀደላቸው መሆኑን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከተማሪዎቹ ሰምቷል። የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የኮምዩኔኬሽን ዳይሬክተር ኤልያስ ወርቁ (ዶ/ር) ተማሪዎቹ በዩኒቨርሲቲው እንዲቆዩ መፍቀዱን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አረጋግጠዋል። "አስፈላጊው በጀት እንዲመጣ ተደርጎ ተማሪዎቹ በግቢው እንዲቆዩ ተደርጓል" ብለዋል። የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አካዳሚክ ምክትል ፕሬዝዳንት ጄይሉ ዑመር (ዶ/ር) ተማሪዎቹ በግቢው ያሉ መሆናቸውን አረጋግጠዋል። ላቀረቡት ቅሬታም ምላሽ የተሰጠ መሆኑን ገልፀዋል። ለበለጠ መረጃ እና አስተያየት ካለዎት      👇👇👇 [https://t.me/allethioschool] [https://t.me/allethioschool]
173 ·

Вся лента · оригинал в Telegram

Open in Telegram Feed t.me/s Каталог площадок Искать в ChatCrawler

A snapshot of an open public feed from the search index ChatCrawler — “Google for public Telegram”; refreshed as the venue is crawled. Times are UTC.

Public content only, official Telegram API. About · FAQ · What we do not do · Remove a page · Catalog